పవిత్ర ఖురాన్ యొక్క భావార్థాల అనువాదం - అమ్హారిక్ అనువాదం - ఆఫ్రికా అకాడమీ

పేజీ నెంబరు:close

external-link copy
138 : 6

وَقَالُواْ هَٰذِهِۦٓ أَنۡعَٰمٞ وَحَرۡثٌ حِجۡرٞ لَّا يَطۡعَمُهَآ إِلَّا مَن نَّشَآءُ بِزَعۡمِهِمۡ وَأَنۡعَٰمٌ حُرِّمَتۡ ظُهُورُهَا وَأَنۡعَٰمٞ لَّا يَذۡكُرُونَ ٱسۡمَ ٱللَّهِ عَلَيۡهَا ٱفۡتِرَآءً عَلَيۡهِۚ سَيَجۡزِيهِم بِمَا كَانُواْ يَفۡتَرُونَ

138. በሀሳባቸውም «እነዚህ እርም የሆኑ ለማዳ እንሰሳና አዝመራ ናቸው:: የምንሻለት ሰው እንጂ ሌላ ማንም አይበላቸዉም:: እነዚህ ደግሞ ጀርባዎቻቸው እርም የተደረገ ለማዳ እንሰሳ ናቸው:: አይጫኑም:: እነዚህ ሲታረዱ በእነርሱ ላይ የአላህን ስም የማይጠሩባቸዉም እንሳሳት ናቸው።» አሉ:: በእርሱ ላይ ለመቅጠፍ ነገሩን ወደ አላህ አስጠጉ:: ይቀጥፉት በነበሩት ነገር በእርግጥ ይቀጣቸዋል:: info
التفاسير:

external-link copy
139 : 6

وَقَالُواْ مَا فِي بُطُونِ هَٰذِهِ ٱلۡأَنۡعَٰمِ خَالِصَةٞ لِّذُكُورِنَا وَمُحَرَّمٌ عَلَىٰٓ أَزۡوَٰجِنَاۖ وَإِن يَكُن مَّيۡتَةٗ فَهُمۡ فِيهِ شُرَكَآءُۚ سَيَجۡزِيهِمۡ وَصۡفَهُمۡۚ إِنَّهُۥ حَكِيمٌ عَلِيمٞ

139. «በእነዚህ እንስሳት ሆዶች ውስጥ ያለው ጽንሱ ሁሉ ለወንዶቻችን ብቻ በተለይ የተፈቀደ ነው:: በሚስቶቻችን ላይ ግን እርም የተደረገ ነው:: ሙት ሆኖ ቢወለድ ግን ወንዶቹም ሆነ ሴቶች በእርሱ ላይ ተጋሪዎች ናቸው።» አሉ:: ይህን በመቅጠፋቸው አላህ በእርግጥ ይቀጣቸዋል:: እርሱ ጥበበኛና አዋቂ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
140 : 6

قَدۡ خَسِرَ ٱلَّذِينَ قَتَلُوٓاْ أَوۡلَٰدَهُمۡ سَفَهَۢا بِغَيۡرِ عِلۡمٖ وَحَرَّمُواْ مَا رَزَقَهُمُ ٱللَّهُ ٱفۡتِرَآءً عَلَى ٱللَّهِۚ قَدۡ ضَلُّواْ وَمَا كَانُواْ مُهۡتَدِينَ

140. እነዚያ ያለ እውቀት በሞኝነት ልጆቻቸውን የገደሉና አላህም የሰጣቸውን ሲሳይ በአላህ ላይ በመቅጠፍ በራሳቸው ላይ እርም ያደረጉ ሰዎች ሁሉ በእርግጥ ከሰሩ:: ተሳሳቱም:: ወደ ትክክለኛው መንገድም የተመሩ አልነበሩም:: info
التفاسير:

external-link copy
141 : 6

۞ وَهُوَ ٱلَّذِيٓ أَنشَأَ جَنَّٰتٖ مَّعۡرُوشَٰتٖ وَغَيۡرَ مَعۡرُوشَٰتٖ وَٱلنَّخۡلَ وَٱلزَّرۡعَ مُخۡتَلِفًا أُكُلُهُۥ وَٱلزَّيۡتُونَ وَٱلرُّمَّانَ مُتَشَٰبِهٗا وَغَيۡرَ مُتَشَٰبِهٖۚ كُلُواْ مِن ثَمَرِهِۦٓ إِذَآ أَثۡمَرَ وَءَاتُواْ حَقَّهُۥ يَوۡمَ حَصَادِهِۦۖ وَلَا تُسۡرِفُوٓاْۚ إِنَّهُۥ لَا يُحِبُّ ٱلۡمُسۡرِفِينَ

141. አላህ ያ (በሀረጉ) ዳስ የሚያደርግላቸውንና ዳስ የማያደርግላቸውን አትክልቶች የፈጠረ ነው:: የተምርን ዛፍ፣ አዝመራን፣ ፍሬዎቹ የተለያዩ ሲሆኑ ወይራንና ሩማንንም ቅጠላቸው ተመሳሳይና ጣዕማቸው የማይመሳሰል ሲሆኑ ፈጠረ:: (ሰዎች ሆይ!) ባፈራ ጊዜም ከፍሬው ብሉ:: ባጨዳዉም ቀን ተገቢውን (ዘካ) ለተገቢው ስጡለት:: አታባክኑም:: አላህ አባካኞችን አይወድምና:: info
التفاسير:

external-link copy
142 : 6

وَمِنَ ٱلۡأَنۡعَٰمِ حَمُولَةٗ وَفَرۡشٗاۚ كُلُواْ مِمَّا رَزَقَكُمُ ٱللَّهُ وَلَا تَتَّبِعُواْ خُطُوَٰتِ ٱلشَّيۡطَٰنِۚ إِنَّهُۥ لَكُمۡ عَدُوّٞ مُّبِينٞ

142. ከለማዳ እንሰሳዎችም የሚጫኑትንም የማይጫኑትንም ፈጠረ:: (ሰዎች ሆይ!) አላህ ከሰጣችሁ ሲሳይ ብሉ:: የሰይጣንንም እርምጃዎች አትከተሉ:: እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና:: info
التفاسير: