పవిత్ర ఖురాన్ యొక్క భావార్థాల అనువాదం - అమ్హారిక్ అనువాదం - ఆఫ్రికా అకాడమీ

పేజీ నెంబరు:close

external-link copy
60 : 6

وَهُوَ ٱلَّذِي يَتَوَفَّىٰكُم بِٱلَّيۡلِ وَيَعۡلَمُ مَا جَرَحۡتُم بِٱلنَّهَارِ ثُمَّ يَبۡعَثُكُمۡ فِيهِ لِيُقۡضَىٰٓ أَجَلٞ مُّسَمّٗىۖ ثُمَّ إِلَيۡهِ مَرۡجِعُكُمۡ ثُمَّ يُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ

60. እርሱ (አላህ) ያ በሌሊት የሚያስተኛችሁ በቀን የሰራችሁትንም ሁሉ የሚያውቅ ከዚያም የተወሰነው ጊዜ ይፈጸም ዘንድ በቀን ውስጥ የሚቀሰቅሳችሁ ነው:: ከዚያም መመለሻችሁ ወደ እርሱ ብቻ ነው:: ከዚያም ትሰሩት የነበራችሁትን ነገር ሁሉ ይነግራችኋል:: info
التفاسير:

external-link copy
61 : 6

وَهُوَ ٱلۡقَاهِرُ فَوۡقَ عِبَادِهِۦۖ وَيُرۡسِلُ عَلَيۡكُمۡ حَفَظَةً حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءَ أَحَدَكُمُ ٱلۡمَوۡتُ تَوَفَّتۡهُ رُسُلُنَا وَهُمۡ لَا يُفَرِّطُونَ

61. እርሱ ከባሮቹ በላይ ሲሆን ሁሉን አሸናፊ ነው:: በእናንተ ላይም ተጠባባቂዎች መላዕክትን ይልካል:: አንዳችሁንም የሞት ሰዓቱ በመጣበት ጊዜ የሞት መልዕክተኞቻችን ትዕዛዛትን የማያጓድሉ ሲሆኑ ይገድሉታል:: info
التفاسير:

external-link copy
62 : 6

ثُمَّ رُدُّوٓاْ إِلَى ٱللَّهِ مَوۡلَىٰهُمُ ٱلۡحَقِّۚ أَلَا لَهُ ٱلۡحُكۡمُ وَهُوَ أَسۡرَعُ ٱلۡحَٰسِبِينَ

62. ከዚያም እውነተኛ ወደ ሆነው ጌታቸው ወደ አላህ ይመለሳሉ:: (ሰዎች ሆይ!) አስትዉሉ! አዋጅ ፍርዱ ለእርሱ ብቻ ነው:: እርሱም ከተቆጣጣሪዎች ሁሉ ይበልጥ ፈጣን ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
63 : 6

قُلۡ مَن يُنَجِّيكُم مِّن ظُلُمَٰتِ ٱلۡبَرِّ وَٱلۡبَحۡرِ تَدۡعُونَهُۥ تَضَرُّعٗا وَخُفۡيَةٗ لَّئِنۡ أَنجَىٰنَا مِنۡ هَٰذِهِۦ لَنَكُونَنَّ مِنَ ٱلشَّٰكِرِينَ

63. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ያ ከየብስና ከባህር ጨለማዎች በግልጽና በሚስጢር ‹ከዚህ ቢያድነን ከአመስጋኞች እንሆናለን› ስትሉ የምትጠሩት ስትሆኑ የሚያድናችሁ ማን ነው?» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
64 : 6

قُلِ ٱللَّهُ يُنَجِّيكُم مِّنۡهَا وَمِن كُلِّ كَرۡبٖ ثُمَّ أَنتُمۡ تُشۡرِكُونَ

64. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ ከእርሷና ከጭንቅም ሁሉ ያድናችኋል:: ከዚያ እናንተ በእሱ ባዕድ አምላክን ታጋራላችሁ።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
65 : 6

قُلۡ هُوَ ٱلۡقَادِرُ عَلَىٰٓ أَن يَبۡعَثَ عَلَيۡكُمۡ عَذَابٗا مِّن فَوۡقِكُمۡ أَوۡ مِن تَحۡتِ أَرۡجُلِكُمۡ أَوۡ يَلۡبِسَكُمۡ شِيَعٗا وَيُذِيقَ بَعۡضَكُم بَأۡسَ بَعۡضٍۗ ٱنظُرۡ كَيۡفَ نُصَرِّفُ ٱلۡأٓيَٰتِ لَعَلَّهُمۡ يَفۡقَهُونَ

65. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እርሱ (አላህ) ከበላያችሁ ወይም ከእግሮቻችሁ በታች ቅጣትን በእናንተ ላይ ሊልክ ወይም የተለያዩ ሕዝቦች ስትሆኑ ሊያደባልቃችሁና ከፊላችሁን የከፊሉን ጭካኔ ሊያቀምስ ቻይ ነው።» በላቸው። ይገነዘቡ ዘንድ አናቅጽን እንዴት እንደምናብራራ ተመልከት። info
التفاسير:

external-link copy
66 : 6

وَكَذَّبَ بِهِۦ قَوۡمُكَ وَهُوَ ٱلۡحَقُّۚ قُل لَّسۡتُ عَلَيۡكُم بِوَكِيلٖ

66. እርሱ(ቁርኣን) ከአላህ የመጣ እውነት ሲሆን ህዝቦችህ ግን አስተባበሉት:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በናንተ ላይ ጠባቂ አይደለሁም።» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
67 : 6

لِّكُلِّ نَبَإٖ مُّسۡتَقَرّٞۚ وَسَوۡفَ تَعۡلَمُونَ

67. ለየወሬ ሁሉ የሚደርስበት መፈጸሚያ ጊዜ አለው:: ወደ ፊትም በትክክል ታውቁታላችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
68 : 6

وَإِذَا رَأَيۡتَ ٱلَّذِينَ يَخُوضُونَ فِيٓ ءَايَٰتِنَا فَأَعۡرِضۡ عَنۡهُمۡ حَتَّىٰ يَخُوضُواْ فِي حَدِيثٍ غَيۡرِهِۦۚ وَإِمَّا يُنسِيَنَّكَ ٱلشَّيۡطَٰنُ فَلَا تَقۡعُدۡ بَعۡدَ ٱلذِّكۡرَىٰ مَعَ ٱلۡقَوۡمِ ٱلظَّٰلِمِينَ

68. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ አናቅጻችንን ለማስተባበል ወደ ክርክር የሚገቡትን ሰዎች በምታይ ጊዜ በሌላ ወሬ እስከሚገቡ ድረስ ተዋቸው:: ሰይጣንም መከልከልህን ቢያስረሳህና አብረሀቸው ሆነህ እንኳን ካስታወስክ በኋላ ከበደለኞች ሕዝቦች ጋር አትቀመጥ:: info
التفاسير: