పవిత్ర ఖురాన్ యొక్క భావార్థాల అనువాదం - అమ్హారిక్ అనువాదం - ఆఫ్రికా అకాడమీ

పేజీ నెంబరు:close

external-link copy
102 : 6

ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمۡۖ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۖ خَٰلِقُ كُلِّ شَيۡءٖ فَٱعۡبُدُوهُۚ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ وَكِيلٞ

102. ይህ ጌታችሁ አላህ ነው:: ከእርሱ በስተቀር አምላክ የለም:: ሁሉን ነገር ፈጣሪ ነው:: ስለዚህ እርሱን ብቻ ተገዙት:: እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
103 : 6

لَّا تُدۡرِكُهُ ٱلۡأَبۡصَٰرُ وَهُوَ يُدۡرِكُ ٱلۡأَبۡصَٰرَۖ وَهُوَ ٱللَّطِيفُ ٱلۡخَبِيرُ

103. አይኖች አያገኙትም:: እርሱ ግን አይኖችን ያያል:: እርሱም ሩህሩህና ውስጠ አዋቂ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
104 : 6

قَدۡ جَآءَكُم بَصَآئِرُ مِن رَّبِّكُمۡۖ فَمَنۡ أَبۡصَرَ فَلِنَفۡسِهِۦۖ وَمَنۡ عَمِيَ فَعَلَيۡهَاۚ وَمَآ أَنَا۠ عَلَيۡكُم بِحَفِيظٖ

104. (ሰዎች ሆይ!) «ከጌታችሁ ዘንድ ብርሃኖች በእርግጥ መጡላችሁ:: እውነቱን የተመለከተ ሰው ጥቅሙ ለነፍሱ ብቻ ነው:: የታወረም ሰው ጉዳቱ በራሱ ላይ ብቻ ነው:: እኔ በእናንተ ላይ ጠባቂ አይደለሁም።» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
105 : 6

وَكَذَٰلِكَ نُصَرِّفُ ٱلۡأٓيَٰتِ وَلِيَقُولُواْ دَرَسۡتَ وَلِنُبَيِّنَهُۥ لِقَوۡمٖ يَعۡلَمُونَ

105. ልክ እንደዚሁ ገምግመው «መጽሐፍ አጥንተሃል» እንዲሉና ለሚያውቁ ህዝቦች ቁርኣንን እንድናብራራ አናቅጽን እንገልፃለን። info
التفاسير:

external-link copy
106 : 6

ٱتَّبِعۡ مَآ أُوحِيَ إِلَيۡكَ مِن رَّبِّكَۖ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۖ وَأَعۡرِضۡ عَنِ ٱلۡمُشۡرِكِينَ

106. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን ብቻ ተከተል:: ከእርሱ በስተቀር ትክክለኛ አምላክ የለም:: አጋሪዎችንም ተዋቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
107 : 6

وَلَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ مَآ أَشۡرَكُواْۗ وَمَا جَعَلۡنَٰكَ عَلَيۡهِمۡ حَفِيظٗاۖ وَمَآ أَنتَ عَلَيۡهِم بِوَكِيلٖ

107. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ በፈለገ ኖሮ እነርሱ ጣኦትን ባላጋሩ ነበር:: በእነርሱም ላይ ጠባቂ አላደረግንህም:: አንተም በእነርሱ ላይ ኃላፊ አይደለህም:: info
التفاسير:

external-link copy
108 : 6

وَلَا تَسُبُّواْ ٱلَّذِينَ يَدۡعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ فَيَسُبُّواْ ٱللَّهَ عَدۡوَۢا بِغَيۡرِ عِلۡمٖۗ كَذَٰلِكَ زَيَّنَّا لِكُلِّ أُمَّةٍ عَمَلَهُمۡ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّهِم مَّرۡجِعُهُمۡ فَيُنَبِّئُهُم بِمَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ

108. (ሙስሊሞች ሆይ!) እነዚያንም ከአላህ ሌላ የሚገዟቸውን ጣዖታትን አትስደቡ:: እነርሱም ድንበርን በማለፍ ያለ እውቀት አላህን ይሰድባሉና:: ልክ እንደዚሁ ለህዝቦች ሁሉ ስራቸውን ደግ አስመሰልንላቸው:: ከዚያም መመለሻቸው ወደ ጌታቸው ብቻ ነው:: ይሰሩት የነበሩትንም ሁሉ ይነግራቸዋል:: info
التفاسير:

external-link copy
109 : 6

وَأَقۡسَمُواْ بِٱللَّهِ جَهۡدَ أَيۡمَٰنِهِمۡ لَئِن جَآءَتۡهُمۡ ءَايَةٞ لَّيُؤۡمِنُنَّ بِهَاۚ قُلۡ إِنَّمَا ٱلۡأٓيَٰتُ عِندَ ٱللَّهِۖ وَمَا يُشۡعِرُكُمۡ أَنَّهَآ إِذَا جَآءَتۡ لَا يُؤۡمِنُونَ

109. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ተዐምር ብትመጣላቸው በእርሷ በቁርጥ እንደሚያምኑ ጥብቅ መሀላዎቻቸውን በአላህ ማሉ:: «ተዓምራትም ሁሉ የሚከሰቱት ከአላህ ብቻ ነው። እርሷ በመጣች ጊዜም አለማመናቸውን ወይም ማመናቸውን ምን አሳወቃችሁ?» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
110 : 6

وَنُقَلِّبُ أَفۡـِٔدَتَهُمۡ وَأَبۡصَٰرَهُمۡ كَمَا لَمۡ يُؤۡمِنُواْ بِهِۦٓ أَوَّلَ مَرَّةٖ وَنَذَرُهُمۡ فِي طُغۡيَٰنِهِمۡ يَعۡمَهُونَ

110. በመጀመሪያም ጊዜ በእርሱ እንዳላመኑ ሁሉ ልቦቻቸውንና አይኖቻቸውን እናገላብጣለን:: በጥመታቸዉም ውስጥ የሚዋልሉ ሲሆኑ እንተዋቸዋለን:: info
التفاسير: