పవిత్ర ఖురాన్ యొక్క భావార్థాల అనువాదం - అమ్హారిక్ అనువాదం - ఆఫ్రికా అకాడమీ

పేజీ నెంబరు:close

external-link copy
9 : 6

وَلَوۡ جَعَلۡنَٰهُ مَلَكٗا لَّجَعَلۡنَٰهُ رَجُلٗا وَلَلَبَسۡنَا عَلَيۡهِم مَّا يَلۡبِسُونَ

9. መልዕክተኛውን ከመላዕክት መካከል ባደረግነው ኖሮ ወንድ ሰው አድርገን በመላክ በእነርሱ ላይ የሚያመሳስሉትን ነገር ባመሳሰልንባቸው ነበር። info
التفاسير:

external-link copy
10 : 6

وَلَقَدِ ٱسۡتُهۡزِئَ بِرُسُلٖ مِّن قَبۡلِكَ فَحَاقَ بِٱلَّذِينَ سَخِرُواْ مِنۡهُم مَّا كَانُواْ بِهِۦ يَسۡتَهۡزِءُونَ

10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት በነበሩ መልዕክተኞችም ላይ ተላግጧል:: እናም በእነዚያ ባላገጡት ላይ ያላገጡበት ውጤት በእነርሱ ላይ ተፈጽሟል:: info
التفاسير:

external-link copy
11 : 6

قُلۡ سِيرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ ثُمَّ ٱنظُرُواْ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلۡمُكَذِّبِينَ

11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ከሓዲያንን) «በምድር ላይ ሂዱና የእነዚያን የአስተባባዮችን መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከቱ።» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
12 : 6

قُل لِّمَن مَّا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ قُل لِّلَّهِۚ كَتَبَ عَلَىٰ نَفۡسِهِ ٱلرَّحۡمَةَۚ لَيَجۡمَعَنَّكُمۡ إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ لَا رَيۡبَ فِيهِۚ ٱلَّذِينَ خَسِرُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ فَهُمۡ لَا يُؤۡمِنُونَ

12. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው: «በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የማን ነው?» በላቸውም: «የአላህ ብቻ ነው። አላህ በራሱ ላይ እዝነትን ፃፈ:: በዚያ ጥርጥር በሌለበት በትንሳኤ ቀን ይሰበስባችኋል:: እነዚያ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩ ማለት እነርሱው ናቸው። እናም አያምኑም። info
التفاسير:

external-link copy
13 : 6

۞ وَلَهُۥ مَا سَكَنَ فِي ٱلَّيۡلِ وَٱلنَّهَارِۚ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡعَلِيمُ

13. «በሌሊትም ሆነ በቀን ጸጥ ያለው ሁሉ የእርሱው ነው:: እርሱም ሰሚውና አዋቂው ነው።» info
التفاسير:

external-link copy
14 : 6

قُلۡ أَغَيۡرَ ٱللَّهِ أَتَّخِذُ وَلِيّٗا فَاطِرِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَهُوَ يُطۡعِمُ وَلَا يُطۡعَمُۗ قُلۡ إِنِّيٓ أُمِرۡتُ أَنۡ أَكُونَ أَوَّلَ مَنۡ أَسۡلَمَۖ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡمُشۡرِكِينَ

14. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ከሆነው አላህ እርሱ ፍጡርን የሚመግብና ለራሱ የማይመገብ አምላክ ሲሆን ሌላን አምላክ እይዛለሁን?» በላቸው። «እኔ መጀመሪያ ትዕዛዝን ከተቀበለ ሰው እንድሆን ታዘዝኩ:: ‹ከአጋሪዎችም ፈጽሞ አትሁን።› ተብያለሁ።» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
15 : 6

قُلۡ إِنِّيٓ أَخَافُ إِنۡ عَصَيۡتُ رَبِّي عَذَابَ يَوۡمٍ عَظِيمٖ

15. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እኔ በጌታዬ ላይ ባምጽ የዚያን የታላቁን ቀን ቅጣት እፈራለሁ።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
16 : 6

مَّن يُصۡرَفۡ عَنۡهُ يَوۡمَئِذٖ فَقَدۡ رَحِمَهُۥۚ وَذَٰلِكَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡمُبِينُ

16. በዚያ ቀን ከእርሱ ላይ ቅጣት የሚመለስለት ሰው ሁሉ በእርግጥ አላህ አዘነለት:: ይህም ግልጽ ስኬት ነው። info
التفاسير:

external-link copy
17 : 6

وَإِن يَمۡسَسۡكَ ٱللَّهُ بِضُرّٖ فَلَا كَاشِفَ لَهُۥٓ إِلَّا هُوَۖ وَإِن يَمۡسَسۡكَ بِخَيۡرٖ فَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ

17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ችግር ቢያደርስብህ ከእርሱ በስተቀር ሌላ ማንም አስወጋጅ የለም:: በጎ ነገርን ቢሰጥህም እርሱ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
18 : 6

وَهُوَ ٱلۡقَاهِرُ فَوۡقَ عِبَادِهِۦۚ وَهُوَ ٱلۡحَكِيمُ ٱلۡخَبِيرُ

18. እርሱ ከባሮቹ በላይ ሲሆን ሁሉን አሸናፊ ነው:: እርሱ ጥበበኛውና ውስጠ አዋቂው ነው። info
التفاسير: