పవిత్ర ఖురాన్ యొక్క భావార్థాల అనువాదం - అమ్హారిక్ అనువాదం - ఆఫ్రికా అకాడమీ

పేజీ నెంబరు:close

external-link copy
28 : 6

بَلۡ بَدَا لَهُم مَّا كَانُواْ يُخۡفُونَ مِن قَبۡلُۖ وَلَوۡ رُدُّواْ لَعَادُواْ لِمَا نُهُواْ عَنۡهُ وَإِنَّهُمۡ لَكَٰذِبُونَ

28. ይልቁንስ ከዚህ በፊት ይደብቁት የነበሩት ነገር ሁሉ ለእነርሱ ተገለጸ:: ወደ ምድረ ዓለም በተመለሱም ኖሮ ወደ ተከለከሉት ነገር በተመለሱ ነበር:: እነርሱ ሐሰተኞች ናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
29 : 6

وَقَالُوٓاْ إِنۡ هِيَ إِلَّا حَيَاتُنَا ٱلدُّنۡيَا وَمَا نَحۡنُ بِمَبۡعُوثِينَ

29. «ሕይወት ማለት ቅርቢቱ ሕይወታችን እንጂ ሌላ አይደለችም:: እኛም ፈጽሞ ተቀስቃሾች አይደለንም።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
30 : 6

وَلَوۡ تَرَىٰٓ إِذۡ وُقِفُواْ عَلَىٰ رَبِّهِمۡۚ قَالَ أَلَيۡسَ هَٰذَا بِٱلۡحَقِّۚ قَالُواْ بَلَىٰ وَرَبِّنَاۚ قَالَ فَذُوقُواْ ٱلۡعَذَابَ بِمَا كُنتُمۡ تَكۡفُرُونَ

30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በጌታቸው ዘንድ ለምርመራ እንዲቆሙ በተደረጉ ጊዜ ብታይ ኖሮ (አስደንጋጭን ነገር ባየህ ነበር::) «ይህ እውነት አይደለምን?» ይላቸዋል:: እነርሱም «በጌታችን ይሁንብን እውነት ነው።» ይላሉ:: «እናም ትክዱት በነበራችሁት ምክንያት ቅጣቱን ቅመሱ።» ይላቸዋል:: info
التفاسير:

external-link copy
31 : 6

قَدۡ خَسِرَ ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِلِقَآءِ ٱللَّهِۖ حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءَتۡهُمُ ٱلسَّاعَةُ بَغۡتَةٗ قَالُواْ يَٰحَسۡرَتَنَا عَلَىٰ مَا فَرَّطۡنَا فِيهَا وَهُمۡ يَحۡمِلُونَ أَوۡزَارَهُمۡ عَلَىٰ ظُهُورِهِمۡۚ أَلَا سَآءَ مَا يَزِرُونَ

31. እነዚያ ከአላህ ጋር መገናኘትን ያስተባበሉ ሁሉ በእርግጥ ከሰሩ:: ስዓቲቱም በድንገት በመጣችባቸው ጊዜ እነርሱ ኃጢአቶቻቸውን በጀርባዎቻቸው ላይ የሚሸከሙ ሲሆኑ «በምድረ ዓለም ባጓደልነው ነገር ላይ ዋ ጥፋታችን!» ይላሉ። አዋጅ ያ የሚሸከሙት ነገር ምንኛ ከፋ! info
التفاسير:

external-link copy
32 : 6

وَمَا ٱلۡحَيَوٰةُ ٱلدُّنۡيَآ إِلَّا لَعِبٞ وَلَهۡوٞۖ وَلَلدَّارُ ٱلۡأٓخِرَةُ خَيۡرٞ لِّلَّذِينَ يَتَّقُونَۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ

32. የቅርቢቱ ሕይወት ማለት ጨዋታና ላግጣ እንጂ ሌላ አይደለችም። የመጨረሻይቱ አገር (ገነት) ግን ለእነዚያ ለሚጠነቀቁት ሰዎች ሁሉ በጣም በላጭ ናት። አታውቁምን? (አትገነዘቡምን)? info
التفاسير:

external-link copy
33 : 6

قَدۡ نَعۡلَمُ إِنَّهُۥ لَيَحۡزُنُكَ ٱلَّذِي يَقُولُونَۖ فَإِنَّهُمۡ لَا يُكَذِّبُونَكَ وَلَٰكِنَّ ٱلظَّٰلِمِينَ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ يَجۡحَدُونَ

33. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያ የሚሉህ ነገር እንደሚያሳዝንህ በእርግጥ እናውቃለን:: እነርሱ በእርግጥ አያስተባብሉህም:: ግን በዳዮች በአላህ አናቅጽ ይክዳሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
34 : 6

وَلَقَدۡ كُذِّبَتۡ رُسُلٞ مِّن قَبۡلِكَ فَصَبَرُواْ عَلَىٰ مَا كُذِّبُواْ وَأُوذُواْ حَتَّىٰٓ أَتَىٰهُمۡ نَصۡرُنَاۚ وَلَا مُبَدِّلَ لِكَلِمَٰتِ ٱللَّهِۚ وَلَقَدۡ جَآءَكَ مِن نَّبَإِيْ ٱلۡمُرۡسَلِينَ

34. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከበፊትህ የነበሩት መልዕክተኞች ተስተባብለዋል:: በተስተባበሉበትም ነገርና በተሰቃዩት ላይ እርዳታችን እስከመጣላቸው ድረስ ታገሱ:: የአላህን ቃላት የሚለዉጥ የለም:: ከመልዕክተኞቹም ወሬ (የምትረጋጋበት) በእርግጥ መጣልህ:: info
التفاسير:

external-link copy
35 : 6

وَإِن كَانَ كَبُرَ عَلَيۡكَ إِعۡرَاضُهُمۡ فَإِنِ ٱسۡتَطَعۡتَ أَن تَبۡتَغِيَ نَفَقٗا فِي ٱلۡأَرۡضِ أَوۡ سُلَّمٗا فِي ٱلسَّمَآءِ فَتَأۡتِيَهُم بِـَٔايَةٖۚ وَلَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ لَجَمَعَهُمۡ عَلَى ٱلۡهُدَىٰۚ فَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡجَٰهِلِينَ

35. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢስላምን መተዋቸው ባንተ ላይ ከባድ ቢሆንብህም በምድር ውስጥ ቀዳዳን ወይም በሰማይ ውስጥ መሰላልን ልትፈልግና ተዓምር ልታመጣላቸው ከቻልክ ሞክር:: አላህ በፈለገ ኖሮ ሁሉንም በቅኑ መንገድ ላይ በሰበሰባቸው ነበር:: ስለዚህ ከተሳሳቱት ሰዎች በፍጹም አትሁን:: info
التفاسير: