ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
62 : 18

فَلَمَّا جَاوَزَا قَالَ لِفَتَىٰهُ ءَاتِنَا غَدَآءَنَا لَقَدۡ لَقِينَا مِن سَفَرِنَا هَٰذَا نَصَبٗا

62. ባለፉም ጊዜ ለወጣቱ «ምሳችንን ስጠን ከዚህ ጉዟችን በእርግጥ ድካምን አግኝተናልና።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
63 : 18

قَالَ أَرَءَيۡتَ إِذۡ أَوَيۡنَآ إِلَى ٱلصَّخۡرَةِ فَإِنِّي نَسِيتُ ٱلۡحُوتَ وَمَآ أَنسَىٰنِيهُ إِلَّا ٱلشَّيۡطَٰنُ أَنۡ أَذۡكُرَهُۥۚ وَٱتَّخَذَ سَبِيلَهُۥ فِي ٱلۡبَحۡرِ عَجَبٗا

63. «አየህን? ወደ ቋጥኟ በተጠጋን ጊዜ እኔ ዐሳውን ረሳሁ፤ ሰይጣን እንጂ ሌላ አላስረሳኝም፤ በባህሩም ውስጥ መንገዱን አስደናቂ መንገድ አድርጎ ያዘ።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
64 : 18

قَالَ ذَٰلِكَ مَا كُنَّا نَبۡغِۚ فَٱرۡتَدَّا عَلَىٰٓ ءَاثَارِهِمَا قَصَصٗا

64. ሙሳም «ይህ እኮ እንፈልገው የነበረው ነው።» አለው። ከዚያ በኮቴዎቻቸው (ዱካቸው) ላይ እየተከተሉ ተመለሱ። info
التفاسير:

external-link copy
65 : 18

فَوَجَدَا عَبۡدٗا مِّنۡ عِبَادِنَآ ءَاتَيۡنَٰهُ رَحۡمَةٗ مِّنۡ عِندِنَا وَعَلَّمۡنَٰهُ مِن لَّدُنَّا عِلۡمٗا

65.ከባሮቻችንም ከእኛ ዘንድ ችሮታን የሰጠነውን ከኛም ዘንድ እውቀትን ያስተማርነውን አንድን ባሪያችንን አገኙ:: info
التفاسير:

external-link copy
66 : 18

قَالَ لَهُۥ مُوسَىٰ هَلۡ أَتَّبِعُكَ عَلَىٰٓ أَن تُعَلِّمَنِ مِمَّا عُلِّمۡتَ رُشۡدٗا

66. ሙሳ «ለእርሱ ከተማርከው ነገር ቀጥተኛን እውቀት ታስተምረኝ ዘንድ ልከተልህ?» አለው። info
التفاسير:

external-link copy
67 : 18

قَالَ إِنَّكَ لَن تَسۡتَطِيعَ مَعِيَ صَبۡرٗا

67. ባሪያዉም አለ: «አንተ ከእኔ ጋር መታገስን በጭራሽ አትችልም። info
التفاسير:

external-link copy
68 : 18

وَكَيۡفَ تَصۡبِرُ عَلَىٰ مَا لَمۡ تُحِطۡ بِهِۦ خُبۡرٗا

68. «በእውቀት ባልደረስክበት ነገር ላይስ እንዴት ትታገሳለህ?» info
التفاسير:

external-link copy
69 : 18

قَالَ سَتَجِدُنِيٓ إِن شَآءَ ٱللَّهُ صَابِرٗا وَلَآ أَعۡصِي لَكَ أَمۡرٗا

69. ሙሳም «አላህ የፈለገ እንደሆነ ታጋሽና ላንተ ትዕዛዝን የማልጥስ ሆኜ ታገኘኛለህ።» አለው። info
التفاسير:

external-link copy
70 : 18

قَالَ فَإِنِ ٱتَّبَعۡتَنِي فَلَا تَسۡـَٔلۡنِي عَن شَيۡءٍ حَتَّىٰٓ أُحۡدِثَ لَكَ مِنۡهُ ذِكۡرٗا

70. «ብትከተለኝም ላንተ ከእርሱ ማውሳትን እስከምጀምርልህ ድረስ ከምንም ነገር እንዳትጠይቀኝ።» አለው። info
التفاسير:

external-link copy
71 : 18

فَٱنطَلَقَا حَتَّىٰٓ إِذَا رَكِبَا فِي ٱلسَّفِينَةِ خَرَقَهَاۖ قَالَ أَخَرَقۡتَهَا لِتُغۡرِقَ أَهۡلَهَا لَقَدۡ جِئۡتَ شَيۡـًٔا إِمۡرٗا

71. ሄዱም:: በመርከቢቱም በተሳፈሩ ጊዜ መርከቢቱን ቀደዳት። «ባለቤቶችዋን ልታሰምጥ ቀደድካትን? ትልቅን ጥፋት በእርግጥ ሠራህ።» አለው። info
التفاسير:

external-link copy
72 : 18

قَالَ أَلَمۡ أَقُلۡ إِنَّكَ لَن تَسۡتَطِيعَ مَعِيَ صَبۡرٗا

72. «አንተ ከእኔ ጋር ትዕግስትን ፈጽሞ አትችልም አላልኩምን?» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
73 : 18

قَالَ لَا تُؤَاخِذۡنِي بِمَا نَسِيتُ وَلَا تُرۡهِقۡنِي مِنۡ أَمۡرِي عُسۡرٗا

73. «በረሳሁት ነገር አትያዝብኝ:: ከነገሬም ችግርን አታሸክመኝ።» አለው። info
التفاسير:

external-link copy
74 : 18

فَٱنطَلَقَا حَتَّىٰٓ إِذَا لَقِيَا غُلَٰمٗا فَقَتَلَهُۥ قَالَ أَقَتَلۡتَ نَفۡسٗا زَكِيَّةَۢ بِغَيۡرِ نَفۡسٖ لَّقَدۡ جِئۡتَ شَيۡـٔٗا نُّكۡرٗا

74. ወርደው ተጓዙም ወጣቱንም ልጅ ባገኘውና በገደለው ጊዜ «ነፍስን ያልገደለችን ንጹህን ነፍስ ገደልክን? በእርግጥ መጥፎን ነገር ሰራህ።» አለው። info
التفاسير: