Salin ng mga Kahulugan ng Marangal na Qur'an - Salin sa Wikang Amhariko ng Akademya ng Aprika

Numero ng Pahina:close

external-link copy
116 : 3

إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَن تُغۡنِيَ عَنۡهُمۡ أَمۡوَٰلُهُمۡ وَلَآ أَوۡلَٰدُهُم مِّنَ ٱللَّهِ شَيۡـٔٗاۖ وَأُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلنَّارِۖ هُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ

116. እነዚያ በአላህ የካዱት ገንዘቦቻቸውና ልጆቻቸው ከአላህ ቅጣት ምንንም አያድኗቸዉም:: እነዚያም የእሳት ጓዶች ናቸው:: እነርሱም በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
117 : 3

مَثَلُ مَا يُنفِقُونَ فِي هَٰذِهِ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا كَمَثَلِ رِيحٖ فِيهَا صِرٌّ أَصَابَتۡ حَرۡثَ قَوۡمٖ ظَلَمُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ فَأَهۡلَكَتۡهُۚ وَمَا ظَلَمَهُمُ ٱللَّهُ وَلَٰكِنۡ أَنفُسَهُمۡ يَظۡلِمُونَ

117. በዚህች በቅርቢቱ ሕይወት የሚለግሱት ነገር ምሳሌው በውስጧ ውርጭ ያለባት ነፋስ ነፍሶቻቸውን የበደሉን ሕዝቦች አዝመራ እንደነካችና እንዳጠፋች ብጤ ነው። አላህም አልበደላቸዉም። ግን እነርሱ ነፍሶቻቸውን በእራሳቸው የሚበድሉ ናቸው እንጂ:: info
التفاسير:

external-link copy
118 : 3

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تَتَّخِذُواْ بِطَانَةٗ مِّن دُونِكُمۡ لَا يَأۡلُونَكُمۡ خَبَالٗا وَدُّواْ مَا عَنِتُّمۡ قَدۡ بَدَتِ ٱلۡبَغۡضَآءُ مِنۡ أَفۡوَٰهِهِمۡ وَمَا تُخۡفِي صُدُورُهُمۡ أَكۡبَرُۚ قَدۡ بَيَّنَّا لَكُمُ ٱلۡأٓيَٰتِۖ إِن كُنتُمۡ تَعۡقِلُونَ

118. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሚስጥረኛን (የልብ ወዳጅ) ከእናንተ ሌላ ከሆኑት አታድርጉ። የእናንተን ጉዳይ ከማበላሸት አይቦዝኑላችሁምና። ጉዳታችሁን ይወዳሉና (ይመኛሉ)። ለእናንተ ያላቸው ጥላቻ ከአፎቻቸው ላይ እንኳ ተገለጸ:: በልቦቻቸው የሚደብቁት ደግሞ ከዚህ ይበልጥ የከፋ ነው:: ልብ የምታደርጉ እንደሆናችሁ ለእናንተ ማብራሪያዎችን በእርግጥ ገለጽን:: info
التفاسير:

external-link copy
119 : 3

هَٰٓأَنتُمۡ أُوْلَآءِ تُحِبُّونَهُمۡ وَلَا يُحِبُّونَكُمۡ وَتُؤۡمِنُونَ بِٱلۡكِتَٰبِ كُلِّهِۦ وَإِذَا لَقُوكُمۡ قَالُوٓاْ ءَامَنَّا وَإِذَا خَلَوۡاْ عَضُّواْ عَلَيۡكُمُ ٱلۡأَنَامِلَ مِنَ ٱلۡغَيۡظِۚ قُلۡ مُوتُواْ بِغَيۡظِكُمۡۗ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمُۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ

119. እናንተ ትወዷቸዋላችሁ:: እነርሱ ግን በፍጹም አይወዷችሁም:: እናንተ በሁሉም መጽሐፍት ታምናላችሁ:: እነርሱ ግን ባገኟችሁ ጊዜ «አምነናል» ይላሉ:: ከናንተ ባገለሉ ጊዜ ግን ከቁጭታቸው የተነሳ በእናንተ ላይ ዐጥቆቻቸውን (ጣቶቻቸውን) ይነክሳሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በቁጭታችሁ ሙቱ። አላህ ልቦች የቋጠሩትን ሁሉ አዋቂ ነውና።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
120 : 3

إِن تَمۡسَسۡكُمۡ حَسَنَةٞ تَسُؤۡهُمۡ وَإِن تُصِبۡكُمۡ سَيِّئَةٞ يَفۡرَحُواْ بِهَاۖ وَإِن تَصۡبِرُواْ وَتَتَّقُواْ لَا يَضُرُّكُمۡ كَيۡدُهُمۡ شَيۡـًٔاۗ إِنَّ ٱللَّهَ بِمَا يَعۡمَلُونَ مُحِيطٞ

120. ደግ ነገር ብታገኙ ይከፋቸዋል:: መጥፎ ነገር ቢደርስባችሁ ግን በሷ ይደሰታሉ:: ከታገሳችሁና አላህን ከፈራችሁ ተንኮላቸው ምንም አይጎዳችሁም:: አላህ ለሚሰሩት ሁሉ በዕውቀቱ ከባቢ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
121 : 3

وَإِذۡ غَدَوۡتَ مِنۡ أَهۡلِكَ تُبَوِّئُ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ مَقَٰعِدَ لِلۡقِتَالِۗ وَٱللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ

121. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አማኞችን ለውጊያ ስፍራዎች የምታዘጋጅ ሆነህ ከቤተሰብህ በጧት በወጣህ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: አላህ ሁሉን ሰሚ ሁሉንም አዋቂ ነውና። info
التفاسير: