ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
35 : 18

وَدَخَلَ جَنَّتَهُۥ وَهُوَ ظَالِمٞ لِّنَفۡسِهِۦ قَالَ مَآ أَظُنُّ أَن تَبِيدَ هَٰذِهِۦٓ أَبَدٗا

35. እርሱም ነፍሱንም በዳይ ሆኖ ወደ አትክልቱ ገባ። (እንዲህም) አለ: «ይህች አትክልት መቸም ትጠፋለች ብዬ አልጠረጥርም። info
التفاسير:

external-link copy
36 : 18

وَمَآ أَظُنُّ ٱلسَّاعَةَ قَآئِمَةٗ وَلَئِن رُّدِدتُّ إِلَىٰ رَبِّي لَأَجِدَنَّ خَيۡرٗا مِّنۡهَا مُنقَلَبٗا

36. «ሰዓቲቱንም ትከሰታለች ብዬ አልጠረጥርም፤ እንደምትለው ወደ ጌታዬም ብመለስ ከእርሷ የበለጠን መመለሻ በእርግጥ አገኛለሁ።» አለው። info
التفاسير:

external-link copy
37 : 18

قَالَ لَهُۥ صَاحِبُهُۥ وَهُوَ يُحَاوِرُهُۥٓ أَكَفَرۡتَ بِٱلَّذِي خَلَقَكَ مِن تُرَابٖ ثُمَّ مِن نُّطۡفَةٖ ثُمَّ سَوَّىٰكَ رَجُلٗا

37. አማኙ ጓደኛውም ለእርሱ የሚመላለሰው ሲሆን (እንዲህ) አለው: «በዚያ ከአፈር ከዚያም ከፍትወት ጠብታ በፈጠረህ ከዚያም ሰው ባደረገህ ሃያል አምላክ ካድክን? info
التفاسير:

external-link copy
38 : 18

لَّٰكِنَّا۠ هُوَ ٱللَّهُ رَبِّي وَلَآ أُشۡرِكُ بِرَبِّيٓ أَحَدٗا

38. «እኔ ግን አላህ ጌታዬ ነው እላለሁ። በጌታዬም አንድንም አላጋራም። info
التفاسير:

external-link copy
39 : 18

وَلَوۡلَآ إِذۡ دَخَلۡتَ جَنَّتَكَ قُلۡتَ مَا شَآءَ ٱللَّهُ لَا قُوَّةَ إِلَّا بِٱللَّهِۚ إِن تَرَنِ أَنَا۠ أَقَلَّ مِنكَ مَالٗا وَوَلَدٗا

39. «እኔን በገንዘብም ሆነ በልጅ ካንተ በጣም ያነስኩ ሆኜ ብታየኝም ወደ አትክልትህ በገባህ ጊዜ ‹አላህ የሻው ሆኗል። በአላህ ቢሆን እንጂ ብልሃትም የለም› አትልም ኖሯልን? info
التفاسير:

external-link copy
40 : 18

فَعَسَىٰ رَبِّيٓ أَن يُؤۡتِيَنِ خَيۡرٗا مِّن جَنَّتِكَ وَيُرۡسِلَ عَلَيۡهَا حُسۡبَانٗا مِّنَ ٱلسَّمَآءِ فَتُصۡبِحَ صَعِيدٗا زَلَقًا

40. «ጌታዬ ከአትክልትህ የበለጠን ሊሰጠኝ በአትክልትህ ላይ ደግሞ በሰማይ መብረቆችን ሊልክባትና የምታንዳልጥ ምልጥ ምድር ልትሆንም ይቻላል። info
التفاسير:

external-link copy
41 : 18

أَوۡ يُصۡبِحَ مَآؤُهَا غَوۡرٗا فَلَن تَسۡتَطِيعَ لَهُۥ طَلَبٗا

41. «ወይም ውሀው ሰራጊ ሊሆንብህ ይችላል። ያን ጊዜ እርሱን መፈለጉን ፈጽሞ አትችልም።» አለው። info
التفاسير:

external-link copy
42 : 18

وَأُحِيطَ بِثَمَرِهِۦ فَأَصۡبَحَ يُقَلِّبُ كَفَّيۡهِ عَلَىٰ مَآ أَنفَقَ فِيهَا وَهِيَ خَاوِيَةٌ عَلَىٰ عُرُوشِهَا وَيَقُولُ يَٰلَيۡتَنِي لَمۡ أُشۡرِكۡ بِرَبِّيٓ أَحَدٗا

42. ሀብቱም ተጠፋ:: እርሷ በዳሶችዋ ላይ የወደቀች ሆና በእርሷ ባወጣው ገንዘብ ላይ የተጸጸተ መዳፎቹን የሚያገላብጥና «ወይ ጸጸቴ! በጌታዬ አንድንም ባላጋራሁ።» የሚል ሆነ። info
التفاسير:

external-link copy
43 : 18

وَلَمۡ تَكُن لَّهُۥ فِئَةٞ يَنصُرُونَهُۥ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَمَا كَانَ مُنتَصِرًا

43.እርሱም ከአላህ ሌላ የሚረዱት ቡድኖች አልነበሩትም:: ተረጂም አልነበረም:: info
التفاسير:

external-link copy
44 : 18

هُنَالِكَ ٱلۡوَلَٰيَةُ لِلَّهِ ٱلۡحَقِّۚ هُوَ خَيۡرٞ ثَوَابٗا وَخَيۡرٌ عُقۡبٗا

44.እዚያ ዘንድ በትንሳኤ ቀን ስልጣኑ እውነተኛ ለሆነው ለአላህ ብቻ ነው:: እርሱ በመመንዳት የበለጠ ፍጻሜንም በማሳመር የበለጠ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
45 : 18

وَٱضۡرِبۡ لَهُم مَّثَلَ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا كَمَآءٍ أَنزَلۡنَٰهُ مِنَ ٱلسَّمَآءِ فَٱخۡتَلَطَ بِهِۦ نَبَاتُ ٱلۡأَرۡضِ فَأَصۡبَحَ هَشِيمٗا تَذۡرُوهُ ٱلرِّيَٰحُۗ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ مُّقۡتَدِرًا

45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነርሱም የቅርቢቱን ህይወት ምሳሌ አውሳላቸው:: እርሷ ከሰማይ እንዳወረድነው ውሃ በእርሱም የምድር ቡቃያ እንደተቀላቀለበት፤ ከተዋበ በኋላም ደርቆ ንፋሶች የሚያበኑት ደቃቅ እንደሆነ ብጤ ናት:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው:: info
التفاسير: