የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ

የገፅ ቁጥር:close

external-link copy
160 : 26

كَذَّبَتۡ قَوۡمُ لُوطٍ ٱلۡمُرۡسَلِينَ

160. የሉጥ ህዝቦች መልዕክተኞችን አስተባበሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
161 : 26

إِذۡ قَالَ لَهُمۡ أَخُوهُمۡ لُوطٌ أَلَا تَتَّقُونَ

161. ወንድማቸው ሉጥ ለእነርሱ ባለ ጊዜ: «አትጠነቀቁምን? info
التفاسير:

external-link copy
162 : 26

إِنِّي لَكُمۡ رَسُولٌ أَمِينٞ

162. «እኔ ለእናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝ። info
التفاسير:

external-link copy
163 : 26

فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ

163. «አላህንም ፍሩ ታዘዙኝም። info
التفاسير:

external-link copy
164 : 26

وَمَآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ مِنۡ أَجۡرٍۖ إِنۡ أَجۡرِيَ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

164. «በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አለምናችሁም:: ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም:: info
التفاسير:

external-link copy
165 : 26

أَتَأۡتُونَ ٱلذُّكۡرَانَ مِنَ ٱلۡعَٰلَمِينَ

165. «ከዓለማት ሰዎች መካከል የተለየ ወንዶችን ትገናኛላችሁን? info
التفاسير:

external-link copy
166 : 26

وَتَذَرُونَ مَا خَلَقَ لَكُمۡ رَبُّكُم مِّنۡ أَزۡوَٰجِكُمۚ بَلۡ أَنتُمۡ قَوۡمٌ عَادُونَ

166. «ከሚስቶቻችሁም ጌታችሁ ለእናንተ የፈጠረላችሁን ትተዋላችሁን? በእውነት እናንተ ወሰን አላፊዎች ህዝቦች ናችሁ።» (አለ) info
التفاسير:

external-link copy
167 : 26

قَالُواْ لَئِن لَّمۡ تَنتَهِ يَٰلُوطُ لَتَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡمُخۡرَجِينَ

167. እነርሱም አሉ: «ሉጥ ሆይ! ከዚህ ነገርህ ባትከለከል በእርግጥ በሀይል ከአገር ከሚወጡት ትሆናለህ።» info
التفاسير:

external-link copy
168 : 26

قَالَ إِنِّي لِعَمَلِكُم مِّنَ ٱلۡقَالِينَ

168. እርሱም አለ: «እኔ ስራችሁን ከሚጠሉት ሰዎች አንዱ ነኝ። info
التفاسير:

external-link copy
169 : 26

رَبِّ نَجِّنِي وَأَهۡلِي مِمَّا يَعۡمَلُونَ

169. «ጌታዬ ሆይ! እኔንም ሆነ ቤተሰቦቼን እኒህ ህዝቦች ከሚሰሩት ስራ ቅጣት አድነን።» info
التفاسير:

external-link copy
170 : 26

فَنَجَّيۡنَٰهُ وَأَهۡلَهُۥٓ أَجۡمَعِينَ

170. እርሱንም ሆነ ቤተሰቦቹንም በጠቅላላ አዳንናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
171 : 26

إِلَّا عَجُوزٗا فِي ٱلۡغَٰبِرِينَ

171. በቀሪዎቹ ውስጥ የሆነች አሮጊት ስተቀር (እርሷ ግን ጠፋች):: info
التفاسير:

external-link copy
172 : 26

ثُمَّ دَمَّرۡنَا ٱلۡأٓخَرِينَ

172. ከዚያም ሌሎቹን አጠፋን። info
التفاسير:

external-link copy
173 : 26

وَأَمۡطَرۡنَا عَلَيۡهِم مَّطَرٗاۖ فَسَآءَ مَطَرُ ٱلۡمُنذَرِينَ

173. በእነርሱም ላይ የድንጋይን ዝናብን አዘነብንባቸው:: የተስፋራሪዎችም ዝናብ ከፋ:: info
التفاسير:

external-link copy
174 : 26

إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗۖ وَمَا كَانَ أَكۡثَرُهُم مُّؤۡمِنِينَ

174. በዚህ ውስጥ አስደናቂ ተዐምር አለበት:: አብዛኞቻቸዉም ምዕምናን አልነበሩም:: info
التفاسير:

external-link copy
175 : 26

وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ

175. ጌታህ እርሱ አሸናፊውና አዛኙ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
176 : 26

كَذَّبَ أَصۡحَٰبُ لۡـَٔيۡكَةِ ٱلۡمُرۡسَلِينَ

176. የአይካ ሰዎች መልዕክተኞችን አስተባበሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
177 : 26

إِذۡ قَالَ لَهُمۡ شُعَيۡبٌ أَلَا تَتَّقُونَ

177. ወንድማቸው ሹዐይብ ለእነርሱ ባላቸው ጊዜ: «አትጠነቀቁምን? info
التفاسير:

external-link copy
178 : 26

إِنِّي لَكُمۡ رَسُولٌ أَمِينٞ

178. «እኔ ለእናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝ። info
التفاسير:

external-link copy
179 : 26

فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ

179. «አላህን ፍሩ፤ ታዘዙኝም። info
التفاسير:

external-link copy
180 : 26

وَمَآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ مِنۡ أَجۡرٍۖ إِنۡ أَجۡرِيَ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

180. «በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አልጠይቃችሁም፤ ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም። info
التفاسير:

external-link copy
181 : 26

۞ أَوۡفُواْ ٱلۡكَيۡلَ وَلَا تَكُونُواْ مِنَ ٱلۡمُخۡسِرِينَ

181. «ስፍርንም ሙሉ:: ከአጎዳዮችም አትሁኑ። info
التفاسير:

external-link copy
182 : 26

وَزِنُواْ بِٱلۡقِسۡطَاسِ ٱلۡمُسۡتَقِيمِ

182. «በትክክለኛ ሚዛንም መዝኑ። info
التفاسير:

external-link copy
183 : 26

وَلَا تَبۡخَسُواْ ٱلنَّاسَ أَشۡيَآءَهُمۡ وَلَا تَعۡثَوۡاْ فِي ٱلۡأَرۡضِ مُفۡسِدِينَ

183. «ሰዎችንም ነገሮቻቸውን አታጉድሉባቸው:: በምድርም ላይ አጥፊዎች ሆናችሁ አታበላሹ። info
التفاسير: