ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
46 : 18

ٱلۡمَالُ وَٱلۡبَنُونَ زِينَةُ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۖ وَٱلۡبَٰقِيَٰتُ ٱلصَّٰلِحَٰتُ خَيۡرٌ عِندَ رَبِّكَ ثَوَابٗا وَخَيۡرٌ أَمَلٗا

46. ገንዘብና ልጆች የቅርቢቱ ህይወት ጌጦች ብቻ ናቸው:: መልካም ቀሪ ሥራዎች ግን በጌታህ ዘንድ በምንዳ በላጭ ናቸው:: በተስፋም በላጭ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
47 : 18

وَيَوۡمَ نُسَيِّرُ ٱلۡجِبَالَ وَتَرَى ٱلۡأَرۡضَ بَارِزَةٗ وَحَشَرۡنَٰهُمۡ فَلَمۡ نُغَادِرۡ مِنۡهُمۡ أَحَدٗا

47. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ተራራዎችን የምናስኬድበትን ቀን አስታውስ:: ምድርንም ግልጽ ሆና ታያታለህ:: እንሰበስባቸዋለንም:: ከእነርሱ አንድንም አንተዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
48 : 18

وَعُرِضُواْ عَلَىٰ رَبِّكَ صَفّٗا لَّقَدۡ جِئۡتُمُونَا كَمَا خَلَقۡنَٰكُمۡ أَوَّلَ مَرَّةِۭۚ بَلۡ زَعَمۡتُمۡ أَلَّن نَّجۡعَلَ لَكُم مَّوۡعِدٗا

48. የተሰለፉ ሆነው በጌታህ ላይ ይቀርባሉ:: ይባላሉም «በመጀመሪያ ጊዜ እንደፈጠርናችሁ በእርግጥ ወደ እኛ መጣችሁ:: በእውነቱ ለእናንተ የመቀስቀሻ ጊዜን አናደርግም መስሏችሁ ነበር።» info
التفاسير:

external-link copy
49 : 18

وَوُضِعَ ٱلۡكِتَٰبُ فَتَرَى ٱلۡمُجۡرِمِينَ مُشۡفِقِينَ مِمَّا فِيهِ وَيَقُولُونَ يَٰوَيۡلَتَنَا مَالِ هَٰذَا ٱلۡكِتَٰبِ لَا يُغَادِرُ صَغِيرَةٗ وَلَا كَبِيرَةً إِلَّآ أَحۡصَىٰهَاۚ وَوَجَدُواْ مَا عَمِلُواْ حَاضِرٗاۗ وَلَا يَظۡلِمُ رَبُّكَ أَحَدٗا

49 ለሰው ሁሉ መጽሐፉ ይቀርባል:: ወዲያዉም ከሓዲያንን በውስጡ ካለው ነገር ፈሪዎች ሆነው ታያቸዋለህ። «ዋ ጥፋታችን! ይህ መጽሐፍ ከሥራ ትንሽንም ትልቅንም የቆጠራት ቢሆን እንጂ የማይተወው ምን አለው?» ይላሉ:: የሠሩትንም ነገር ሁሉ ቅርብ ሆኖ ያገኙታል:: ጌታህም አንድንም አይበድልም:: info
التفاسير:

external-link copy
50 : 18

وَإِذۡ قُلۡنَا لِلۡمَلَٰٓئِكَةِ ٱسۡجُدُواْ لِأٓدَمَ فَسَجَدُوٓاْ إِلَّآ إِبۡلِيسَ كَانَ مِنَ ٱلۡجِنِّ فَفَسَقَ عَنۡ أَمۡرِ رَبِّهِۦٓۗ أَفَتَتَّخِذُونَهُۥ وَذُرِّيَّتَهُۥٓ أَوۡلِيَآءَ مِن دُونِي وَهُمۡ لَكُمۡ عَدُوُّۢۚ بِئۡسَ لِلظَّٰلِمِينَ بَدَلٗا

50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለመላዕክት «ለአደም ስገዱ።» ባልናቸው ጊዜ (የሆነውን አስታውስ):: ወዲያዉም ዲያብሎስ ብቻ ሲቀር ሁሉም ሰገዱ:: ከአጋንንት ጎሳ ነበርና:: ከጌታዉም ትዕዛዝ ወጣ:: እርሱንና ዘሮቹን እነርሱም ለእናንተ ጠላቶች ሲሆኑ ከኔ ሌላ ረዳቶች ታደርጋላችሁን? ለበዳዮች ልዋጭነቱ ከፋ:: info
التفاسير:

external-link copy
51 : 18

۞ مَّآ أَشۡهَدتُّهُمۡ خَلۡقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَلَا خَلۡقَ أَنفُسِهِمۡ وَمَا كُنتُ مُتَّخِذَ ٱلۡمُضِلِّينَ عَضُدٗا

51.የሰማያትና የምድርም አፈጣጠር አላሰየኋቸዉም:: የነፍሶቻቸውንም አፈጣጠር እንደዚሁ አሳሳቾችንም ረዳቶች አድርጌ የምይዝ አይደለሁም:: info
التفاسير:

external-link copy
52 : 18

وَيَوۡمَ يَقُولُ نَادُواْ شُرَكَآءِيَ ٱلَّذِينَ زَعَمۡتُمۡ فَدَعَوۡهُمۡ فَلَمۡ يَسۡتَجِيبُواْ لَهُمۡ وَجَعَلۡنَا بَيۡنَهُم مَّوۡبِقٗا

52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያንም አምላክ የምትሏቸውን ተጋሪዎቼን ጥሩ።» የሚልበትን ቀን አስታውስ:: ይጠሯቸዋልም። ግን አይመልሱላቸዉም:: በመካከላቸዉም መጥፊያን ስፍራ ገሀነምንም አደረግን። info
التفاسير:

external-link copy
53 : 18

وَرَءَا ٱلۡمُجۡرِمُونَ ٱلنَّارَ فَظَنُّوٓاْ أَنَّهُم مُّوَاقِعُوهَا وَلَمۡ يَجِدُواْ عَنۡهَا مَصۡرِفٗا

53. ከሓዲያንም እሳትን ያያሉ፤ እነርሱም በውስጧ ወዳቂዎች መሆናቸውን ያረጋግጣሉ:: ከእርሷም መሸሻን አያገኙም። info
التفاسير: