ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
98 : 18

قَالَ هَٰذَا رَحۡمَةٞ مِّن رَّبِّيۖ فَإِذَا جَآءَ وَعۡدُ رَبِّي جَعَلَهُۥ دَكَّآءَۖ وَكَانَ وَعۡدُ رَبِّي حَقّٗا

98. «ይህ ግድብ ከጌታዬ ችሮታዎች ነው:: የጌታዬ ቀጠሮ በመጣ ጊዜ እንኩትኩት ያደርገዋል:: የጌታዬም ቀጠሮ የተረጋገጠ ነው።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
99 : 18

۞ وَتَرَكۡنَا بَعۡضَهُمۡ يَوۡمَئِذٖ يَمُوجُ فِي بَعۡضٖۖ وَنُفِخَ فِي ٱلصُّورِ فَجَمَعۡنَٰهُمۡ جَمۡعٗا

99. በዚያን ቀን ከፊላቸውን በከፊሉ የሚቀላቀሉ አድርገን እንተዋቸዋለን:: በቀንዱም ይነፋል:: መሰብሰብንም እንሰበስባቸዋለን:: info
التفاسير:

external-link copy
100 : 18

وَعَرَضۡنَا جَهَنَّمَ يَوۡمَئِذٖ لِّلۡكَٰفِرِينَ عَرۡضًا

100. ገሀነምንም በዚያ ቀን ለከሓዲያን በጣም ማቅረብን እናቀርባታለን:: info
التفاسير:

external-link copy
101 : 18

ٱلَّذِينَ كَانَتۡ أَعۡيُنُهُمۡ فِي غِطَآءٍ عَن ذِكۡرِي وَكَانُواْ لَا يَسۡتَطِيعُونَ سَمۡعًا

101.ለእነዚያ አይኖቻቸው ከግሳጼዬ በሽፋን ውስጥ ለነበሩትና መስማትንም የማይችሉ ለነበሩት እናቀርባታለን:: info
التفاسير:

external-link copy
102 : 18

أَفَحَسِبَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ أَن يَتَّخِذُواْ عِبَادِي مِن دُونِيٓ أَوۡلِيَآءَۚ إِنَّآ أَعۡتَدۡنَا جَهَنَّمَ لِلۡكَٰفِرِينَ نُزُلٗا

102. እነዚያ በእኔ የካዱት ባሮቼን ከኔ ሌላ አማልክት አድርገው መያዛቸውን የማያስቆጣኝ አድርገው አሰቡን? እኛ ገሀነምን ለከሓዲያን መስተንግዶ አዘጋጅተናል:: info
التفاسير:

external-link copy
103 : 18

قُلۡ هَلۡ نُنَبِّئُكُم بِٱلۡأَخۡسَرِينَ أَعۡمَٰلًا

103. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (እንዲህ) በላቸው: «በሥራዎች በጣም ከሳሪዎቹን እንንገራችሁን? info
التفاسير:

external-link copy
104 : 18

ٱلَّذِينَ ضَلَّ سَعۡيُهُمۡ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا وَهُمۡ يَحۡسَبُونَ أَنَّهُمۡ يُحۡسِنُونَ صُنۡعًا

104. «እነዚያ እነርሱ ሥራን የሚያሳምሩ የሚመስላቸው ሲሆኑ በቅርቢቱ ህይወት ሥራቸው የጠፋባቸው ናቸው።» info
التفاسير:

external-link copy
105 : 18

أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِمۡ وَلِقَآئِهِۦ فَحَبِطَتۡ أَعۡمَٰلُهُمۡ فَلَا نُقِيمُ لَهُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ وَزۡنٗا

105. እነዚያ እነርሱ በጌታቸው ተዓምራትና መገናኘት የካዱ ናቸው። ሥራዎቻቸዉም ተበላሸ:: ለእነርሱም በትንሳኤ ቀን ሚዛንን አናቆምላቸዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
106 : 18

ذَٰلِكَ جَزَآؤُهُمۡ جَهَنَّمُ بِمَا كَفَرُواْ وَٱتَّخَذُوٓاْ ءَايَٰتِي وَرُسُلِي هُزُوًا

106. ነገሩ ይህ ነው:: በክህደታቸው፣ አንቀፆቼንና መልዕክተኞቼንም መሳለቂያ አድርገው በመያዛቸው ፍዳቸው ገሀነም ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
107 : 18

إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ كَانَتۡ لَهُمۡ جَنَّٰتُ ٱلۡفِرۡدَوۡسِ نُزُلًا

107. እነዚያ በአላህ ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ ፊርደውስ የተባለው የገነት ክፍል ለእነርሱ መስፈሪያ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
108 : 18

خَٰلِدِينَ فِيهَا لَا يَبۡغُونَ عَنۡهَا حِوَلٗا

108. በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች፤ ከእርሷም መዛወርን የማይፈልጉ ሲሆኑ መስፈሪያቸው ነው። info
التفاسير:

external-link copy
109 : 18

قُل لَّوۡ كَانَ ٱلۡبَحۡرُ مِدَادٗا لِّكَلِمَٰتِ رَبِّي لَنَفِدَ ٱلۡبَحۡرُ قَبۡلَ أَن تَنفَدَ كَلِمَٰتُ رَبِّي وَلَوۡ جِئۡنَا بِمِثۡلِهِۦ مَدَدٗا

109. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ባህሩ ለጌታዬ ቃላት መጻፊያ ቀለሞችን ቢሆን ኖሮ ብጤውን ጭማሪ ብናመጣም እንኳ የጌታዬ ቃላት ከማለቋ በፊት ባህሩ ባለቀ ነበር።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
110 : 18

قُلۡ إِنَّمَآ أَنَا۠ بَشَرٞ مِّثۡلُكُمۡ يُوحَىٰٓ إِلَيَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمۡ إِلَٰهٞ وَٰحِدٞۖ فَمَن كَانَ يَرۡجُواْ لِقَآءَ رَبِّهِۦ فَلۡيَعۡمَلۡ عَمَلٗا صَٰلِحٗا وَلَا يُشۡرِكۡ بِعِبَادَةِ رَبِّهِۦٓ أَحَدَۢا

110. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እኔ መሰላችሁ ሰው ነኝ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው የሚል መልዕክት ወደ እኔ የሚወረድልኝ:: እናም ከጌታው ጋር መገናኘት የሚፈልግ ሰው ሁሉ መልካም ሥራን ይሥራ:: በጌታዉም መገዛት ላይ አንድንም አያጋራ።» በላቸው። info
التفاسير: