పవిత్ర ఖురాన్ యొక్క భావార్థాల అనువాదం - అమ్హారిక్ అనువాదం - ఆఫ్రికా అకాడమీ

పేజీ నెంబరు:close

external-link copy
95 : 6

۞ إِنَّ ٱللَّهَ فَالِقُ ٱلۡحَبِّ وَٱلنَّوَىٰۖ يُخۡرِجُ ٱلۡحَيَّ مِنَ ٱلۡمَيِّتِ وَمُخۡرِجُ ٱلۡمَيِّتِ مِنَ ٱلۡحَيِّۚ ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُۖ فَأَنَّىٰ تُؤۡفَكُونَ

95. አላህ የፍሬና የዛፍ ቅንጣትን ፈልቃቂ ነው:: ከሙት ነገር ሕያውን ያወጣል:: ከሕያዉም ነገር ሙትን አውጭ ነው:: ይህ አላህ ጌታችሁ ነው:: ታዲያ እንዴት ከእውነት ትሸሻላችሁ (ትርቃላችሁ)? info
التفاسير:

external-link copy
96 : 6

فَالِقُ ٱلۡإِصۡبَاحِ وَجَعَلَ ٱلَّيۡلَ سَكَنٗا وَٱلشَّمۡسَ وَٱلۡقَمَرَ حُسۡبَانٗاۚ ذَٰلِكَ تَقۡدِيرُ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡعَلِيمِ

96. ጎሕን ከጽልመት ጨለማ ፈልቃቂ፤ ሌሊቱን ማረፊያ፤ ጸሐይንና ጨረቃን ለጊዜ ስሌት መጠቀሚያ ያደረገ አምላክ ነው:: ይህ የዚያ የአሸናፊውና የሁሉን አዋቂው አምላክ ውሳኔ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
97 : 6

وَهُوَ ٱلَّذِي جَعَلَ لَكُمُ ٱلنُّجُومَ لِتَهۡتَدُواْ بِهَا فِي ظُلُمَٰتِ ٱلۡبَرِّ وَٱلۡبَحۡرِۗ قَدۡ فَصَّلۡنَا ٱلۡأٓيَٰتِ لِقَوۡمٖ يَعۡلَمُونَ

97. አላህ ያ በየብስና በባህር ጨለማዎች ውስጥ ራሳችሁን መምራት ትችሉ ዘንድ ከዋክብትን የፈጠረላችሁ አምላክ ነው:: ለሚያውቁ ሁሉ አናቅጽን በሚገባ አብራርተናል:: info
التفاسير:

external-link copy
98 : 6

وَهُوَ ٱلَّذِيٓ أَنشَأَكُم مِّن نَّفۡسٖ وَٰحِدَةٖ فَمُسۡتَقَرّٞ وَمُسۡتَوۡدَعٞۗ قَدۡ فَصَّلۡنَا ٱلۡأٓيَٰتِ لِقَوۡمٖ يَفۡقَهُونَ

98. (ሰዎች ሆይ! ) እርሱ (አላህ) ያ ከአንዲት ነፍስ ያስገኛችሁ አምላክ ነው:: በማሕጸን ውስጥ ማረፊያንና ምድር ላይም መኖሪያን አመቻቸላችሁ:: መገንዘብ ለሚችሉ ሁሉ አናቅጽን በሚገባ አብራርተናል:: info
التفاسير:

external-link copy
99 : 6

وَهُوَ ٱلَّذِيٓ أَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ فَأَخۡرَجۡنَا بِهِۦ نَبَاتَ كُلِّ شَيۡءٖ فَأَخۡرَجۡنَا مِنۡهُ خَضِرٗا نُّخۡرِجُ مِنۡهُ حَبّٗا مُّتَرَاكِبٗا وَمِنَ ٱلنَّخۡلِ مِن طَلۡعِهَا قِنۡوَانٞ دَانِيَةٞ وَجَنَّٰتٖ مِّنۡ أَعۡنَابٖ وَٱلزَّيۡتُونَ وَٱلرُّمَّانَ مُشۡتَبِهٗا وَغَيۡرَ مُتَشَٰبِهٍۗ ٱنظُرُوٓاْ إِلَىٰ ثَمَرِهِۦٓ إِذَآ أَثۡمَرَ وَيَنۡعِهِۦٓۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكُمۡ لَأٓيَٰتٖ لِّقَوۡمٖ يُؤۡمِنُونَ

99. እርሱ (አላህ) ያ ከሰማይ ውሃን ያወረደ አምላክ ነው:: በእርሱም የሁሉንም ዓይነት እጽዋት አበቀልን:: የተደራረበን ቅንጣት የምናወጣበትን ለምለም አዝመራም ከርሱ አወጣን:: ከዘንባባ እንቡጥም የተቀራረቡ የሆኑ ዘለላዎችን አወጣን:: የወይን አትክልት ቦታዎችን አዘጋጀን:: ቅጠሎቻቸው የሚመሳሰሉ ፍሬዎቻቸው ግን የማይመሳሰሉ የሆኑትን የዘይቱን(ወይራ) እና የሩማን እጽዋትም ከሰማይ ባወረድነው ዝናብ አበቀልን:: (የሰው ልጆች ሆይ!) ፍሬውን ባፈራና በበሰለ ጊዜ እስቲ ተመልከቱት:: እጅግ አስደናቂ ሆኖ ታገኙታላችሁ:: በእነዚህ ክስተቶች ውስጥ በትክክል በአላህ ለሚያምኑ ሰዎች ሁሉ በርካታ ተአምራት አሉበት:: info
التفاسير:

external-link copy
100 : 6

وَجَعَلُواْ لِلَّهِ شُرَكَآءَ ٱلۡجِنَّ وَخَلَقَهُمۡۖ وَخَرَقُواْ لَهُۥ بَنِينَ وَبَنَٰتِۭ بِغَيۡرِ عِلۡمٖۚ سُبۡحَٰنَهُۥ وَتَعَٰلَىٰ عَمَّا يَصِفُونَ

100. (ሰዎች) የፈጠራቸው አላህ ሲሆን አጋንንትን በመታዘዝ ለእርሱ ተጋሪዎች አደረጉ:: ወንዶች ልጆችና ሴቶች ልጆች አለው በማለት ያለ ዕውቀት በእርሱ ላይ ቀጠፉ:: አላህ ጥራት የተገባውና ከሚሉት ነገር ሁሉ የላቀ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
101 : 6

بَدِيعُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ أَنَّىٰ يَكُونُ لَهُۥ وَلَدٞ وَلَمۡ تَكُن لَّهُۥ صَٰحِبَةٞۖ وَخَلَقَ كُلَّ شَيۡءٖۖ وَهُوَ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمٞ

101. እርሱ ሰማያትንና ምድርን ያለ ብጤ ፈጣሪ ነው:: ለእርሱም ሚስት የሌለው ሲሆን እንዴት ለእርሱ ልጅ ይኖረዋል? ሁሉንም ነገር ፈጠረ:: እርሱ ሁሉንም ነገር አዋቂ ነውና:: info
التفاسير: