የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ

የገፅ ቁጥር:close

external-link copy
40 : 26

لَعَلَّنَا نَتَّبِعُ ٱلسَّحَرَةَ إِن كَانُواْ هُمُ ٱلۡغَٰلِبِينَ

40. «ድግምተኞቹን እነርሱ አሸናፊዎች ቢሆኑ እንከተል ዘንድ» ተባለ። info
التفاسير:

external-link copy
41 : 26

فَلَمَّا جَآءَ ٱلسَّحَرَةُ قَالُواْ لِفِرۡعَوۡنَ أَئِنَّ لَنَا لَأَجۡرًا إِن كُنَّا نَحۡنُ ٱلۡغَٰلِبِينَ

41. ድግምተኞቹም በመጡ ጊዜ ለፈርዖን: «እኛ አሸናፊዎች ብንሆን ለእኛ ዋጋ አለን?» አሉት። info
التفاسير:

external-link copy
42 : 26

قَالَ نَعَمۡ وَإِنَّكُمۡ إِذٗا لَّمِنَ ٱلۡمُقَرَّبِينَ

42. እርሱም( ፈርዖን) «አዎን። እናንተ ያን ጊዜ እኔ ዘንድ ከባለሟሎቹ ትሆናላችሁ።» አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
43 : 26

قَالَ لَهُم مُّوسَىٰٓ أَلۡقُواْ مَآ أَنتُم مُّلۡقُونَ

43. ሙሳ ለእነርሱ: «የምትጥሉትን ጣሉ።» አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
44 : 26

فَأَلۡقَوۡاْ حِبَالَهُمۡ وَعِصِيَّهُمۡ وَقَالُواْ بِعِزَّةِ فِرۡعَوۡنَ إِنَّا لَنَحۡنُ ٱلۡغَٰلِبُونَ

44. ገመዶቻቸውንና በትሮቻቸውንም ጣሉ:: «በፈርዖንም ክብር ይሁንብን። እኛ በእርግጥ አሸናፊዎች ነን።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
45 : 26

فَأَلۡقَىٰ مُوسَىٰ عَصَاهُ فَإِذَا هِيَ تَلۡقَفُ مَا يَأۡفِكُونَ

45. ሙሳም ብትሩን ጣለ:: ወዲያዉም እርሷ የሚያስመስሉትን ሁሉ ትውጣለች:: info
التفاسير:

external-link copy
46 : 26

فَأُلۡقِيَ ٱلسَّحَرَةُ سَٰجِدِينَ

46. ከዚያም ድግምተኞቹ ሰጋጆች ሆነው ሱጁድ አደረጉ(ወረዱ)። info
التفاسير:

external-link copy
47 : 26

قَالُوٓاْ ءَامَنَّا بِرَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

47. እነርሱም አሉ፡- «በዓለማት ጌታ አመንን። info
التفاسير:

external-link copy
48 : 26

رَبِّ مُوسَىٰ وَهَٰرُونَ

48. «በሙሳና በሃሩን ጌታ (አመንን)።» (አሉ) info
التفاسير:

external-link copy
49 : 26

قَالَ ءَامَنتُمۡ لَهُۥ قَبۡلَ أَنۡ ءَاذَنَ لَكُمۡۖ إِنَّهُۥ لَكَبِيرُكُمُ ٱلَّذِي عَلَّمَكُمُ ٱلسِّحۡرَ فَلَسَوۡفَ تَعۡلَمُونَۚ لَأُقَطِّعَنَّ أَيۡدِيَكُمۡ وَأَرۡجُلَكُم مِّنۡ خِلَٰفٖ وَلَأُصَلِّبَنَّكُمۡ أَجۡمَعِينَ

49. ፈርዖንም «ለእናንተ ሳልፈቅድላችሁ በፊት ለእርሱ አመናችሁን? እርሱ ያ ድግምትን ያስተማራችሁ ታላቃችሁ ነው። ወደፊትም በእርግጥ የሚያገኛችሁን ታውቃላችሁ:: እጆቻችሁንና እግሮቻችሁን ቀኝና ግራን (በማናጋት) በማፈራረቅ እቆራርጣችኋለሁ:: ሁላችሁንም እሰቅላችኃለሁ።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
50 : 26

قَالُواْ لَا ضَيۡرَۖ إِنَّآ إِلَىٰ رَبِّنَا مُنقَلِبُونَ

50. እነርሱም አሉ፡- «ጉዳት የለብንም እኛ ወደ ጌታችን ተመላሾች ነን። info
التفاسير:

external-link copy
51 : 26

إِنَّا نَطۡمَعُ أَن يَغۡفِرَ لَنَا رَبُّنَا خَطَٰيَٰنَآ أَن كُنَّآ أَوَّلَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ

51. «እኛ የምዕምናን መጀመሪያ በመሆናችን ጌታችን ኃጢአቶቻችንን ለኛ ሊምር እንከጅላለን።» info
التفاسير:

external-link copy
52 : 26

۞ وَأَوۡحَيۡنَآ إِلَىٰ مُوسَىٰٓ أَنۡ أَسۡرِ بِعِبَادِيٓ إِنَّكُم مُّتَّبَعُونَ

52. ወደ ሙሳም «ባሮቼን ይዘህ ሌሊት ሂድ እናንተ የሚከተሏችሁ ናችሁና።» ስንል ላክን። info
التفاسير:

external-link copy
53 : 26

فَأَرۡسَلَ فِرۡعَوۡنُ فِي ٱلۡمَدَآئِنِ حَٰشِرِينَ

53. ፈርዖንም በየከተሞቹ ሰብሳቢዎችን (እንዲህ ሲል) ላከ:: info
التفاسير:

external-link copy
54 : 26

إِنَّ هَٰٓؤُلَآءِ لَشِرۡذِمَةٞ قَلِيلُونَ

54. «እነዚህ ጥቂቶቹ ቡድኖች ናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
55 : 26

وَإِنَّهُمۡ لَنَا لَغَآئِظُونَ

55. «እነርሱም ለእኛ አስቆጪዎች ናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
56 : 26

وَإِنَّا لَجَمِيعٌ حَٰذِرُونَ

56. «እኛም ብዙዎች ጥንቁቆች ነን።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
57 : 26

فَأَخۡرَجۡنَٰهُم مِّن جَنَّٰتٖ وَعُيُونٖ

57. አወጣናቸዉም፤ ከአትክልቶችና ከምንጮች:: info
التفاسير:

external-link copy
58 : 26

وَكُنُوزٖ وَمَقَامٖ كَرِيمٖ

58. ከድልቦችም ከመልካም መቀመጫዎችም፤ info
التفاسير:

external-link copy
59 : 26

كَذَٰلِكَۖ وَأَوۡرَثۡنَٰهَا بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ

59. ልክ እንደዚሁ ለኢስራኢል ልጆች አወረስናትም:: info
التفاسير:

external-link copy
60 : 26

فَأَتۡبَعُوهُم مُّشۡرِقِينَ

60. ጸሐይዋ ስትወጣም ተከተሏቸው:: info
التفاسير: