పవిత్ర ఖురాన్ యొక్క భావార్థాల అనువాదం - అమ్హారిక్ అనువాదం - ఆఫ్రికా అకాడమీ

పేజీ నెంబరు:close

external-link copy
36 : 6

۞ إِنَّمَا يَسۡتَجِيبُ ٱلَّذِينَ يَسۡمَعُونَۘ وَٱلۡمَوۡتَىٰ يَبۡعَثُهُمُ ٱللَّهُ ثُمَّ إِلَيۡهِ يُرۡجَعُونَ

36. ጥሪን የሚቀበሉት እነዚያ የሚሰሙት ብቻ ናቸው:: ሙታንማ አላህ ይቀሰቅሳቸዋል:: ከዚያም ወደ እርሱ ብቻ ይመለሳሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
37 : 6

وَقَالُواْ لَوۡلَا نُزِّلَ عَلَيۡهِ ءَايَةٞ مِّن رَّبِّهِۦۚ قُلۡ إِنَّ ٱللَّهَ قَادِرٌ عَلَىٰٓ أَن يُنَزِّلَ ءَايَةٗ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ

37. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሓዲያን «ከጌታው በእርሱ ላይ ለምን ተአምር አልተወረደለትም?» አሉ:: «አላህ ተአምርን ለማውረድ ቻይ ነው:: ግን አብዛኞቻቸው ይህን እውነታ አያውቁም።» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
38 : 6

وَمَا مِن دَآبَّةٖ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلَا طَٰٓئِرٖ يَطِيرُ بِجَنَاحَيۡهِ إِلَّآ أُمَمٌ أَمۡثَالُكُمۚ مَّا فَرَّطۡنَا فِي ٱلۡكِتَٰبِ مِن شَيۡءٖۚ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّهِمۡ يُحۡشَرُونَ

38. በምድር ላይ የሚሄድ ተንቀሳቃሽም ሆነ በሁለት ክንፎቹ የሚበር ሁሉ መሰሎቻችሁ ሕዝቦች እንጂ ሌላ አይደሉም:: በመጽሐፉ ውስጥ ምንንም ነገር አልተውንም:: ከዚያ ሁሉም ወደ ጌታቸው ይሰበሰባሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
39 : 6

وَٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا صُمّٞ وَبُكۡمٞ فِي ٱلظُّلُمَٰتِۗ مَن يَشَإِ ٱللَّهُ يُضۡلِلۡهُ وَمَن يَشَأۡ يَجۡعَلۡهُ عَلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ

39. እነዚያ በአናቅጻችን ያስተባበሉ ሁሉ እውነትን የማይሰሙ ደንቆሮዎች፤ ሐቅን የማይናገሩ ዲዳዎችና በጨለማዎች ውስጥ ያሉ ናቸው:: አላህ መጥመሙን የሚሻበትን ሰው ያጠመዋል:: ወደ ቀናው መንገድ መመራቱን የሚሻለትን ሰው ደግሞ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ያደርገዋል:: info
التفاسير:

external-link copy
40 : 6

قُلۡ أَرَءَيۡتَكُمۡ إِنۡ أَتَىٰكُمۡ عَذَابُ ٱللَّهِ أَوۡ أَتَتۡكُمُ ٱلسَّاعَةُ أَغَيۡرَ ٱللَّهِ تَدۡعُونَ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ

40. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የአላህ ቅጣት ቢመጣባችሁ ወይም ትንሳኤ ብትመጣባችሁ ከአላህ ሌላ ትጠራላችሁን? እውነተኞች ከሆናችሁ (እስኪ ንገሩኝ።)» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
41 : 6

بَلۡ إِيَّاهُ تَدۡعُونَ فَيَكۡشِفُ مَا تَدۡعُونَ إِلَيۡهِ إِن شَآءَ وَتَنسَوۡنَ مَا تُشۡرِكُونَ

41. «በፍፁም። እውነታው እርሱን ብቻ ትጠራላችሁ:: ቢሻ ወደ እርሱ የምትጠሩበትን ነገር ያስወግድላችኋልና የምታጋሩትንም ሁሉ ትረሱታላችሁ።» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
42 : 6

وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَآ إِلَىٰٓ أُمَمٖ مِّن قَبۡلِكَ فَأَخَذۡنَٰهُم بِٱلۡبَأۡسَآءِ وَٱلضَّرَّآءِ لَعَلَّهُمۡ يَتَضَرَّعُونَ

42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት ለነበሩት ሕዝቦች አያሌ መልዕክተኞችን በእርግጥ ላክን:: (ከዚያም እንቢተኛ ሆኑ::) ለእኛ ይተናነሱም ዘንድ በድህነትና በችግር ቀጣናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
43 : 6

فَلَوۡلَآ إِذۡ جَآءَهُم بَأۡسُنَا تَضَرَّعُواْ وَلَٰكِن قَسَتۡ قُلُوبُهُمۡ وَزَيَّنَ لَهُمُ ٱلشَّيۡطَٰنُ مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ

43. ታዲያ ቅጣታችን በመጣባቸው ጊዜ አይተናነሱም ኖሯልን? ነገር ግን ልቦቻቸው ደረቁ:: ይሰሩት የነበሩትንም መጥፎ ነገር ሰይጣን መልካም ነገር አስመስሎ አሳያቸው። info
التفاسير:

external-link copy
44 : 6

فَلَمَّا نَسُواْ مَا ذُكِّرُواْ بِهِۦ فَتَحۡنَا عَلَيۡهِمۡ أَبۡوَٰبَ كُلِّ شَيۡءٍ حَتَّىٰٓ إِذَا فَرِحُواْ بِمَآ أُوتُوٓاْ أَخَذۡنَٰهُم بَغۡتَةٗ فَإِذَا هُم مُّبۡلِسُونَ

44. በእርሱ ይገሰጹበት የነበረውን ነገር በዘነጉ ጊዜ ለእነርሱ የሁሉን ነገር ደጃፎችን ከፈትንላቸውና በኑሮ አስመቸናቸው:: በተሰጡትም ነገር በተደሰቱ ጊዜ በድንገት ያዝናቸው:: ወዲያውኑም እነርሱ ተስፋ ቆራጮች ሆኑ። info
التفاسير: