పవిత్ర ఖురాన్ యొక్క భావార్థాల అనువాదం - అమ్హారిక్ అనువాదం - ఆఫ్రికా అకాడమీ

పేజీ నెంబరు:close

external-link copy
158 : 6

هَلۡ يَنظُرُونَ إِلَّآ أَن تَأۡتِيَهُمُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ أَوۡ يَأۡتِيَ رَبُّكَ أَوۡ يَأۡتِيَ بَعۡضُ ءَايَٰتِ رَبِّكَۗ يَوۡمَ يَأۡتِي بَعۡضُ ءَايَٰتِ رَبِّكَ لَا يَنفَعُ نَفۡسًا إِيمَٰنُهَا لَمۡ تَكُنۡ ءَامَنَتۡ مِن قَبۡلُ أَوۡ كَسَبَتۡ فِيٓ إِيمَٰنِهَا خَيۡرٗاۗ قُلِ ٱنتَظِرُوٓاْ إِنَّا مُنتَظِرُونَ

158. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሓዲያን መላዕክት ልትመጣላቸው ወይንም ጌታህ ሊመጣ ወይም ከጌታህ ምልክቶች ከፊሉ ሊመጣ እንጂ ሌላን ይጠባበቃሉን? ከጌታህ ምልክቶች ከፊሉ የሚመጣበት ቀን ግን ከዚያ በፊት አማኝ ያልነበረች ነፍስ ሁሉ ወይም አምና በእምነቷ በጎ ያልሰራች ነፍስ ሁሉ እምነቷ (ጸጸቷ) አይጠቅማትም:: «ያን ቀን እናንተም ተጠባበቁ እኛም ተጠባባቂዎች ነን።» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
159 : 6

إِنَّ ٱلَّذِينَ فَرَّقُواْ دِينَهُمۡ وَكَانُواْ شِيَعٗا لَّسۡتَ مِنۡهُمۡ فِي شَيۡءٍۚ إِنَّمَآ أَمۡرُهُمۡ إِلَى ٱللَّهِ ثُمَّ يُنَبِّئُهُم بِمَا كَانُواْ يَفۡعَلُونَ

159. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነዚያ ሃይማኖታቸውን ከለያዩና ቡድን ቡድን ከሆኑ (ሰዎች) ጋር አይደለህም:: ነገራቸው ወደ አላህ ብቻ ነው:: ከዚያም ይሰሩት የነበሩትን ሁሉ ይነግራቸዋል:: info
التفاسير:

external-link copy
160 : 6

مَن جَآءَ بِٱلۡحَسَنَةِ فَلَهُۥ عَشۡرُ أَمۡثَالِهَاۖ وَمَن جَآءَ بِٱلسَّيِّئَةِ فَلَا يُجۡزَىٰٓ إِلَّا مِثۡلَهَا وَهُمۡ لَا يُظۡلَمُونَ

160. መልካምን ስራ የሰራ ሁሉ ለእርሱ አስር እጥፍ ምንዳ አሉት:: ክፉ ስራን የሰራ ግን መሰሏን ብቻ እንጂ አይመነዳም:: እነርሱም ቅንጣት አይበደሉም:: info
التفاسير:

external-link copy
161 : 6

قُلۡ إِنَّنِي هَدَىٰنِي رَبِّيٓ إِلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ دِينٗا قِيَمٗا مِّلَّةَ إِبۡرَٰهِيمَ حَنِيفٗاۚ وَمَا كَانَ مِنَ ٱلۡمُشۡرِكِينَ

161. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እኔ ጌታዬ ወደ ቀጥተኛው መንገድ፤ የተስተካከለ ወደሆነው ሃይማኖት የኢብራሂም መንገድ መራኝ:: እሱም ከአጋሪዎች አልነበረም።» በል። info
التفاسير:

external-link copy
162 : 6

قُلۡ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحۡيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

162.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው: «ስግደቴ፤ መገዛቴ (መስዋዕቴ)፣ ሕይወቴ፤ ሞቴ የሚገባው ለዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ ብቻ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
163 : 6

لَا شَرِيكَ لَهُۥۖ وَبِذَٰلِكَ أُمِرۡتُ وَأَنَا۠ أَوَّلُ ٱلۡمُسۡلِمِينَ

163. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ለእርሱ (ለአላህ) አጋር የለዉም:: በዚህ (አላህን ከተጋሪ በማጥራት) ታዘዝኩ:: እኔ የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ።» በል። info
التفاسير:

external-link copy
164 : 6

قُلۡ أَغَيۡرَ ٱللَّهِ أَبۡغِي رَبّٗا وَهُوَ رَبُّ كُلِّ شَيۡءٖۚ وَلَا تَكۡسِبُ كُلُّ نَفۡسٍ إِلَّا عَلَيۡهَاۚ وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٞ وِزۡرَ أُخۡرَىٰۚ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّكُم مَّرۡجِعُكُمۡ فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمۡ فِيهِ تَخۡتَلِفُونَ

164. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ የሁሉ ጌታ ሲሆን ከአላህ በስተቀር ሌላን ጌታ እፈልጋለሁን? ነፍስ ሁሉ በራሷ ላይ እንጂ ክፉን አትሰራም:: ወንጀለኛ ነፍስ ሁሉ የሌላይቱን ነፍስ ኃጢአት አትሸከምም:: ከዚያ መመለሻችሁ ወደ ጌታችሁ ነው:: ከዚያም ትለያዩበት የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
165 : 6

وَهُوَ ٱلَّذِي جَعَلَكُمۡ خَلَٰٓئِفَ ٱلۡأَرۡضِ وَرَفَعَ بَعۡضَكُمۡ فَوۡقَ بَعۡضٖ دَرَجَٰتٖ لِّيَبۡلُوَكُمۡ فِي مَآ ءَاتَىٰكُمۡۗ إِنَّ رَبَّكَ سَرِيعُ ٱلۡعِقَابِ وَإِنَّهُۥ لَغَفُورٞ رَّحِيمُۢ

165. (ሰዎች ሆይ!) እርሱ (አላህ) ያ በምድር ላይ ምትኮች ያደረጋችሁ በሰጣችሁም ጸጋ ሊፈትናችሁ ከፊላችሁን በከፊሉ ላይ በደረጃዎች ከፍ ያደረገ ሃያል ጌታ ነው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ቅጣቱ ፈጣን ነው:: አላህ እጅግ መሀሪና ሩህሩህ ነው:: info
التفاسير: