የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ

የገፅ ቁጥር:close

external-link copy
112 : 26

قَالَ وَمَا عِلۡمِي بِمَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ

112. እርሱም አላቸው፡- «ይሰሩት በነበሩት ነገር ምን ዕውቀት አለኝና? info
التفاسير:

external-link copy
113 : 26

إِنۡ حِسَابُهُمۡ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّيۖ لَوۡ تَشۡعُرُونَ

113. «ምርመራቸው በጌታዬ ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም:: ብታውቁ ኖሮ ይህንን ትረዱት ነበር። info
التفاسير:

external-link copy
114 : 26

وَمَآ أَنَا۠ بِطَارِدِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ

114. «እኔ አማኞችን አባራሪ አይደለሁም። info
التفاسير:

external-link copy
115 : 26

إِنۡ أَنَا۠ إِلَّا نَذِيرٞ مُّبِينٞ

115. «እኔም እኮ ግልጽ አስፈራሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም።» (አለ) info
التفاسير:

external-link copy
116 : 26

قَالُواْ لَئِن لَّمۡ تَنتَهِ يَٰنُوحُ لَتَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡمَرۡجُومِينَ

116. «ኑህ ሆይ! ከምትለው ባትከለከል በእርግጥ ከሚወገሩት ትሆናለህ።» አሉት። info
التفاسير:

external-link copy
117 : 26

قَالَ رَبِّ إِنَّ قَوۡمِي كَذَّبُونِ

117. እርሱም አለ፡- «ጌታየ ሆይ! ህዝቦቼ አስተባበሉኝ። info
التفاسير:

external-link copy
118 : 26

فَٱفۡتَحۡ بَيۡنِي وَبَيۡنَهُمۡ فَتۡحٗا وَنَجِّنِي وَمَن مَّعِيَ مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ

118. «በእኔና በእነርሱም መካከል ተገቢ ፍርድን ፍረድ:: ከእነርሱ አድነኝም:: ከእኔ ጋር ያሉትን አማኞችም አድን።» info
التفاسير:

external-link copy
119 : 26

فَأَنجَيۡنَٰهُ وَمَن مَّعَهُۥ فِي ٱلۡفُلۡكِ ٱلۡمَشۡحُونِ

119. እርሱንም ሆነ ከእርሱ ጋር ያሉትን ሁሉ በተሞላው መርከብ ውስጥ አዳንን:: info
التفاسير:

external-link copy
120 : 26

ثُمَّ أَغۡرَقۡنَا بَعۡدُ ٱلۡبَاقِينَ

120. ከዚያም በኋላ ቀሪዎቹን አሰመጥን። info
التفاسير:

external-link copy
121 : 26

إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗۖ وَمَا كَانَ أَكۡثَرُهُم مُّؤۡمِنِينَ

121. በዚህ ውስጥ ታላቅ ግሣጼ አለበት፤ አብዛሀኞቻቸዉም ትክክለኛ አማኞች አልነበሩም:: info
التفاسير:

external-link copy
122 : 26

وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ

122. ጌታህም እርሱ በእርግጥ ሁሉን አሸናፊዉና አዛኙ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
123 : 26

كَذَّبَتۡ عَادٌ ٱلۡمُرۡسَلِينَ

123. ዓድ መልዕክተኞችን አስተባበለች፤ info
التفاسير:

external-link copy
124 : 26

إِذۡ قَالَ لَهُمۡ أَخُوهُمۡ هُودٌ أَلَا تَتَّقُونَ

124. ወንድማቸው ሁድ ለእነርሱ ባላቸው ጊዜ: «አትጠነቀቁምን? info
التفاسير:

external-link copy
125 : 26

إِنِّي لَكُمۡ رَسُولٌ أَمِينٞ

125. «እኔ ለእናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝ። info
التفاسير:

external-link copy
126 : 26

فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ

126. «አላህን ብቻ ፍሩ ታዘዙኝም። info
التفاسير:

external-link copy
127 : 26

وَمَآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ مِنۡ أَجۡرٍۖ إِنۡ أَجۡرِيَ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

127. «በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አለምናችሁም:: ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ ብቻ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም። info
التفاسير:

external-link copy
128 : 26

أَتَبۡنُونَ بِكُلِّ رِيعٍ ءَايَةٗ تَعۡبَثُونَ

128. «የምትጫወቱ ሆናችሁ በከፍተኛ ስፍራ ሁሉ ላይ ምልክት ትገነባላችሁን? info
التفاسير:

external-link copy
129 : 26

وَتَتَّخِذُونَ مَصَانِعَ لَعَلَّكُمۡ تَخۡلُدُونَ

129. «የውሃ ማጠራቀሚያዎችንና ህንፃዎችንም ለዘላለም መኖርን የምትከጅሉ ሆናችሁ ትሰራላችሁን? info
التفاسير:

external-link copy
130 : 26

وَإِذَا بَطَشۡتُم بَطَشۡتُمۡ جَبَّارِينَ

130. «በቀጣችሁም ጊዜ ጨካኞች ሆናችሁ ትቀጣላችሁን? info
التفاسير:

external-link copy
131 : 26

فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ

131. «አላህንም ፍሩ። ታዘዙኝም። info
التفاسير:

external-link copy
132 : 26

وَٱتَّقُواْ ٱلَّذِيٓ أَمَدَّكُم بِمَا تَعۡلَمُونَ

132. «ያንንም በምታውቁት ጸጋ ያጣቀማችሁን ጌታን (አላህን) ፍሩ። info
التفاسير:

external-link copy
133 : 26

أَمَدَّكُم بِأَنۡعَٰمٖ وَبَنِينَ

133. «በእንስሳዎችና በልጆችም ያጣቀማችሁ። info
التفاسير:

external-link copy
134 : 26

وَجَنَّٰتٖ وَعُيُونٍ

134. «በአትክልቶችና በምንጮችም ያጣቀማችሁን ጌታን (አላህን) ፍሩ። info
التفاسير:

external-link copy
135 : 26

إِنِّيٓ أَخَافُ عَلَيۡكُمۡ عَذَابَ يَوۡمٍ عَظِيمٖ

135. «እኔ በእናንተ ላይ የታላቅን ቀን ቅጣት እፈራለሁና።» info
التفاسير:

external-link copy
136 : 26

قَالُواْ سَوَآءٌ عَلَيۡنَآ أَوَعَظۡتَ أَمۡ لَمۡ تَكُن مِّنَ ٱلۡوَٰعِظِينَ

136. እነርሱም አሉ: «ብትገስጽም ወይም ከገሳጮች ባትሆንም በእኛ ላይ እኩል ነው። info
التفاسير: