Salin ng mga Kahulugan ng Marangal na Qur'an - Salin sa Wikang Amhariko ng Akademya ng Aprika

Numero ng Pahina:close

external-link copy
101 : 3

وَكَيۡفَ تَكۡفُرُونَ وَأَنتُمۡ تُتۡلَىٰ عَلَيۡكُمۡ ءَايَٰتُ ٱللَّهِ وَفِيكُمۡ رَسُولُهُۥۗ وَمَن يَعۡتَصِم بِٱللَّهِ فَقَدۡ هُدِيَ إِلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ

101. የአላህ አናቅጽ በእናንተ ላይ እየተነበቡና መልዕክተኛዉም በመካከላችሁ እያለ እንዴት ትክዳላችሁ? በአላህ የሚጠበቅ ሰው ሁሉ ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ተመራ:: info
التفاسير:

external-link copy
102 : 3

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱتَّقُواْ ٱللَّهَ حَقَّ تُقَاتِهِۦ وَلَا تَمُوتُنَّ إِلَّا وَأَنتُم مُّسۡلِمُونَ

102. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ትክክለኛውን ፍራቻ ፍሩት። እናንተም ሙስሊሞች ሆናችሁ እንጂ አትሙቱ። info
التفاسير:

external-link copy
103 : 3

وَٱعۡتَصِمُواْ بِحَبۡلِ ٱللَّهِ جَمِيعٗا وَلَا تَفَرَّقُواْۚ وَٱذۡكُرُواْ نِعۡمَتَ ٱللَّهِ عَلَيۡكُمۡ إِذۡ كُنتُمۡ أَعۡدَآءٗ فَأَلَّفَ بَيۡنَ قُلُوبِكُمۡ فَأَصۡبَحۡتُم بِنِعۡمَتِهِۦٓ إِخۡوَٰنٗا وَكُنتُمۡ عَلَىٰ شَفَا حُفۡرَةٖ مِّنَ ٱلنَّارِ فَأَنقَذَكُم مِّنۡهَاۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمۡ ءَايَٰتِهِۦ لَعَلَّكُمۡ تَهۡتَدُونَ

103. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) የአላህን ጠንካራ የእምነት ገመድም ሁላችሁም ያዙ:: አትለያዩም። ጠበኞች በነበራችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ የዋለውን የአላህን ጸጋም አስታውሱ:: ይሀውም በልቦቻችሁ መካከል አስማማ በጸጋዉም ወንድማማቾች ሆናችሁ:: በእሳት ጉድጓድ አፋፍ ላይ የነበራችሁ ስትሆኑ ከእርሷም አዳናችሁ:: ወደ ቀጥተኛው መንገድ ትመሩ ዘንድ አላህ ለእናንተ አናቅጽን እንደዚሁ ያብራራል:: info
التفاسير:

external-link copy
104 : 3

وَلۡتَكُن مِّنكُمۡ أُمَّةٞ يَدۡعُونَ إِلَى ٱلۡخَيۡرِ وَيَأۡمُرُونَ بِٱلۡمَعۡرُوفِ وَيَنۡهَوۡنَ عَنِ ٱلۡمُنكَرِۚ وَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُفۡلِحُونَ

104. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ከናንተ መካከል ወደ በጎ ነገር የሚጠሩና በመልካም ስራ የሚያዙ፤ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ቡድኖች ይኑሩ:: እነዚያ ከእሳት የሚድኑ እነርሱው ናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
105 : 3

وَلَا تَكُونُواْ كَٱلَّذِينَ تَفَرَّقُواْ وَٱخۡتَلَفُواْ مِنۢ بَعۡدِ مَا جَآءَهُمُ ٱلۡبَيِّنَٰتُۚ وَأُوْلَٰٓئِكَ لَهُمۡ عَذَابٌ عَظِيمٞ

105. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) እንደነዚያ ግልጽ ተዐምራት ከመጣላቸው በኋላ እንደተለያዩትና እንደተጨቃጨቁት የመጽሐፉ ባለቤት ሰዎች አትሁኑ:: እነዚያም ለነርሱ ታላቅ ቅጣት አለባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
106 : 3

يَوۡمَ تَبۡيَضُّ وُجُوهٞ وَتَسۡوَدُّ وُجُوهٞۚ فَأَمَّا ٱلَّذِينَ ٱسۡوَدَّتۡ وُجُوهُهُمۡ أَكَفَرۡتُم بَعۡدَ إِيمَٰنِكُمۡ فَذُوقُواْ ٱلۡعَذَابَ بِمَا كُنتُمۡ تَكۡفُرُونَ

106.ያን ፊቶች የሚያበሩበትና ፊቶች የሚጠቁሩበትን የትንሳኤን ቀን አስታውሱ። እነዚያ ፊቶቻቸው የጠቆሩት ወገኖች «ከእምነታችሁ በኋላ ካዳችሁን? እግዲያዉስ ትክዱ የነበራችሁትን ነገር ቅጣቱን ቅመሱ።» ይባላሉ። info
التفاسير:

external-link copy
107 : 3

وَأَمَّا ٱلَّذِينَ ٱبۡيَضَّتۡ وُجُوهُهُمۡ فَفِي رَحۡمَةِ ٱللَّهِۖ هُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ

107. እነዚያ ፊቶቻቸው ያበሩት ወገኖች ደግሞ በአላህ ችሮታ ገነት ውስጥ ናቸው:: እነርሱ በውስጧ ዘወታሪዎች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
108 : 3

تِلۡكَ ءَايَٰتُ ٱللَّهِ نَتۡلُوهَا عَلَيۡكَ بِٱلۡحَقِّۗ وَمَا ٱللَّهُ يُرِيدُ ظُلۡمٗا لِّلۡعَٰلَمِينَ

108. እነኚህ ባንተ ላይ በእውነት የምናነባቸው የአላህ አናቅጽ ናቸው:: አላህም ለዓለማት በደልን የሚሻ አይደለም:: info
التفاسير: