పవిత్ర ఖురాన్ యొక్క భావార్థాల అనువాదం - అమ్హారిక్ అనువాదం - ఆఫ్రికా అకాడమీ

పేజీ నెంబరు:close

external-link copy
125 : 6

فَمَن يُرِدِ ٱللَّهُ أَن يَهۡدِيَهُۥ يَشۡرَحۡ صَدۡرَهُۥ لِلۡإِسۡلَٰمِۖ وَمَن يُرِدۡ أَن يُضِلَّهُۥ يَجۡعَلۡ صَدۡرَهُۥ ضَيِّقًا حَرَجٗا كَأَنَّمَا يَصَّعَّدُ فِي ٱلسَّمَآءِۚ كَذَٰلِكَ يَجۡعَلُ ٱللَّهُ ٱلرِّجۡسَ عَلَى ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ

125. አላህ ሊመራው የሚሻውን ሁሉ ልቡን ለኢስላም ይከፍትለታል:: ሊያጠመው የሚሻውን ደግሞ ልቡን ጠባብና ተቸጋሪ ወደ ሰማይ ለመውጣት እንደሚታገል ያደርገዋል:: ልክ እንደዚሁ አላህ በእነዚያ በማያምኑት ሰዎች ላይ ርክሰትን ያደርጋል:: info
التفاسير:

external-link copy
126 : 6

وَهَٰذَا صِرَٰطُ رَبِّكَ مُسۡتَقِيمٗاۗ قَدۡ فَصَّلۡنَا ٱلۡأٓيَٰتِ لِقَوۡمٖ يَذَّكَّرُونَ

126. ይህ ያለህበት መንገድ ቀጥተኛ ሲሆን የጌታህ መንገድ ነው:: ለሚያስታውሱ ህዝቦች አናቅጽን እርግጥ ዘርዝረናል:: info
التفاسير:

external-link copy
127 : 6

۞ لَهُمۡ دَارُ ٱلسَّلَٰمِ عِندَ رَبِّهِمۡۖ وَهُوَ وَلِيُّهُم بِمَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ

127. ለእነርሱም በጌታቸው ዘንድ የሰላም ሀገር አለላቸው። እርሱ ይሰሩት በነበሩት ምክንያትም ረዳታቸው ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
128 : 6

وَيَوۡمَ يَحۡشُرُهُمۡ جَمِيعٗا يَٰمَعۡشَرَ ٱلۡجِنِّ قَدِ ٱسۡتَكۡثَرۡتُم مِّنَ ٱلۡإِنسِۖ وَقَالَ أَوۡلِيَآؤُهُم مِّنَ ٱلۡإِنسِ رَبَّنَا ٱسۡتَمۡتَعَ بَعۡضُنَا بِبَعۡضٖ وَبَلَغۡنَآ أَجَلَنَا ٱلَّذِيٓ أَجَّلۡتَ لَنَاۚ قَالَ ٱلنَّارُ مَثۡوَىٰكُمۡ خَٰلِدِينَ فِيهَآ إِلَّا مَا شَآءَ ٱللَّهُۚ إِنَّ رَبَّكَ حَكِيمٌ عَلِيمٞ

128. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሁሉንም በአንድ ቦታ በሚሰበስባቸው ቀን የሚሆነውን አስታውስ:: «የአጋንንት ቡድኖች ሆይ! ከሰዎች ቡድንን በማጥመም በእርግጥ አበዛችሁ።» ይባላሉ:: ከሰዎችም መካከል የሆኑት ወዳጆቻቸው «ጌታችን ሆይ! ከፊላችን በከፊሉ ተጠቀመ:: ያንን ለእኛ የወሰንክልንን ጊዜያችንን ደረስን።» ይላሉ:: «እሳቲቱ አላህ የሻው ጊዜ ሲቀር በውስጧ ዘወታሪዎች ስትሆኑ መኖሪያችሁ ናት።» ይላቸዋል:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ጥበበኛና አዋቂ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
129 : 6

وَكَذَٰلِكَ نُوَلِّي بَعۡضَ ٱلظَّٰلِمِينَ بَعۡضَۢا بِمَا كَانُواْ يَكۡسِبُونَ

129. ልክ እንደዚሁ አንዳንድ በደለኞችን ይሰሩት በነበሩት ጥፋት ምክንያት በከፊሎች ላይ እንሾማለን:: info
التفاسير:

external-link copy
130 : 6

يَٰمَعۡشَرَ ٱلۡجِنِّ وَٱلۡإِنسِ أَلَمۡ يَأۡتِكُمۡ رُسُلٞ مِّنكُمۡ يَقُصُّونَ عَلَيۡكُمۡ ءَايَٰتِي وَيُنذِرُونَكُمۡ لِقَآءَ يَوۡمِكُمۡ هَٰذَاۚ قَالُواْ شَهِدۡنَا عَلَىٰٓ أَنفُسِنَاۖ وَغَرَّتۡهُمُ ٱلۡحَيَوٰةُ ٱلدُّنۡيَا وَشَهِدُواْ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمۡ أَنَّهُمۡ كَانُواْ كَٰفِرِينَ

130. «የአጋንትና የሰዎች ቡድኖች ሆይ! አንቀፆቼን በእናንተ ላይ የሚተርኩ የዚህንም ቀናችሁን ቅጣት ማግኘትን የሚያስፈራሯችሁ ከናንተው የሆኑ መልዕክተኞች አልመጡላችሁም ነበርን?» ይባላሉ:: «በነፍሶቻችን ላይ መሰከርን።» ይላሉ። የዱንያ ህይወት አታለለቻቸው። በነፍሶቻቸው ላይ እነርሱ ከሓዲያን የነበሩ መሆናቸውንም በራሳቸው መሰከሩ። info
التفاسير: