ශුද්ධවූ අල් කුර්ආන් අර්ථ කථනය - අම්හාරික් පරිවර්තනය - අප්‍රිකානු අකාඩමිය

පිටු අංක:close

external-link copy
89 : 2

وَلَمَّا جَآءَهُمۡ كِتَٰبٞ مِّنۡ عِندِ ٱللَّهِ مُصَدِّقٞ لِّمَا مَعَهُمۡ وَكَانُواْ مِن قَبۡلُ يَسۡتَفۡتِحُونَ عَلَى ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ فَلَمَّا جَآءَهُم مَّا عَرَفُواْ كَفَرُواْ بِهِۦۚ فَلَعۡنَةُ ٱللَّهِ عَلَى ٱلۡكَٰفِرِينَ

89. ከእነርሱ ጋር ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭ የሆነ መጽሐፍ ከአላህ ዘንድ በመጣላቸው ጊዜ ከመምጣቱ በፊት በእነዚያ በካዱት ላይ ይረዱበት የነበሩ ሲሆኑ ያ ቀድሞውኑ ያውቁት የነበረ ነገር በመጣላቸው ጊዜ በእርሱ ካዱ:: እናም የአላህ እርግማን በካሐዲያን ላይ ይሁን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
90 : 2

بِئۡسَمَا ٱشۡتَرَوۡاْ بِهِۦٓ أَنفُسَهُمۡ أَن يَكۡفُرُواْ بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ بَغۡيًا أَن يُنَزِّلَ ٱللَّهُ مِن فَضۡلِهِۦ عَلَىٰ مَن يَشَآءُ مِنۡ عِبَادِهِۦۖ فَبَآءُو بِغَضَبٍ عَلَىٰ غَضَبٖۚ وَلِلۡكَٰفِرِينَ عَذَابٞ مُّهِينٞ

90. ነፍሶቻቸውን የሸጡበት (የለወጡበት) ነገር ከፋ! ይኸዉም አላህ ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ ችሮታውን ማውረዱን በመመቅኘት አላህ ባወረደው ነገር መካዳቸው ነው:: እናም የአላህን ቁጣ በተደጋጋሚ አትርፈዋል:: ለካሐዲያንም አዋራጅ ቅጣት አለባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
91 : 2

وَإِذَا قِيلَ لَهُمۡ ءَامِنُواْ بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ قَالُواْ نُؤۡمِنُ بِمَآ أُنزِلَ عَلَيۡنَا وَيَكۡفُرُونَ بِمَا وَرَآءَهُۥ وَهُوَ ٱلۡحَقُّ مُصَدِّقٗا لِّمَا مَعَهُمۡۗ قُلۡ فَلِمَ تَقۡتُلُونَ أَنۢبِيَآءَ ٱللَّهِ مِن قَبۡلُ إِن كُنتُم مُّؤۡمِنِينَ

91. «አላህ ባወረደው እመኑ» በተባሉ ጊዜ «በእኛ ላይ በተወረደው መጽሐፍ ብቻ እናምናለን» ይላሉ:: ከእርሱ ኋላ የመጣው ቁርኣን ምንም እንኳን ከእነርሱ ጋር ላለው መጽሐፍ አረጋጋጭና ትክክለኛ የሆነ ቢሆንም ይክዳሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ትክክለኛ አማኞች ከሆናችሁ ከአሁን በፊት የአላህን ነብያትን ለምን ገደላችሁ?» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
92 : 2

۞ وَلَقَدۡ جَآءَكُم مُّوسَىٰ بِٱلۡبَيِّنَٰتِ ثُمَّ ٱتَّخَذۡتُمُ ٱلۡعِجۡلَ مِنۢ بَعۡدِهِۦ وَأَنتُمۡ ظَٰلِمُونَ

92. ሙሳ በግልጽ መረጃ ታጅቦ ወደ እናንተ መጥቶ ነበር:: ግን እርሱ በሌለበት ወይፈንን አምላክ አደረጋችሁ:: አጥፊዎች ነበራችሁ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
93 : 2

وَإِذۡ أَخَذۡنَا مِيثَٰقَكُمۡ وَرَفَعۡنَا فَوۡقَكُمُ ٱلطُّورَ خُذُواْ مَآ ءَاتَيۡنَٰكُم بِقُوَّةٖ وَٱسۡمَعُواْۖ قَالُواْ سَمِعۡنَا وَعَصَيۡنَا وَأُشۡرِبُواْ فِي قُلُوبِهِمُ ٱلۡعِجۡلَ بِكُفۡرِهِمۡۚ قُلۡ بِئۡسَمَا يَأۡمُرُكُم بِهِۦٓ إِيمَٰنُكُمۡ إِن كُنتُم مُّؤۡمِنِينَ

93. የጡርን ጋራ ከበላያችሁ በማንሳት (በተውራት ሕግ እንደትሰሩ) ቃል ኪዳናችሁን በያዝን ጊዜ (የሆነውን አስታውሱ):: «የሰጠናችሁን በጽናት ያዙ:: ያልነውንም ስሙ።» አልን:: «ሰማን ግን አመጽን» አሉ:: የወይፈኑም ውዴታ በክህደታቸው ምክንያት በልቦቻቸው ውስጥ ገብቷል:: «ትክክለኛ አማኞች እንደሆናችሁ እምነታችሁ የሚያዛችሁ ነገር የከፋ ነው።» በላቸው። info
التفاسير: