ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
28 : 18

وَٱصۡبِرۡ نَفۡسَكَ مَعَ ٱلَّذِينَ يَدۡعُونَ رَبَّهُم بِٱلۡغَدَوٰةِ وَٱلۡعَشِيِّ يُرِيدُونَ وَجۡهَهُۥۖ وَلَا تَعۡدُ عَيۡنَاكَ عَنۡهُمۡ تُرِيدُ زِينَةَ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۖ وَلَا تُطِعۡ مَنۡ أَغۡفَلۡنَا قَلۡبَهُۥ عَن ذِكۡرِنَا وَٱتَّبَعَ هَوَىٰهُ وَكَانَ أَمۡرُهُۥ فُرُطٗا

28. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ነፍስህንም ከእነዚያ ጌታቸውን ፊቱን የሚሹ ሆነው በጥዋትና በማታ ከሚገዙት ጋር አስታግስ:: የቅርቢቱንም ህይወት ሽልማት የምትሻ ሆነህ አይኖችህ ከእነርሱ ወደ ሌላ አይለፉ:: ያ ልቡን እኛን ከማስታወስ ያዘነጋነውንና የግል ፍላጎቱን የተከተለውን ነገሩ ሁሉ ወሰን ማለፍ የሆነውን ሰው አትታዘዝ። info
التفاسير:

external-link copy
29 : 18

وَقُلِ ٱلۡحَقُّ مِن رَّبِّكُمۡۖ فَمَن شَآءَ فَلۡيُؤۡمِن وَمَن شَآءَ فَلۡيَكۡفُرۡۚ إِنَّآ أَعۡتَدۡنَا لِلظَّٰلِمِينَ نَارًا أَحَاطَ بِهِمۡ سُرَادِقُهَاۚ وَإِن يَسۡتَغِيثُواْ يُغَاثُواْ بِمَآءٖ كَٱلۡمُهۡلِ يَشۡوِي ٱلۡوُجُوهَۚ بِئۡسَ ٱلشَّرَابُ وَسَآءَتۡ مُرۡتَفَقًا

29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰዎች ሆይ! እውነቱ ሁሉ ከጌታችሁ ነው:: ስለዚህ የፈለገም ሰው በእውነቱ ይመን:: የፈለገም ሰው ይካድ።» በላቸው:: እኛ ለበደለኛ ከሓዲያን አጥሯ በእነርሱ ላይ የከበበ የሆነችውን እሳት አዘጋጅተናል:: ከጥም ለመዳን እርዳታን ቢፈልጉ እንደ ዘይት ዝቃጭ ባለ ፊቶችን በሚጠብስ ውሃ ይረዳሉ:: መጠጡም ከፋ፤ መደገፊያይቱም ምንኛ አስከፋች! info
التفاسير:

external-link copy
30 : 18

إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ إِنَّا لَا نُضِيعُ أَجۡرَ مَنۡ أَحۡسَنَ عَمَلًا

30. እነዚያ በአላህ ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ እኛ ሥራ ያሳመረን ምንዳ አናጠፋም። info
التفاسير:

external-link copy
31 : 18

أُوْلَٰٓئِكَ لَهُمۡ جَنَّٰتُ عَدۡنٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهِمُ ٱلۡأَنۡهَٰرُ يُحَلَّوۡنَ فِيهَا مِنۡ أَسَاوِرَ مِن ذَهَبٖ وَيَلۡبَسُونَ ثِيَابًا خُضۡرٗا مِّن سُندُسٖ وَإِسۡتَبۡرَقٖ مُّتَّكِـِٔينَ فِيهَا عَلَى ٱلۡأَرَآئِكِۚ نِعۡمَ ٱلثَّوَابُ وَحَسُنَتۡ مُرۡتَفَقٗا

31.እነዚያ ለእነርሱ የመኖሪያ ገነቶች ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው አሏቸው:: በእርሷ ውስጥ ከወርቅ የሆኑን አምባሮች ይሸለማሉ:: ከቀጭን ሀርና ከወፍራም ሀርም አረንጓዴ ልብሶችን ይለብሳሉ:: በውስጧ በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ የተደገፉ ሆነው ይቀመጣሉ:: እነዚህ ሰዎች ምንዳቸው ምን ያምር! መኖሪያቸው ገነትም ምንኛ አማረች! info
التفاسير:

external-link copy
32 : 18

۞ وَٱضۡرِبۡ لَهُم مَّثَلٗا رَّجُلَيۡنِ جَعَلۡنَا لِأَحَدِهِمَا جَنَّتَيۡنِ مِنۡ أَعۡنَٰبٖ وَحَفَفۡنَٰهُمَا بِنَخۡلٖ وَجَعَلۡنَا بَيۡنَهُمَا زَرۡعٗا

32. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለከሓዲያን የሁለትን ሰዎችን ምሳሌ ግለጽላቸው:: ለአንደኛው ከሓዲ ሁለት የወይን አትክልቶች አደረግንለት። በዘንባባም ከበብናቸው። በመካከላቸውም አዝመራን አደረግን። info
التفاسير:

external-link copy
33 : 18

كِلۡتَا ٱلۡجَنَّتَيۡنِ ءَاتَتۡ أُكُلَهَا وَلَمۡ تَظۡلِم مِّنۡهُ شَيۡـٔٗاۚ وَفَجَّرۡنَا خِلَٰلَهُمَا نَهَرٗا

33. ሁለቱም አትክልቶች ሰብላቸውን ሰጡ፤ ከርሱም ምንም አላጎደሉም። በመካከላቸዉም ወንዝን አፈሰስን። info
التفاسير:

external-link copy
34 : 18

وَكَانَ لَهُۥ ثَمَرٞ فَقَالَ لِصَٰحِبِهِۦ وَهُوَ يُحَاوِرُهُۥٓ أَنَا۠ أَكۡثَرُ مِنكَ مَالٗا وَأَعَزُّ نَفَرٗا

34.ለእርሱ ከአትክልቶቹ ሌላ ፍሬያማ ሀብት ነበረው:: ለአማኙ ጓደኛዉም የሚወዳደረው ሲሆን «እኔ ካንተ በገንዘብ ይበልጥ የበዛሁ በወገንም ይበልጥ የበረታሁ ነኝ።» አለው። info
التفاسير: