ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
16 : 18

وَإِذِ ٱعۡتَزَلۡتُمُوهُمۡ وَمَا يَعۡبُدُونَ إِلَّا ٱللَّهَ فَأۡوُۥٓاْ إِلَى ٱلۡكَهۡفِ يَنشُرۡ لَكُمۡ رَبُّكُم مِّن رَّحۡمَتِهِۦ وَيُهَيِّئۡ لَكُم مِّنۡ أَمۡرِكُم مِّرۡفَقٗا

16. «እነርሱንና ያንን ከአላህ ሌላ የሚገዙትን በተለያችሁ ጊዜ ወደ ዋሻው ተጠጉ። ጌታችሁ ለእናንተ ከችሮታው ይዘረጋላችኋልና፤ ከነገራችሁም ለእናንተ መጠቃቀሚያ ያዘጋጅላችኋልና።» (ተባባሉ)። info
التفاسير:

external-link copy
17 : 18

۞ وَتَرَى ٱلشَّمۡسَ إِذَا طَلَعَت تَّزَٰوَرُ عَن كَهۡفِهِمۡ ذَاتَ ٱلۡيَمِينِ وَإِذَا غَرَبَت تَّقۡرِضُهُمۡ ذَاتَ ٱلشِّمَالِ وَهُمۡ فِي فَجۡوَةٖ مِّنۡهُۚ ذَٰلِكَ مِنۡ ءَايَٰتِ ٱللَّهِۗ مَن يَهۡدِ ٱللَّهُ فَهُوَ ٱلۡمُهۡتَدِۖ وَمَن يُضۡلِلۡ فَلَن تَجِدَ لَهُۥ وَلِيّٗا مُّرۡشِدٗا

17.ጸሐይዋ በወጣች ጊዜ ከዋሻቸው ወደ ቀኝ ጎን ስታዘነብል ታያታለህ:: በገባችም ጊዜ ከሰፊው ዋሻ ውስጥ እያሉ በግራ በኩል ትተዋቸዋለች:: ይህ ከአላህ ተዓምራት አንዱ ነው:: አላህ ያቀናው በእርግጥም የተቀናው እርሱ ብቻ ነው:: እርሱ ያጠመመውን ደግሞ ቅኑን መንገድ የሚመራው ረዳት ማንንም አታገኝለትም:: info
التفاسير:

external-link copy
18 : 18

وَتَحۡسَبُهُمۡ أَيۡقَاظٗا وَهُمۡ رُقُودٞۚ وَنُقَلِّبُهُمۡ ذَاتَ ٱلۡيَمِينِ وَذَاتَ ٱلشِّمَالِۖ وَكَلۡبُهُم بَٰسِطٞ ذِرَاعَيۡهِ بِٱلۡوَصِيدِۚ لَوِ ٱطَّلَعۡتَ عَلَيۡهِمۡ لَوَلَّيۡتَ مِنۡهُمۡ فِرَارٗا وَلَمُلِئۡتَ مِنۡهُمۡ رُعۡبٗا

18. እነርሱ በጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ እያሉ የነቁ ይመስሉሃል:: ወደቀኝና ወደ ግራ ጎናቸው እናገላብጣቸዋለን:: ውሻቸዉም በዋሻቸው በር ላይ የፊት እግሩን ዘርግቷል:: ብታያቸው ኖሮ ከእነርሱ በእርግጥ የምትሸሽ ኾነህ በዞርክ ነበር:: በፍርሀትም በተሞላህ ነበር:: info
التفاسير:

external-link copy
19 : 18

وَكَذَٰلِكَ بَعَثۡنَٰهُمۡ لِيَتَسَآءَلُواْ بَيۡنَهُمۡۚ قَالَ قَآئِلٞ مِّنۡهُمۡ كَمۡ لَبِثۡتُمۡۖ قَالُواْ لَبِثۡنَا يَوۡمًا أَوۡ بَعۡضَ يَوۡمٖۚ قَالُواْ رَبُّكُمۡ أَعۡلَمُ بِمَا لَبِثۡتُمۡ فَٱبۡعَثُوٓاْ أَحَدَكُم بِوَرِقِكُمۡ هَٰذِهِۦٓ إِلَى ٱلۡمَدِينَةِ فَلۡيَنظُرۡ أَيُّهَآ أَزۡكَىٰ طَعَامٗا فَلۡيَأۡتِكُم بِرِزۡقٖ مِّنۡهُ وَلۡيَتَلَطَّفۡ وَلَا يُشۡعِرَنَّ بِكُمۡ أَحَدًا

19. ልክ እንዳስተኛናቸውም ሁሉ በመካከላቸው እንዲጠያየቁም ቀሰቀስናቸው:: ከእነርሱ አንድ ተናጋሪ «ምን ያህል ቆያችሁ አለ?» ሌሎቹም «አንድን ቀን ወይም የቀንን ከፊል ቆየን።» አሉ። ተባባሉም: «ጌታችሁ የቆያችሁትን ጊዜ ልክ አዋቂ ነው:: ከዚህም ገንዘባችሁ ጋር አንዳችሁን ወደ ከተማይቱ ላኩ:: ከምግብ የትኛዋ ንጹህ መሆኗንም ይመልከት:: (ከንጹሑ) ምግብን ያምጣላችሁ:: ቀስም ይበል:: በእናንተም አንድንም ሰው አያሳውቅ። info
التفاسير:

external-link copy
20 : 18

إِنَّهُمۡ إِن يَظۡهَرُواْ عَلَيۡكُمۡ يَرۡجُمُوكُمۡ أَوۡ يُعِيدُوكُمۡ فِي مِلَّتِهِمۡ وَلَن تُفۡلِحُوٓاْ إِذًا أَبَدٗا

20. «እነርሱ በእናንተ ላይ ቢዘልቁ ይቀጠቅጧችኋል:: ወይም ወደ ሃይማኖታቸው ይመልሷችኋል፤ ያን ጊዜም በፍጹም ፍላጎታችሁን አታገኙም።» ተባባሉ። info
التفاسير: