Salin ng mga Kahulugan ng Marangal na Qur'an - Salin sa Wikang Amhariko ng Akademya ng Aprika

Numero ng Pahina:close

external-link copy
166 : 3

وَمَآ أَصَٰبَكُمۡ يَوۡمَ ٱلۡتَقَى ٱلۡجَمۡعَانِ فَبِإِذۡنِ ٱللَّهِ وَلِيَعۡلَمَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ

166. (የመልዕክተኛችን ባልደረቦች ሆይ!) ያ ሁለት ቡድኖች በተጋጠሙ ቀን የደረሰባችሁ በአላህ ፈቃድ ብቻ ነው:: የአማኞችን አቋም ሊፈትንና ማንነታቸውን ሊገልጽ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
167 : 3

وَلِيَعۡلَمَ ٱلَّذِينَ نَافَقُواْۚ وَقِيلَ لَهُمۡ تَعَالَوۡاْ قَٰتِلُواْ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ أَوِ ٱدۡفَعُواْۖ قَالُواْ لَوۡ نَعۡلَمُ قِتَالٗا لَّٱتَّبَعۡنَٰكُمۡۗ هُمۡ لِلۡكُفۡرِ يَوۡمَئِذٍ أَقۡرَبُ مِنۡهُمۡ لِلۡإِيمَٰنِۚ يَقُولُونَ بِأَفۡوَٰهِهِم مَّا لَيۡسَ فِي قُلُوبِهِمۡۚ وَٱللَّهُ أَعۡلَمُ بِمَا يَكۡتُمُونَ

167. እነዚያንም የነፈቁትንና «ኑ በአላህ መንገድ ተጋደሉ ወይም ተከላከሉ።» የተባሉትን ሊገልጽ ነው ይህን ያደረገው። አስመሳዮቹም «ውጊያን ብናውቅ ኖሮ በተከተልናችሁ ነበር።» አሉ:: እነርሱም ያን ጊዜ ከእምነት ይልቅ ወደ ክህደት የቀረቡ ናቸው:: በልቦቻቸው የሌለውን በአፎቻቸው ይናገራሉ። አላህም የሚደብቁትን ሁሉ አዋቂ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
168 : 3

ٱلَّذِينَ قَالُواْ لِإِخۡوَٰنِهِمۡ وَقَعَدُواْ لَوۡ أَطَاعُونَا مَا قُتِلُواْۗ قُلۡ فَٱدۡرَءُواْ عَنۡ أَنفُسِكُمُ ٱلۡمَوۡتَ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ

168. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚህ ከትግል ወደ ኋላ የቀሩ ሲሆኑ ለወንድሞቻቸው «እኛን በታዘዙን ኖሮ ባልተገደሉ ነበር።» ያሉ ናቸው:: «እውነተኞችም ከሆናችሁ እስቲ ከነፍሶቻችሁ ላይ ሞትን ገፍትሩ።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
169 : 3

وَلَا تَحۡسَبَنَّ ٱلَّذِينَ قُتِلُواْ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ أَمۡوَٰتَۢاۚ بَلۡ أَحۡيَآءٌ عِندَ رَبِّهِمۡ يُرۡزَقُونَ

169. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያንም በአላህ መንገድ የተገደሉትን ሰማዕታት ሙታን አድርገህ አትገምታቸው:: በእርግጥ እነርሱ ጌታቸው ዘንድ ሕያው ናቸውና:: ከጌታቸው ዘንድም ሲሳይ ይለገሳሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
170 : 3

فَرِحِينَ بِمَآ ءَاتَىٰهُمُ ٱللَّهُ مِن فَضۡلِهِۦ وَيَسۡتَبۡشِرُونَ بِٱلَّذِينَ لَمۡ يَلۡحَقُواْ بِهِم مِّنۡ خَلۡفِهِمۡ أَلَّا خَوۡفٌ عَلَيۡهِمۡ وَلَا هُمۡ يَحۡزَنُونَ

170. አላህ ከችሮታው በሰጣቸው ነገር ተደሳቾች (ሲሆኑ ይመገባሉ):: በእነዚያም ከኋላቸው ገና ባልተከተሏቸውም (ባልሞቱትም እንደነርሱው ከተሰው) በእነርሱ ላይ ስጋትም ትካዜም የሌለባቸው ለመሆናቸው ይደሰታሉ። info
التفاسير:

external-link copy
171 : 3

۞ يَسۡتَبۡشِرُونَ بِنِعۡمَةٖ مِّنَ ٱللَّهِ وَفَضۡلٖ وَأَنَّ ٱللَّهَ لَا يُضِيعُ أَجۡرَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ

171. በአላህ ጸጋ፤ ችሮታና የአማኞችን ምንዳ የማያጠፋ በመሆኑም ይደሰታሉ። info
التفاسير:

external-link copy
172 : 3

ٱلَّذِينَ ٱسۡتَجَابُواْ لِلَّهِ وَٱلرَّسُولِ مِنۢ بَعۡدِ مَآ أَصَابَهُمُ ٱلۡقَرۡحُۚ لِلَّذِينَ أَحۡسَنُواْ مِنۡهُمۡ وَٱتَّقَوۡاْ أَجۡرٌ عَظِيمٌ

172. እነዚያን የመቁሰል አደጋ ከደረሰባቸው በኋላ ለአላህና ለመልዕክተኛው የታዘዙት ከእነርሱ መካከል በጎ ተግባርን ለሰሩና አላህንም ለፈሩት ሁሉ ታላቅ ምንዳ አለላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
173 : 3

ٱلَّذِينَ قَالَ لَهُمُ ٱلنَّاسُ إِنَّ ٱلنَّاسَ قَدۡ جَمَعُواْ لَكُمۡ فَٱخۡشَوۡهُمۡ فَزَادَهُمۡ إِيمَٰنٗا وَقَالُواْ حَسۡبُنَا ٱللَّهُ وَنِعۡمَ ٱلۡوَكِيلُ

173. እነዚያም ሰዎች ለእነርሱ «ጠላቶች ለእናንተ ጦርን እንደገና አከማችተዋልና ፍሯቸው።» ያሏቸውና ይህም በእምነት ላይ እምነትን የጨመረላቸው ቃላቸዉም «በቂያችን አላህ ነው፤ እርሱም ምን ያምር መጠጊያ ነው!» ያሉ ናቸው። info
التفاسير: