Salin ng mga Kahulugan ng Marangal na Qur'an - Salin sa Wikang Amhariko ng Akademya ng Aprika

Numero ng Pahina:close

external-link copy
158 : 3

وَلَئِن مُّتُّمۡ أَوۡ قُتِلۡتُمۡ لَإِلَى ٱللَّهِ تُحۡشَرُونَ

158. በጂሃድ ብትሞቱ ወይም ብትገደሉ ወደ አላህ ብቻ ትሰበሰባላችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
159 : 3

فَبِمَا رَحۡمَةٖ مِّنَ ٱللَّهِ لِنتَ لَهُمۡۖ وَلَوۡ كُنتَ فَظًّا غَلِيظَ ٱلۡقَلۡبِ لَٱنفَضُّواْ مِنۡ حَوۡلِكَۖ فَٱعۡفُ عَنۡهُمۡ وَٱسۡتَغۡفِرۡ لَهُمۡ وَشَاوِرۡهُمۡ فِي ٱلۡأَمۡرِۖ فَإِذَا عَزَمۡتَ فَتَوَكَّلۡ عَلَى ٱللَّهِۚ إِنَّ ٱللَّهَ يُحِبُّ ٱلۡمُتَوَكِّلِينَ

159. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ ችሮታ ለዘብክላቸው:: አመለ መጥፎና ልበ ደረቅ በሆንክ ኖሮ ከአጠገብህ በተበተኑ ነበር:: ከእነርሱም ጥፋት ይቅር በል:: ለእነርሱም ከአላህ ምህረትን ለምንላቸው:: በሁሉም ነገር ላይ አማክራቸው:: ከዚያ ቁርጥ ሀሳብ ባደረገክ ጊዜ በአላህ ላይ ብቻ ተመካ:: አላህ በእርሱ ላይ ብቻ ተመኪዎችን ይወዳልና:: info
التفاسير:

external-link copy
160 : 3

إِن يَنصُرۡكُمُ ٱللَّهُ فَلَا غَالِبَ لَكُمۡۖ وَإِن يَخۡذُلۡكُمۡ فَمَن ذَا ٱلَّذِي يَنصُرُكُم مِّنۢ بَعۡدِهِۦۗ وَعَلَى ٱللَّهِ فَلۡيَتَوَكَّلِ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ

160. (ሙስሊሞች ሆይ!) አላህ ከረዳችሁ እናንተን የሚያሸንፍ የለም:: እርሱ ካዋረዳቸሁ ደግሞ ከእርሱ ማዋረድ በኋላ የሚረዳችሁ ያ ማን ነው? አማኞች በአላህ ላይ ብቻ ይመኩ። info
التفاسير:

external-link copy
161 : 3

وَمَا كَانَ لِنَبِيٍّ أَن يَغُلَّۚ وَمَن يَغۡلُلۡ يَأۡتِ بِمَا غَلَّ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۚ ثُمَّ تُوَفَّىٰ كُلُّ نَفۡسٖ مَّا كَسَبَتۡ وَهُمۡ لَا يُظۡلَمُونَ

161. የምርኮን ገንዘብ መደበቅ ከነብይ የሚሆን አይደለም። የምርኮን ገንዘብ የሚደብቅም በትንሳኤ ቀን የደበቀውን ነገር ተሸክሞ ይመጣል:: ከዚያ ነፍስ ሁሉ የስራዋን ዋጋ ትመነዳለች:: እነርሱም አይበደሉም። info
التفاسير:

external-link copy
162 : 3

أَفَمَنِ ٱتَّبَعَ رِضۡوَٰنَ ٱللَّهِ كَمَنۢ بَآءَ بِسَخَطٖ مِّنَ ٱللَّهِ وَمَأۡوَىٰهُ جَهَنَّمُۖ وَبِئۡسَ ٱلۡمَصِيرُ

162. የአላህን ውዴታ የተከተለ ሁሉ የአላህን ቁጣ እንዳተረፈና መኖሪያውም ገሀነም እንደሆነው ነውን? ገሀነም ማረፊያነቱ እጅግ ከፋ! info
التفاسير:

external-link copy
163 : 3

هُمۡ دَرَجَٰتٌ عِندَ ٱللَّهِۗ وَٱللَّهُ بَصِيرُۢ بِمَا يَعۡمَلُونَ

163. ሁሉም በአላህ ዘንድ ባለ ልዩ ልዩ ደረጃዎች ናቸው:: አላህ የሚሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
164 : 3

لَقَدۡ مَنَّ ٱللَّهُ عَلَى ٱلۡمُؤۡمِنِينَ إِذۡ بَعَثَ فِيهِمۡ رَسُولٗا مِّنۡ أَنفُسِهِمۡ يَتۡلُواْ عَلَيۡهِمۡ ءَايَٰتِهِۦ وَيُزَكِّيهِمۡ وَيُعَلِّمُهُمُ ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡحِكۡمَةَ وَإِن كَانُواْ مِن قَبۡلُ لَفِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٍ

164. አላህ በአማኞች ላይ ከመካከላቸው የሆነን፤ በእነርሱም ላይ አናቅጽን የሚያነብ፤ ከርክሰት የሚያጠራቸው፤ መጽሐፍንና ጥበብንም የሚያስተምራቸውን መልዕክተኛ በላከላቸው ጊዜ በእርግጥ ለገሰላቸው:: እነርሱም ከዚያ በፊት ግልጽ ስህተት ውስጥ ነበሩ:: info
التفاسير:

external-link copy
165 : 3

أَوَلَمَّآ أَصَٰبَتۡكُم مُّصِيبَةٞ قَدۡ أَصَبۡتُم مِّثۡلَيۡهَا قُلۡتُمۡ أَنَّىٰ هَٰذَاۖ قُلۡ هُوَ مِنۡ عِندِ أَنفُسِكُمۡۗ إِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ

165. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ ያደረሳችሁትን ጥቃት ግማሽ በአገኛችሁ (በደረሰባችሁ) ጊዜ ይህ ከየት ነው የመጣብን አላችሁን? እርሱ ከነፍሶቻችሁ ዘንድ ነው:: አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው።» በላቸው። info
التفاسير: