ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
54 : 18

وَلَقَدۡ صَرَّفۡنَا فِي هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانِ لِلنَّاسِ مِن كُلِّ مَثَلٖۚ وَكَانَ ٱلۡإِنسَٰنُ أَكۡثَرَ شَيۡءٖ جَدَلٗا

54. በዚህም ቁርኣን ውስጥ ከየምሳሌው ሁሉ ለሰዎች መላልሰን ገለጽን፤ ሰዉም ከነገሩ ሁሉ ይበልጥ ክርክረ ብዙ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
55 : 18

وَمَا مَنَعَ ٱلنَّاسَ أَن يُؤۡمِنُوٓاْ إِذۡ جَآءَهُمُ ٱلۡهُدَىٰ وَيَسۡتَغۡفِرُواْ رَبَّهُمۡ إِلَّآ أَن تَأۡتِيَهُمۡ سُنَّةُ ٱلۡأَوَّلِينَ أَوۡ يَأۡتِيَهُمُ ٱلۡعَذَابُ قُبُلٗا

55.ሰዎችንም መመሪያ በመጣላችሁ ጊዜ ከማመንና ጌታቸውንም ምህረትን ከመለመን የከለከላቸው የመጀመሪያዎቹ ህዝቦች ልማድ መጥፋት ልትመጣባቸው ወይም ቅጣቱ በየዓይነቱ ሊመጣባቸው መጠባበቅ ብቻ እንጂ ሌላ አይደለም:: info
التفاسير:

external-link copy
56 : 18

وَمَا نُرۡسِلُ ٱلۡمُرۡسَلِينَ إِلَّا مُبَشِّرِينَ وَمُنذِرِينَۚ وَيُجَٰدِلُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِٱلۡبَٰطِلِ لِيُدۡحِضُواْ بِهِ ٱلۡحَقَّۖ وَٱتَّخَذُوٓاْ ءَايَٰتِي وَمَآ أُنذِرُواْ هُزُوٗا

56. መልዕክተኞችንም አብሳሪዎችና አስፈራሪዎች ሆነው እንጂ አንልክም:: እነዚያ የካዱትም በውሸት እውነቱን በእሱ ሊያበላሹ ይከራከራሉ:: አንቀፆቼንና በእርሱ የተስፈራሩበትንም ነገር ማላገጫ አድርገው ያዙ:: info
التفاسير:

external-link copy
57 : 18

وَمَنۡ أَظۡلَمُ مِمَّن ذُكِّرَ بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِۦ فَأَعۡرَضَ عَنۡهَا وَنَسِيَ مَا قَدَّمَتۡ يَدَاهُۚ إِنَّا جَعَلۡنَا عَلَىٰ قُلُوبِهِمۡ أَكِنَّةً أَن يَفۡقَهُوهُ وَفِيٓ ءَاذَانِهِمۡ وَقۡرٗاۖ وَإِن تَدۡعُهُمۡ إِلَى ٱلۡهُدَىٰ فَلَن يَهۡتَدُوٓاْ إِذًا أَبَدٗا

57.በጌታዉም አናቅጽ ከተገሰጸና ከእርሷም ከዞረ፤ ሁለት እጆቹም ያስቀደሙትን ነገር ከረሳቸዉም ይበልጥ በዳይ ማን ነው? እኛ በልቦቻቸው ላይ እንዳያውቁት ሽፋኖችን፤ በጆሮዎቻቸዉም ውስጥ ድንቁርናን አደረግን። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ መመራትም ብትጠራቸው ያን ጊዜ ፈጽሞ አይመሩም:: info
التفاسير:

external-link copy
58 : 18

وَرَبُّكَ ٱلۡغَفُورُ ذُو ٱلرَّحۡمَةِۖ لَوۡ يُؤَاخِذُهُم بِمَا كَسَبُواْ لَعَجَّلَ لَهُمُ ٱلۡعَذَابَۚ بَل لَّهُم مَّوۡعِدٞ لَّن يَجِدُواْ مِن دُونِهِۦ مَوۡئِلٗا

58. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም በጣም መሀሪው የእዝነት ባለቤት ነው:: በሠሩት ሥራ ቢይዛቸው ኖሮ ቅጣቱን ለእነርሱ ባስቸኮለባቸው ነበር:: ግን ለእነርሱ ከእርሱ ሌላ መጠጊያን ፈጽሞ የማያገኙበት ቀጠሮ አላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
59 : 18

وَتِلۡكَ ٱلۡقُرَىٰٓ أَهۡلَكۡنَٰهُمۡ لَمَّا ظَلَمُواْ وَجَعَلۡنَا لِمَهۡلِكِهِم مَّوۡعِدٗا

59.እነዚህ ከተሞችም በበደሉ ጊዜ አጠፋናቸው፤ ለመጥፊያቸዉም የተወሰነ ጊዜ አደረግን:: info
التفاسير:

external-link copy
60 : 18

وَإِذۡ قَالَ مُوسَىٰ لِفَتَىٰهُ لَآ أَبۡرَحُ حَتَّىٰٓ أَبۡلُغَ مَجۡمَعَ ٱلۡبَحۡرَيۡنِ أَوۡ أَمۡضِيَ حُقُبٗا

60. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሙሳ ለወጣቱ «የሁለቱን ባህሮች መገናኛ እስከምደርስ ወይም ብዙን ጊዜ እስከምሄድ ድረስ ከመጓዝ አልወገድም።» ያለውን (አስታውስ)። info
التفاسير:

external-link copy
61 : 18

فَلَمَّا بَلَغَا مَجۡمَعَ بَيۡنِهِمَا نَسِيَا حُوتَهُمَا فَٱتَّخَذَ سَبِيلَهُۥ فِي ٱلۡبَحۡرِ سَرَبٗا

61. የሁለቱን ባህር መገናኛ በደረሱም ጊዜ ዓሳቸውን ረሱ፤ ዓሳውም መንገዱን በባህር ውስጥ ቀዳዳ አድርጎ ያዘ። info
التفاسير: