የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ

የገፅ ቁጥር:close

external-link copy
84 : 26

وَٱجۡعَل لِّي لِسَانَ صِدۡقٖ فِي ٱلۡأٓخِرِينَ

84. «በኋለኞቹም ህዝቦች ውስጥ ለእኔ መልካም ዝናን አድርግልኝ። info
التفاسير:

external-link copy
85 : 26

وَٱجۡعَلۡنِي مِن وَرَثَةِ جَنَّةِ ٱلنَّعِيمِ

85. «የጸጋይቱን ገነት ከሚወርሱትም ሰዎች አድርገኝ። info
التفاسير:

external-link copy
86 : 26

وَٱغۡفِرۡ لِأَبِيٓ إِنَّهُۥ كَانَ مِنَ ٱلضَّآلِّينَ

86. «ለአባቴም ኃጢያቱን ማር። እርሱ ከተሳሳቱት ነበርና። info
التفاسير:

external-link copy
87 : 26

وَلَا تُخۡزِنِي يَوۡمَ يُبۡعَثُونَ

87. «በሚቀሰቀሱበት ቀንም አታዋርደኝ። info
التفاسير:

external-link copy
88 : 26

يَوۡمَ لَا يَنفَعُ مَالٞ وَلَا بَنُونَ

88. «ገንዘብም ሆነ ልጆች በማይጠቅሙበት ቀን፤ info
التفاسير:

external-link copy
89 : 26

إِلَّا مَنۡ أَتَى ٱللَّهَ بِقَلۡبٖ سَلِيمٖ

89. «ወደ አላህ በንጹህ ልብ የመጣ ቢሆን አንጂ።» info
التفاسير:

external-link copy
90 : 26

وَأُزۡلِفَتِ ٱلۡجَنَّةُ لِلۡمُتَّقِينَ

90. ገነትም ለጥንቁቆቹ በምትቀረብበት ቀን፤ info
التفاسير:

external-link copy
91 : 26

وَبُرِّزَتِ ٱلۡجَحِيمُ لِلۡغَاوِينَ

91. ገሀነምም ለጠማሞቹ በምትገለጽበት ቀን:: info
التفاسير:

external-link copy
92 : 26

وَقِيلَ لَهُمۡ أَيۡنَ مَا كُنتُمۡ تَعۡبُدُونَ

92. ለእነርሱም «እነዚያ ትገዟቸው የነበራችሁት የት ናቸው? info
التفاسير:

external-link copy
93 : 26

مِن دُونِ ٱللَّهِ هَلۡ يَنصُرُونَكُمۡ أَوۡ يَنتَصِرُونَ

93. « ከአላህ ሌላ ሲሆኑ (ትገዟቸው የነበራችሁ) ይረዱዋችኋልን? ወይስ ለራሳቸው ይረዳሉን?» በሚባል ቀን። info
التفاسير:

external-link copy
94 : 26

فَكُبۡكِبُواْ فِيهَا هُمۡ وَٱلۡغَاوُۥنَ

94. በውስጧም እነርሱና ጠማሞች በፊቶቻቸው ተጥለው ይንከባለላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
95 : 26

وَجُنُودُ إِبۡلِيسَ أَجۡمَعُونَ

95 የሰይጣንም ሰራዊቶች መላዉም ይጣላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
96 : 26

قَالُواْ وَهُمۡ فِيهَا يَخۡتَصِمُونَ

96. እነርሱም በርሷ ውስጥ የሚከራከሩ ሆነው ይላሉ: info
التفاسير:

external-link copy
97 : 26

تَٱللَّهِ إِن كُنَّا لَفِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٍ

97. «በአላህ እንምላለን፤ እኛ በግልጽ መሳሳት ውስጥ ነብርን። info
التفاسير:

external-link copy
98 : 26

إِذۡ نُسَوِّيكُم بِرَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

98. «በዓለማት ጌታ ባስተካከልናችሁ ጊዜ። info
التفاسير:

external-link copy
99 : 26

وَمَآ أَضَلَّنَآ إِلَّا ٱلۡمُجۡرِمُونَ

99. «አመጸኞቹም እንጅ ሌላ አላሳሳተንም። info
التفاسير:

external-link copy
100 : 26

فَمَا لَنَا مِن شَٰفِعِينَ

100. «ከአማላጆችም ለኛ ምንም የለንም። info
التفاسير:

external-link copy
101 : 26

وَلَا صَدِيقٍ حَمِيمٖ

101. «አዛኝ ወዳጅም የለንም። info
التفاسير:

external-link copy
102 : 26

فَلَوۡ أَنَّ لَنَا كَرَّةٗ فَنَكُونَ مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ

102 «ለእኛም አንዲት ጊዜ እንኳን የመመለስ እድል በኖረንና ከትክክለኛ አማኞች በሆን እንመኛለን።» ይላሉ። info
التفاسير:

external-link copy
103 : 26

إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗۖ وَمَا كَانَ أَكۡثَرُهُم مُّؤۡمِنِينَ

103. በዚህ ውስጥ አስደናቂ ግሣጼ አለበት:: አብዛሀኞቻቸዉም ትክክለኛ አማኞች አልነበሩም:: info
التفاسير:

external-link copy
104 : 26

وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ

104. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም እርሱ በእርግጥ ሁሉን አሸናፊዉና አዛኙ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
105 : 26

كَذَّبَتۡ قَوۡمُ نُوحٍ ٱلۡمُرۡسَلِينَ

105. የኑህ ህዝቦች መልዕክተኞችን አስተባበሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
106 : 26

إِذۡ قَالَ لَهُمۡ أَخُوهُمۡ نُوحٌ أَلَا تَتَّقُونَ

106. ወንድማቸው ኑህ ለእነርሱ ባላቸው ጊዜ፡ «አትጠነቀቁምን? info
التفاسير:

external-link copy
107 : 26

إِنِّي لَكُمۡ رَسُولٌ أَمِينٞ

107. «እኔ ለእናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝ። info
التفاسير:

external-link copy
108 : 26

فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ

108. «አላህንም ፍሩ ታዘዙኝም። info
التفاسير:

external-link copy
109 : 26

وَمَآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ مِنۡ أَجۡرٍۖ إِنۡ أَجۡرِيَ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

109. «በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አልጠይቃችሁም:: ዋጋዬ ከዓለማት ጌታ ብቻ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም። info
التفاسير:

external-link copy
110 : 26

فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ

110. «አላህንም ፍሩ። ታዘዙኝም።» info
التفاسير:

external-link copy
111 : 26

۞ قَالُوٓاْ أَنُؤۡمِنُ لَكَ وَٱتَّبَعَكَ ٱلۡأَرۡذَلُونَ

111. እነርሱም «ወራዶቹ ብቻ የተከተሉህ ሆነህ ላንተ እናምናለን?» አሉት። info
التفاسير: