ශුද්ධවූ අල් කුර්ආන් අර්ථ කථනය - අම්හාරික් පරිවර්තනය - අප්‍රිකානු අකාඩමිය

පිටු අංක:close

external-link copy
270 : 2

وَمَآ أَنفَقۡتُم مِّن نَّفَقَةٍ أَوۡ نَذَرۡتُم مِّن نَّذۡرٖ فَإِنَّ ٱللَّهَ يَعۡلَمُهُۥۗ وَمَا لِلظَّٰلِمِينَ مِنۡ أَنصَارٍ

270. ከምጽዋት ማንኛውንም የለገሳችሁትን ወይም ከስለት የተሳላችሁትን አላህ ጠንቅቆ ያውቀዋል:: ለበዳዮች (ግፈኞች) ሁሉ ምንም አይነት ረዳቶች የሏቸዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
271 : 2

إِن تُبۡدُواْ ٱلصَّدَقَٰتِ فَنِعِمَّا هِيَۖ وَإِن تُخۡفُوهَا وَتُؤۡتُوهَا ٱلۡفُقَرَآءَ فَهُوَ خَيۡرٞ لَّكُمۡۚ وَيُكَفِّرُ عَنكُم مِّن سَيِّـَٔاتِكُمۡۗ وَٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ خَبِيرٞ

271. ምጽዋቶችን ብትገልጹ እርሷ ምንኛ መልካም ተግባር ናት:: ብትደብቋትና ለድሆች ብትሰጧት እርሱ ለእናንተ በላጭ ነው:: ከኃጢአቶቻችሁ ከእናንተ ያብሳል:: አላህ በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
272 : 2

۞ لَّيۡسَ عَلَيۡكَ هُدَىٰهُمۡ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ يَهۡدِي مَن يَشَآءُۗ وَمَا تُنفِقُواْ مِنۡ خَيۡرٖ فَلِأَنفُسِكُمۡۚ وَمَا تُنفِقُونَ إِلَّا ٱبۡتِغَآءَ وَجۡهِ ٱللَّهِۚ وَمَا تُنفِقُواْ مِنۡ خَيۡرٖ يُوَفَّ إِلَيۡكُمۡ وَأَنتُمۡ لَا تُظۡلَمُونَ

272. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱን ማቅናት ባንተ ላይ ግዴታ የለብህም:: አላህ ግን የሚሻውን ሰው ያቀናል:: የምትለግሱት ገንዘብ ሁሉ ምንዳው ለነፍሶቻችሁ ብቻ ነው:: የአላህን ውዴታውን በመፈለግ እንጂ ምንንም አትለግሱ:: ከገንዘብም የምትለግሱት ሁሉ ምንዳው ወደ እናንተ ይሞላል:: እናንተም ቅንጣት ያህል አትበደሉም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
273 : 2

لِلۡفُقَرَآءِ ٱلَّذِينَ أُحۡصِرُواْ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ لَا يَسۡتَطِيعُونَ ضَرۡبٗا فِي ٱلۡأَرۡضِ يَحۡسَبُهُمُ ٱلۡجَاهِلُ أَغۡنِيَآءَ مِنَ ٱلتَّعَفُّفِ تَعۡرِفُهُم بِسِيمَٰهُمۡ لَا يَسۡـَٔلُونَ ٱلنَّاسَ إِلۡحَافٗاۗ وَمَا تُنفِقُواْ مِنۡ خَيۡرٖ فَإِنَّ ٱللَّهَ بِهِۦ عَلِيمٌ

273. (ምጽዋት የምትሰጡት ዘካና ልገሳ) ለእነዚያ በአላህ መንገድ በግል ሕይወታቸው ከመንቀሳቀስ (ለታገዱት) ፋታ ላጡ ድሆች ነው:: መሬት ውስጥ መጓዝ (ልመና) አይችሉም:: ከቁጥብነታቸው የተነሳ ውስጣቸውን የማያውቅ ሰው ሁሉ ሀብታሞች ናቸው ብሎ ይገምታቸዋል:: በምልክታቸው ታውቃቸዋለህ:: ሰዎችን በችክታ አይለምኑም:: ከገንዘብም የምትለግሱትን ሁሉ አላህ ሁሉን አዋቂ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
274 : 2

ٱلَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمۡوَٰلَهُم بِٱلَّيۡلِ وَٱلنَّهَارِ سِرّٗا وَعَلَانِيَةٗ فَلَهُمۡ أَجۡرُهُمۡ عِندَ رَبِّهِمۡ وَلَا خَوۡفٌ عَلَيۡهِمۡ وَلَا هُمۡ يَحۡزَنُونَ

274. እነዚያ ገንዘቦቻቸውን በሌሊትና በቀን በድብቅም ሆነ በግልጽ የሚለግሱ ሰዎች ሁሉ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ዋጋቸው ይስ-ሰጣቸዋል:: በእነርሱም ላይ ምንም ይደርስብናል ብለው ፍርሀት የለባቸዉም:: ምንም ነገር ያመልጠናል ብለው አያዝኑም፡፡ info
التفاسير: