የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ

የገፅ ቁጥር:close

external-link copy
20 : 26

قَالَ فَعَلۡتُهَآ إِذٗا وَأَنَا۠ مِنَ ٱلضَّآلِّينَ

20. ሙሳም አለ፡ «ያን ጊዜ እኔም ከተሳሳቱት ሆኜ ሰራኋት። info
التفاسير:

external-link copy
21 : 26

فَفَرَرۡتُ مِنكُمۡ لَمَّا خِفۡتُكُمۡ فَوَهَبَ لِي رَبِّي حُكۡمٗا وَجَعَلَنِي مِنَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ

21. «በፈራኋችሁም ጊዜ ከናንተ ሸሸሁ። ጌታዬም ለእኔ ጥበብን ሰጠኝ:: ከመልዕክተኞችም አደረገኝ:። info
التفاسير:

external-link copy
22 : 26

وَتِلۡكَ نِعۡمَةٞ تَمُنُّهَا عَلَيَّ أَنۡ عَبَّدتَّ بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ

22. «ይህችም የኢስራኢልን ልጆች ባሪያ በማድረግህ በእኔ ላይ የምትመጻድቅባት ጸጋ ናት።» info
التفاسير:

external-link copy
23 : 26

قَالَ فِرۡعَوۡنُ وَمَا رَبُّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

23. ፈርዖን: «ሙሳ ሆይ! ላከኝ የምትለው የዓለማት ጌታ ምንድን ነው?» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
24 : 26

قَالَ رَبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَآۖ إِن كُنتُم مُّوقِنِينَ

24. ሙሳ፡- «የሰማያት የምድርና በመካከላቸዉም ያለው ፍጡር ሁሉ ጌታ ነው። የምታረጋግጡ ብትሆኑ ነገሩ ይህ ነው።» አለው። info
التفاسير:

external-link copy
25 : 26

قَالَ لِمَنۡ حَوۡلَهُۥٓ أَلَا تَسۡتَمِعُونَ

25. ፈርዖንም ዙሪያውን ላሉት ሰዎች: «አትሰሙምን?» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
26 : 26

قَالَ رَبُّكُمۡ وَرَبُّ ءَابَآئِكُمُ ٱلۡأَوَّلِينَ

26. ሙሳ፡- «ጌታችሁና የመጀመሪያዎቹ አባቶቻችሁም ጌታ ነው።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
27 : 26

قَالَ إِنَّ رَسُولَكُمُ ٱلَّذِيٓ أُرۡسِلَ إِلَيۡكُمۡ لَمَجۡنُونٞ

27. ፈርዖን፡- «ያ ወደ እናንተ የተላከው መልዕክተኛችሁ በእርግጥ ዕብድ ነው።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
28 : 26

قَالَ رَبُّ ٱلۡمَشۡرِقِ وَٱلۡمَغۡرِبِ وَمَا بَيۡنَهُمَآۖ إِن كُنتُمۡ تَعۡقِلُونَ

28. ሙሳ፡- «(አላህ) የምስራቅና የምዕራብ በመካከላቸዉም ያለው ነገር ሁሉ ጌታ ነው:: ታውቁ እንደሆናችሁ (እመኑበት)።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
29 : 26

قَالَ لَئِنِ ٱتَّخَذۡتَ إِلَٰهًا غَيۡرِي لَأَجۡعَلَنَّكَ مِنَ ٱلۡمَسۡجُونِينَ

29. ፈርዖን: «ከእኔ ሌላ አምላክን ብትይዝ በእውነቱ ከእስረኞቹ አደርግሃለሁ።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
30 : 26

قَالَ أَوَلَوۡ جِئۡتُكَ بِشَيۡءٖ مُّبِينٖ

30. ሙሳ፡- «ግልጽ የሆነ አስረጅ ባመጣም እንኳን?» አለው። info
التفاسير:

external-link copy
31 : 26

قَالَ فَأۡتِ بِهِۦٓ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ

31. ፊርዓውን «እንግዲያውስ ከእውነተኞች እንደሆንክ አስረጁን አምጣው።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
32 : 26

فَأَلۡقَىٰ عَصَاهُ فَإِذَا هِيَ ثُعۡبَانٞ مُّبِينٞ

32. በትሩንም ጣለ:: እርሷም ወዲያውኑ ግልጽ እባብ ሆነች:: info
التفاسير:

external-link copy
33 : 26

وَنَزَعَ يَدَهُۥ فَإِذَا هِيَ بَيۡضَآءُ لِلنَّٰظِرِينَ

33 እጁንም አወጣ እርሷም ወዲያውኑ ለተመልካቾች ነጭ (የምታበራ) ሆነች:: info
التفاسير:

external-link copy
34 : 26

قَالَ لِلۡمَلَإِ حَوۡلَهُۥٓ إِنَّ هَٰذَا لَسَٰحِرٌ عَلِيمٞ

34. ፈርዖንም በዙሪያው ላሉት መማክርት አለ: «ይህ በእርግጥ አዋቂ ድግምተኛ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
35 : 26

يُرِيدُ أَن يُخۡرِجَكُم مِّنۡ أَرۡضِكُم بِسِحۡرِهِۦ فَمَاذَا تَأۡمُرُونَ

35. «ከምድራችሁ በድግምት ሊያወጣችሁ ይፈልጋልና ምንን ታዛላችሁ?» አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
36 : 26

قَالُوٓاْ أَرۡجِهۡ وَأَخَاهُ وَٱبۡعَثۡ فِي ٱلۡمَدَآئِنِ حَٰشِرِينَ

36. እነርሱም አሉ: «እርሱንና ወንድሙን አቆያቸው:: ወደየከተሞቹ ሁሉ ሰብሳቢዎችን ላክ። info
التفاسير:

external-link copy
37 : 26

يَأۡتُوكَ بِكُلِّ سَحَّارٍ عَلِيمٖ

37. «በጣም አዋቂ ድግምተኞችን ሁሉ ያመጡልሃልና።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
38 : 26

فَجُمِعَ ٱلسَّحَرَةُ لِمِيقَٰتِ يَوۡمٖ مَّعۡلُومٖ

38. ድግምተኞችም በታወቀ ቀን ቀጠሮ ተሰበሰቡ:: info
التفاسير:

external-link copy
39 : 26

وَقِيلَ لِلنَّاسِ هَلۡ أَنتُم مُّجۡتَمِعُونَ

39. ለሰዎቹም ተባለ: «እናንተ ተሰብስባችኋልን? info
التفاسير: