పవిత్ర ఖురాన్ యొక్క భావార్థాల అనువాదం - అమ్హారిక్ అనువాదం - ఆఫ్రికా అకాడమీ

పేజీ నెంబరు:close

external-link copy
74 : 6

۞ وَإِذۡ قَالَ إِبۡرَٰهِيمُ لِأَبِيهِ ءَازَرَ أَتَتَّخِذُ أَصۡنَامًا ءَالِهَةً إِنِّيٓ أَرَىٰكَ وَقَوۡمَكَ فِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٖ

74. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢብራሂም ለአባቱ ለአዘር፡- «ጣኦትን አማልክት ታደርጋለህን? እኔ አንተንም ወገኖችህንም ግልጽ ጥመት ውስጥ ሆናችሁ አየኋችሁ።» ባለው ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: info
التفاسير:

external-link copy
75 : 6

وَكَذَٰلِكَ نُرِيٓ إِبۡرَٰهِيمَ مَلَكُوتَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَلِيَكُونَ مِنَ ٱلۡمُوقِنِينَ

75. ልክ በዚህ አኳኋን ኢብራሂም ጽኑ እምነት ይኖረው ዘንድ የሰማያትንና የምድርን ግዛት አሳየነው:: info
التفاسير:

external-link copy
76 : 6

فَلَمَّا جَنَّ عَلَيۡهِ ٱلَّيۡلُ رَءَا كَوۡكَبٗاۖ قَالَ هَٰذَا رَبِّيۖ فَلَمَّآ أَفَلَ قَالَ لَآ أُحِبُّ ٱلۡأٓفِلِينَ

76. ሌሊቱ በጽልመቱ በሸፈነው ጊዜ አንድ ኮከብ አየ። «ይህ ጌታዬ ነው» አለም:: ኮከቡ በጠለቀ ጊዜም፡- «ጠላቂዎችን አልወድም» አለ:: info
التفاسير:

external-link copy
77 : 6

فَلَمَّا رَءَا ٱلۡقَمَرَ بَازِغٗا قَالَ هَٰذَا رَبِّيۖ فَلَمَّآ أَفَلَ قَالَ لَئِن لَّمۡ يَهۡدِنِي رَبِّي لَأَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡقَوۡمِ ٱلضَّآلِّينَ

77. ጨረቃውን ደምቆ ባየ ጊዜም፡- «ይህ ጌታዬ ነው።» አለ:: ጨረቃውም በጠለቀ ጊዜ፡- «ጌታዬ ቅኑን ጎዳና ካልመራኝ መንገድ ከተሳሳቱ ሰዎች እሆናለሁ።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
78 : 6

فَلَمَّا رَءَا ٱلشَّمۡسَ بَازِغَةٗ قَالَ هَٰذَا رَبِّي هَٰذَآ أَكۡبَرُۖ فَلَمَّآ أَفَلَتۡ قَالَ يَٰقَوۡمِ إِنِّي بَرِيٓءٞ مِّمَّا تُشۡرِكُونَ

78. ጸሐይዋንም ደምቃ ጮራዋን ባየ ጊዜ፡- «ይህ ጌታዬ ነው። ይህ በጣም ትልቅ ነው።» አለ:: በጠለቀችም ጊዜ (አንዲህ) አለ፡- «ወገኖቼ ሆይ! እኔ ከምታጋሩት ሁሉ የጠራሁ ነኝ። info
التفاسير:

external-link copy
79 : 6

إِنِّي وَجَّهۡتُ وَجۡهِيَ لِلَّذِي فَطَرَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ حَنِيفٗاۖ وَمَآ أَنَا۠ مِنَ ٱلۡمُشۡرِكِينَ

79. «እኔ ወደ ቀጥተኛው ሃይማኖት የተዘነበልኩ ስሆን ፊቴን ሰማያትንና ምድርን ወደ ፈጠረው አምላክ አላህ አዙሬያለሁ:: እናም ከአጋሪዎችም አይደለሁም።» (አለ)። info
التفاسير:

external-link copy
80 : 6

وَحَآجَّهُۥ قَوۡمُهُۥۚ قَالَ أَتُحَٰٓجُّوٓنِّي فِي ٱللَّهِ وَقَدۡ هَدَىٰنِۚ وَلَآ أَخَافُ مَا تُشۡرِكُونَ بِهِۦٓ إِلَّآ أَن يَشَآءَ رَبِّي شَيۡـٔٗاۚ وَسِعَ رَبِّي كُلَّ شَيۡءٍ عِلۡمًاۚ أَفَلَا تَتَذَكَّرُونَ

80. ወገኖቹም ተከራከሩት። (እርሱም) አላቸው: «በእርግጥ የመራኝ ስሆን በአላህ ጉዳይ ትከራከሩኛላችሁን? በእርሱም የምታጋሩትን ነገር አልፈራም:: ግን ጌታዬ ቢሻ (ያገኘኛል):: ጌታዬም ሁሉንም ነገር በእውቀቱ ሰፋ። አትገነዘቡምን? info
التفاسير:

external-link copy
81 : 6

وَكَيۡفَ أَخَافُ مَآ أَشۡرَكۡتُمۡ وَلَا تَخَافُونَ أَنَّكُمۡ أَشۡرَكۡتُم بِٱللَّهِ مَا لَمۡ يُنَزِّلۡ بِهِۦ عَلَيۡكُمۡ سُلۡطَٰنٗاۚ فَأَيُّ ٱلۡفَرِيقَيۡنِ أَحَقُّ بِٱلۡأَمۡنِۖ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ

81. «በእናንተ ላይ በእርሱ ማስረጃ ያላወረደበትን እናንተ ማጋራታችሁን የማትፈሩ ስትሆኑ የምታጋሩትን ጣዖት እንዴት እኔ እፈራለሁ?! የምታውቁም ብትሆኑ ከሁለቱ ክፍሎች ደህና ለመሆን ይበልጥ ተገቢው ማንኛው ነው?» አለ። info
التفاسير: