Salin ng mga Kahulugan ng Marangal na Qur'an - Salin sa Wikang Amhariko ng Akademya ng Aprika

Numero ng Pahina:close

external-link copy
133 : 3

۞ وَسَارِعُوٓاْ إِلَىٰ مَغۡفِرَةٖ مِّن رَّبِّكُمۡ وَجَنَّةٍ عَرۡضُهَا ٱلسَّمَٰوَٰتُ وَٱلۡأَرۡضُ أُعِدَّتۡ لِلۡمُتَّقِينَ

133. ወደ ጌታችሁ ምህረትና ስፋቷ ሰባቱ ሰማያትንና ምድርን ያክል ወደ ሆነችው ገነት አላህን ለሚፈሩ የተዘጋጀች ስትሆን ተቻኮሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
134 : 3

ٱلَّذِينَ يُنفِقُونَ فِي ٱلسَّرَّآءِ وَٱلضَّرَّآءِ وَٱلۡكَٰظِمِينَ ٱلۡغَيۡظَ وَٱلۡعَافِينَ عَنِ ٱلنَّاسِۗ وَٱللَّهُ يُحِبُّ ٱلۡمُحۡسِنِينَ

134. ለእነዚያ በድሎትም ሆነ በችግር ጊዜ ለሚለግሱት፤ ቁጭትንም ገቺዎች፤ ለሰዎችም ይቅርታ አድራጊዎች ለሆኑት፤ አላህ በጎ ሰሪዎችን ሁሉ ይወዳልና:: info
التفاسير:

external-link copy
135 : 3

وَٱلَّذِينَ إِذَا فَعَلُواْ فَٰحِشَةً أَوۡ ظَلَمُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ ذَكَرُواْ ٱللَّهَ فَٱسۡتَغۡفَرُواْ لِذُنُوبِهِمۡ وَمَن يَغۡفِرُ ٱلذُّنُوبَ إِلَّا ٱللَّهُ وَلَمۡ يُصِرُّواْ عَلَىٰ مَا فَعَلُواْ وَهُمۡ يَعۡلَمُونَ

135. ለእነዚያም መጥፎ ስራን በሰሩ ወይም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ አላህን የሚያስታውሱና ለኃጢአቶቻቸው ምህረትን የሚለምኑ ለሆኑት ተደግሳለች:: ከአላህ ሌላ ኃጢአቶችን የሚምር ማን ነው? (አንድም የለም::) በስህተት በሰሩት ላይ እነርሱ የሚያውቁ ሲሆኑ የማይዘወትሩ ለሆኑት ሁሉ ተደግሳለች:: info
التفاسير:

external-link copy
136 : 3

أُوْلَٰٓئِكَ جَزَآؤُهُم مَّغۡفِرَةٞ مِّن رَّبِّهِمۡ وَجَنَّٰتٞ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَاۚ وَنِعۡمَ أَجۡرُ ٱلۡعَٰمِلِينَ

136. እነዚያ ምንዳቸው ከጌታቸው ምህረትና በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ በስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶችም ናቸው:: የመልካም ሰሪዎች ሁሉ ምንዳ የሆነችው ገነት ምንኛ አማረች! info
التفاسير:

external-link copy
137 : 3

قَدۡ خَلَتۡ مِن قَبۡلِكُمۡ سُنَنٞ فَسِيرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَٱنظُرُواْ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلۡمُكَذِّبِينَ

137. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ከእናንተ በፊት በእርግጥ ብዙ አልፈዋል። በምድር ላይ ሂዱና ያስተባባዮች ፍፃሜ እንዴት እንደነበረ ተመልከቱ። info
التفاسير:

external-link copy
138 : 3

هَٰذَا بَيَانٞ لِّلنَّاسِ وَهُدٗى وَمَوۡعِظَةٞ لِّلۡمُتَّقِينَ

138. ይህ ቁርኣን ለሰዎች ሁሉ ማብራርያ፤ ለጥንቁቆችም መመሪያና ገሳጭ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
139 : 3

وَلَا تَهِنُواْ وَلَا تَحۡزَنُواْ وَأَنتُمُ ٱلۡأَعۡلَوۡنَ إِن كُنتُم مُّؤۡمِنِينَ

139. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) እናንተ የበላዮች ናችሁና ትክክለኛ አማኞች እንደሆናችሁ አትድከሙ (አትስነፉ)። አትዘኑም። info
التفاسير:

external-link copy
140 : 3

إِن يَمۡسَسۡكُمۡ قَرۡحٞ فَقَدۡ مَسَّ ٱلۡقَوۡمَ قَرۡحٞ مِّثۡلُهُۥۚ وَتِلۡكَ ٱلۡأَيَّامُ نُدَاوِلُهَا بَيۡنَ ٱلنَّاسِ وَلِيَعۡلَمَ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَيَتَّخِذَ مِنكُمۡ شُهَدَآءَۗ وَٱللَّهُ لَا يُحِبُّ ٱلظَّٰلِمِينَ

140. አማኞች ሆይ! የመቁስል ጉዳት ቢያገኛችሁ ሌሎች ህዝቦችም መሰሉ የመቁሰል ጉዳት አግኝቷቸዋል። እንዲሁ ቀናትን በሰዎች መካከል እናፈራርቃቸዋለን:: አላህ እነዚያን በትክክል በሱ ያመኑትን ሊለይና ከእናንተም መካከል ሰማዕታትን ሊመርጥ እንዲህ አይነት ቀናት እንዲፈራረቁ ያደርጋል:: አላህም በዳዮችን ሁሉ አይወድምና:: info
التفاسير: