የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ

የገፅ ቁጥር:close

external-link copy
50 : 17

۞ قُلۡ كُونُواْ حِجَارَةً أَوۡ حَدِيدًا

50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (እንዲህ) በላቸው: «ድንጋዮች ወይም ብረትም ሁኑ፤ info
التفاسير:

external-link copy
51 : 17

أَوۡ خَلۡقٗا مِّمَّا يَكۡبُرُ فِي صُدُورِكُمۡۚ فَسَيَقُولُونَ مَن يُعِيدُنَاۖ قُلِ ٱلَّذِي فَطَرَكُمۡ أَوَّلَ مَرَّةٖۚ فَسَيُنۡغِضُونَ إِلَيۡكَ رُءُوسَهُمۡ وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هُوَۖ قُلۡ عَسَىٰٓ أَن يَكُونَ قَرِيبٗا

51. ወይም በልቦቻቸሁ ውስጥ የሚተልቅን ፍጥረትም ሁኑ (መቀስቀሳችሁ አይቀርም።)» «የሚመልሰንም ማነው?» ይላሉም። «ያ በመጀመሪያ ጊዜ የፈጠራችሁ ነው።» በላቸው:: ወደ አንተም ራሶቻቸውን ይነቀንቃሉ። «እርሱም መቼ ነው?» ይላሉም:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እንዲህ) በላቸው: «እርሱ በቅርብ ቀን ሊሆን ይችላል። info
التفاسير:

external-link copy
52 : 17

يَوۡمَ يَدۡعُوكُمۡ فَتَسۡتَجِيبُونَ بِحَمۡدِهِۦ وَتَظُنُّونَ إِن لَّبِثۡتُمۡ إِلَّا قَلِيلٗا

52. «እርሱም የሚጠራችሁንና አላህን አመስጋኞቹ ሆናችሁ ጥሪውን የምትቀበሉበት፤ ጥቂትን ቀናት እንጂ ያልቆያችሁ መሆናችሁን የምትጠራጠሩበት ቀን ነው።» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
53 : 17

وَقُل لِّعِبَادِي يَقُولُواْ ٱلَّتِي هِيَ أَحۡسَنُۚ إِنَّ ٱلشَّيۡطَٰنَ يَنزَغُ بَيۡنَهُمۡۚ إِنَّ ٱلشَّيۡطَٰنَ كَانَ لِلۡإِنسَٰنِ عَدُوّٗا مُّبِينٗا

53. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለባሮቼም ንገራቸው:: መልካም የሆነችውን ቃል ብቻ ይናገሩ:: ሰይጣን በመካከላቸው ያበላሻልና:: ሰይጣን ለሰው ልጆች ግልጽ ጠላት ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
54 : 17

رَّبُّكُمۡ أَعۡلَمُ بِكُمۡۖ إِن يَشَأۡ يَرۡحَمۡكُمۡ أَوۡ إِن يَشَأۡ يُعَذِّبۡكُمۡۚ وَمَآ أَرۡسَلۡنَٰكَ عَلَيۡهِمۡ وَكِيلٗا

54. (ሰዎች ሆይ!) ጌታችሁ በእናንተ ሁኔታ አዋቂ ነው:: ቢፈልግ ያዝንላችኋል፤ ቢፈልግም ይቀጣችኃል። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእነርሱ ላይ ሀላፊ ሆነህ አላክንህም:: አታስገድዳቸዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
55 : 17

وَرَبُّكَ أَعۡلَمُ بِمَن فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۗ وَلَقَدۡ فَضَّلۡنَا بَعۡضَ ٱلنَّبِيِّـۧنَ عَلَىٰ بَعۡضٖۖ وَءَاتَيۡنَا دَاوُۥدَ زَبُورٗا

55. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በሰማያትና በምድር ያለውን ሁሉ አዋቂ ነው:: ከፊሉን ነብያት በከፊሉ ላይ አብልጠናል:: ዳውድንም ዘቡርን ሰጥተነዋል:: info
التفاسير:

external-link copy
56 : 17

قُلِ ٱدۡعُواْ ٱلَّذِينَ زَعَمۡتُم مِّن دُونِهِۦ فَلَا يَمۡلِكُونَ كَشۡفَ ٱلضُّرِّ عَنكُمۡ وَلَا تَحۡوِيلًا

56. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በለቸው (ጣዖታዊያን ሆይ!) « እነዚያን ከእርሱ ሌላ አማልዕክት የምትሏቸውን እስቲ ጥሯቸው:: ከናንተም ላይ ጉዳትን ማስወገድን ወደ ሌላ ማዞርንም አይችሉም።»። info
التفاسير:

external-link copy
57 : 17

أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ يَدۡعُونَ يَبۡتَغُونَ إِلَىٰ رَبِّهِمُ ٱلۡوَسِيلَةَ أَيُّهُمۡ أَقۡرَبُ وَيَرۡجُونَ رَحۡمَتَهُۥ وَيَخَافُونَ عَذَابَهُۥٓۚ إِنَّ عَذَابَ رَبِّكَ كَانَ مَحۡذُورٗا

57. እነዚያ እነርሱ የሚገዟቸው ማንኛቸዉም (ወደ አላህ) በጣም ቀራቢያቸው እንኳን ለራሳቸው ወደ ጌታቸው መቃረቢያን ሥራ ይፈልጋሉ:: እዝነቱንም ይከጅላሉ:: ቅጣቱንም ይፈራሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህ ቅጣት የሚፈራ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
58 : 17

وَإِن مِّن قَرۡيَةٍ إِلَّا نَحۡنُ مُهۡلِكُوهَا قَبۡلَ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ أَوۡ مُعَذِّبُوهَا عَذَابٗا شَدِيدٗاۚ كَانَ ذَٰلِكَ فِي ٱلۡكِتَٰبِ مَسۡطُورٗا

58. አንዲትም ከተማ የለችም እኛ ከትንሳኤ ቀን በፊት አጥፊዎችዋ ወይም ብርቱን ቅጣት ቀጭዎችዋ ብንሆን እንጂ:: ይህም በመጽሐፍ የተጻፈ ነው:: info
التفاسير: