పవిత్ర ఖురాన్ యొక్క భావార్థాల అనువాదం - అమ్హారిక్ అనువాదం - ఆఫ్రికా అకాడమీ

పేజీ నెంబరు:close

external-link copy
131 : 6

ذَٰلِكَ أَن لَّمۡ يَكُن رَّبُّكَ مُهۡلِكَ ٱلۡقُرَىٰ بِظُلۡمٖ وَأَهۡلُهَا غَٰفِلُونَ

131. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ የሆነው ጌታህ ከተሞችን ባለቤቶችዋ (ማስጠንቀቂያ ያልመጣላቸው) ዘንጊዎች ሆነው ሳሉ በበደል ምክንያት አጥፊ ባለመሆኑ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
132 : 6

وَلِكُلّٖ دَرَجَٰتٞ مِّمَّا عَمِلُواْۚ وَمَا رَبُّكَ بِغَٰفِلٍ عَمَّا يَعۡمَلُونَ

132. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለሁሉም ከሰሩት (አንፃር) የተበላለጡ ደረጃዎች አሏቸው:: ጌታህም ከሚሰሩት ስራ ዝንጉ አይደለም:: info
التفاسير:

external-link copy
133 : 6

وَرَبُّكَ ٱلۡغَنِيُّ ذُو ٱلرَّحۡمَةِۚ إِن يَشَأۡ يُذۡهِبۡكُمۡ وَيَسۡتَخۡلِفۡ مِنۢ بَعۡدِكُم مَّا يَشَآءُ كَمَآ أَنشَأَكُم مِّن ذُرِّيَّةِ قَوۡمٍ ءَاخَرِينَ

133. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም በራሱ ተብቃቂ የእዝነት ባለቤት ነው:: ቢሻ ከምድረ ገጽ ያጠፋችኋል:: ከሌሎች ህዝቦችም ዘሮች እንዳስገኛችሁ ሁሉ ከበኋላችሁም የሚሻውን ሰው ይተካል:: info
التفاسير:

external-link copy
134 : 6

إِنَّ مَا تُوعَدُونَ لَأٓتٖۖ وَمَآ أَنتُم بِمُعۡجِزِينَ

134. (ሰዎች ሆይ!) የምትቀጠሩት ሁሉ በእርግጥ መጪ ነው:: እናንተም የምታቅቱ አይደላችሁም:: info
التفاسير:

external-link copy
135 : 6

قُلۡ يَٰقَوۡمِ ٱعۡمَلُواْ عَلَىٰ مَكَانَتِكُمۡ إِنِّي عَامِلٞۖ فَسَوۡفَ تَعۡلَمُونَ مَن تَكُونُ لَهُۥ عَٰقِبَةُ ٱلدَّارِۚ إِنَّهُۥ لَا يُفۡلِحُ ٱلظَّٰلِمُونَ

135. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ህዝቦቼ ሆይ! በችሎታችሁ ላይ ስሩ እኔ በችሎታዬ ላይ ሰሪ ነኝና:: ምስጉኒቱ ሀገር ገነት ለእርሱ የምትሆንለት ሰው ማን እንደሆነ ወደፊት ታውቃላችሁ:: እነሆ በደለኞች ሁሉ ምንጊዜም አይድኑም።» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
136 : 6

وَجَعَلُواْ لِلَّهِ مِمَّا ذَرَأَ مِنَ ٱلۡحَرۡثِ وَٱلۡأَنۡعَٰمِ نَصِيبٗا فَقَالُواْ هَٰذَا لِلَّهِ بِزَعۡمِهِمۡ وَهَٰذَا لِشُرَكَآئِنَاۖ فَمَا كَانَ لِشُرَكَآئِهِمۡ فَلَا يَصِلُ إِلَى ٱللَّهِۖ وَمَا كَانَ لِلَّهِ فَهُوَ يَصِلُ إِلَىٰ شُرَكَآئِهِمۡۗ سَآءَ مَا يَحۡكُمُونَ

136. አጋሪዎች ለአላህ ከፈጠራቸው ፍጡራን ከአዝመራውም ከግመል፣ ከከብት፣ ከፍየል፤ ከበጉም ድርሻን አደረጉለት:: በሀሳባቸዉም «ይህ የአላህ ነው፤ ይህ ደግሞ ለተጋሪዎቻችን ነው።» አሉ። ለተጋሪዎቻቸው የሆነው ነገር ወደ አላህ ምንጊዜም አይደርስም:: ለአላህ የሆነው ነገር ግን ወደ ተጋሪዎቹ ይደርሳል አሉ። የሚፈርዱት ፍርድ ከፋ! info
التفاسير:

external-link copy
137 : 6

وَكَذَٰلِكَ زَيَّنَ لِكَثِيرٖ مِّنَ ٱلۡمُشۡرِكِينَ قَتۡلَ أَوۡلَٰدِهِمۡ شُرَكَآؤُهُمۡ لِيُرۡدُوهُمۡ وَلِيَلۡبِسُواْ عَلَيۡهِمۡ دِينَهُمۡۖ وَلَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ مَا فَعَلُوهُۖ فَذَرۡهُمۡ وَمَا يَفۡتَرُونَ

137. ልክ እንደዚሁ ከአጋሪዎች ለብዙዎቹ ሊያጠፏቸውና ሀይማኖታቸውንም በነሱ ላይ ሊያቀላቅሉባቸው ዘንድ ልጆቻቸውን መግደልን ተጋሪዎቻቸው ጣኦታቱ አሳመሩላቸው:: አላህም በሻ ኖሮ (ይህን ጸያፍ ተግባር) ባልሰሩት ነበር:: እናም ከቅጥፈታቸው ጋር ተዋቸው:: info
التفاسير: