Salin ng mga Kahulugan ng Marangal na Qur'an - Salin sa Wikang Amhariko ng Akademya ng Aprika

Numero ng Pahina:close

external-link copy
62 : 3

إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ ٱلۡقَصَصُ ٱلۡحَقُّۚ وَمَا مِنۡ إِلَٰهٍ إِلَّا ٱللَّهُۚ وَإِنَّ ٱللَّهَ لَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ

62.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ እውነተኛው ታሪክ ነው:: ትክክለኛ አምላክም ከአላህ በስተቀር የለም። አላህም አሸናፊውና ጥበበኛው አምላክ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
63 : 3

فَإِن تَوَلَّوۡاْ فَإِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمُۢ بِٱلۡمُفۡسِدِينَ

63. (ከማመን) እምቢ ቢሉም (አጥፊዎቹ እነርሱ ናቸው።) አላህ አጥፊዎቹን (ከደህናዎቹ) ለይቶ አዋቂ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
64 : 3

قُلۡ يَٰٓأَهۡلَ ٱلۡكِتَٰبِ تَعَالَوۡاْ إِلَىٰ كَلِمَةٖ سَوَآءِۭ بَيۡنَنَا وَبَيۡنَكُمۡ أَلَّا نَعۡبُدَ إِلَّا ٱللَّهَ وَلَا نُشۡرِكَ بِهِۦ شَيۡـٔٗا وَلَا يَتَّخِذَ بَعۡضُنَا بَعۡضًا أَرۡبَابٗا مِّن دُونِ ٱللَّهِۚ فَإِن تَوَلَّوۡاْ فَقُولُواْ ٱشۡهَدُواْ بِأَنَّا مُسۡلِمُونَ

64.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ሆነችው ቃል ኑ። (እርሷም) ‹አላህን ብቻ እንጂ ሌላን ላንገዛ፤ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፤ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይዝ› ነው።» በላቸው። (ሙስሊሞች ሆይ!) እምቢ ካሉም «እኛ ሙስሊሞች መሆናችንን መስክሩ።» በሏቸው። info
التفاسير:

external-link copy
65 : 3

يَٰٓأَهۡلَ ٱلۡكِتَٰبِ لِمَ تُحَآجُّونَ فِيٓ إِبۡرَٰهِيمَ وَمَآ أُنزِلَتِ ٱلتَّوۡرَىٰةُ وَٱلۡإِنجِيلُ إِلَّا مِنۢ بَعۡدِهِۦٓۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ

65. እናንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በኢብራሂም (ዙሪያ) ለምን ትከራከራላችሁ? ተውራትና ኢንጂል ከእርሱ በኋላ እንጂ አልተወረዱ። ልብ አትሉምን? info
التفاسير:

external-link copy
66 : 3

هَٰٓأَنتُمۡ هَٰٓؤُلَآءِ حَٰجَجۡتُمۡ فِيمَا لَكُم بِهِۦ عِلۡمٞ فَلِمَ تُحَآجُّونَ فِيمَا لَيۡسَ لَكُم بِهِۦ عِلۡمٞۚ وَٱللَّهُ يَعۡلَمُ وَأَنتُمۡ لَا تَعۡلَمُونَ

66 እናንተ እነዚያ እውቀት ባላችሁ ነገር የተከራከራችሁ ናችሁ፡፡ ታዲያ እውቀት በሌላቸሁ ነገር ላይ ለምን ትከራከራላችሁ? አላህ ሁሉን ነገር ያውቃል። እናንተ ግን አታውቁም። info
التفاسير:

external-link copy
67 : 3

مَا كَانَ إِبۡرَٰهِيمُ يَهُودِيّٗا وَلَا نَصۡرَانِيّٗا وَلَٰكِن كَانَ حَنِيفٗا مُّسۡلِمٗا وَمَا كَانَ مِنَ ٱلۡمُشۡرِكِينَ

67. ኢብራሂም አይሁድም ሆነ ክርስቲያን አልነበረም:: ግን በቀጥተኛው ሃይማኖት ቀጥ ያለ ሙስሊም ነበር:: ከአጋሪዎችም አልነበረም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
68 : 3

إِنَّ أَوۡلَى ٱلنَّاسِ بِإِبۡرَٰهِيمَ لَلَّذِينَ ٱتَّبَعُوهُ وَهَٰذَا ٱلنَّبِيُّ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْۗ وَٱللَّهُ وَلِيُّ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ

68.በኢብራሂም ይበልጥ ተገቢዎቹ እነዚያ የተከተሉት፤ ይህ ነብይ (ነብዩ ሙሐመድ) እና እነዚያ ያመኑት ብቻ ናቸው፡፡ አላህ የአማኞች ወዳጅ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
69 : 3

وَدَّت طَّآئِفَةٞ مِّنۡ أَهۡلِ ٱلۡكِتَٰبِ لَوۡ يُضِلُّونَكُمۡ وَمَا يُضِلُّونَ إِلَّآ أَنفُسَهُمۡ وَمَا يَشۡعُرُونَ

69. (ሙስሊሞች ሆይ!) ከመጽሐፉ ባለቤቶች የተወሰኑት ነፍሶቻቸውን እንጂ የማያሳስቱ ሲሆኑ እናንተን ሊያሳስቷችሁ ተመኙ:: እራሳቸውን እንጂ ማንንም አያሳሳስቱም፡፡ እነርሱ ግን ይህንን እውነታ አያውቁም። info
التفاسير:

external-link copy
70 : 3

يَٰٓأَهۡلَ ٱلۡكِتَٰبِ لِمَ تَكۡفُرُونَ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ وَأَنتُمۡ تَشۡهَدُونَ

70. እናንተ የመጽሐፍ ባለቤቶች ሆይ! እናንተ የምታውቁ ስትሆኑ በአላህ አናቅጽ ለምን ትክዳላችሁ? info
التفاسير: