የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ

የገፅ ቁጥር:close

external-link copy
87 : 17

إِلَّا رَحۡمَةٗ مِّن رَّبِّكَۚ إِنَّ فَضۡلَهُۥ كَانَ عَلَيۡكَ كَبِيرٗا

87. ግን ከጌታህ በሆነው እዝነት ጠበቅነው:: ችሮታው ባንተ ላይ ታላቅ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
88 : 17

قُل لَّئِنِ ٱجۡتَمَعَتِ ٱلۡإِنسُ وَٱلۡجِنُّ عَلَىٰٓ أَن يَأۡتُواْ بِمِثۡلِ هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانِ لَا يَأۡتُونَ بِمِثۡلِهِۦ وَلَوۡ كَانَ بَعۡضُهُمۡ لِبَعۡضٖ ظَهِيرٗا

88. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰዎችና ጋኔኖች የዚህን ቁርኣን ቢጤ በማምጣት ላይ ቢሰበሰቡና ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳት ቢሆኑም እንኳ ብጤውን አያመጡም።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
89 : 17

وَلَقَدۡ صَرَّفۡنَا لِلنَّاسِ فِي هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانِ مِن كُلِّ مَثَلٖ فَأَبَىٰٓ أَكۡثَرُ ٱلنَّاسِ إِلَّا كُفُورٗا

89. በዚህም ቁርኣን ውስጥ ከምሳሌው ሁሉ ለሰዎች በእርግጥ መላልሰን አብራራን:: አብዛኞቹም ሰዎች ክህደትን እንጂ ሌላን እምቢ አሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
90 : 17

وَقَالُواْ لَن نُّؤۡمِنَ لَكَ حَتَّىٰ تَفۡجُرَ لَنَا مِنَ ٱلۡأَرۡضِ يَنۢبُوعًا

90. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አሉም: «ለእኛ ከምድር ምንጭን እስከምታፈልቅልን ድረስ ላንተ አናምንም። info
التفاسير:

external-link copy
91 : 17

أَوۡ تَكُونَ لَكَ جَنَّةٞ مِّن نَّخِيلٖ وَعِنَبٖ فَتُفَجِّرَ ٱلۡأَنۡهَٰرَ خِلَٰلَهَا تَفۡجِيرًا

91. «ወይም ከዘንባባዎችና ከወይን የሆነች አትክልት ላንተ እስከምትኖርህና በመካከሏም ጅረቶችን በብዛት እስከምታንቧቧ ድረስ info
التفاسير:

external-link copy
92 : 17

أَوۡ تُسۡقِطَ ٱلسَّمَآءَ كَمَا زَعَمۡتَ عَلَيۡنَا كِسَفًا أَوۡ تَأۡتِيَ بِٱللَّهِ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةِ قَبِيلًا

92. «ወይም እንደምትለው ከሰማይ ቁራጮችን በእኛ ላይ እስከምታወርድ ወይም አላህንና መላዕክትን በግልጽ እስከምታመጣ ድረስ info
التفاسير:

external-link copy
93 : 17

أَوۡ يَكُونَ لَكَ بَيۡتٞ مِّن زُخۡرُفٍ أَوۡ تَرۡقَىٰ فِي ٱلسَّمَآءِ وَلَن نُّؤۡمِنَ لِرُقِيِّكَ حَتَّىٰ تُنَزِّلَ عَلَيۡنَا كِتَٰبٗا نَّقۡرَؤُهُۥۗ قُلۡ سُبۡحَانَ رَبِّي هَلۡ كُنتُ إِلَّا بَشَرٗا رَّسُولٗا

93 «ወይም ከወርቅ የሆነ ቤት ላንተ እስከሚኖርህ ወይም በሰማይ እስከምትወጣ፤ ለመውጣትህም በእኛ ላይ የምናነበው የሆነን መጽሐፍ እስከምታወርድልን ድረስ ፈጽሞ አናምንልህም።» አሉ:: «ጌታዬ ጥራት ይገባው:: እኔ መልዕክተኛ (የሆንኩ) ሰው እንጂ ሌላ ነገር ነኝ እንዴ?!» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
94 : 17

وَمَا مَنَعَ ٱلنَّاسَ أَن يُؤۡمِنُوٓاْ إِذۡ جَآءَهُمُ ٱلۡهُدَىٰٓ إِلَّآ أَن قَالُوٓاْ أَبَعَثَ ٱللَّهُ بَشَرٗا رَّسُولٗا

94. ሰዎችን መሪ ቁርኣን በመጣላቸው ጊዜ በሱ ከማመን «አላህ ሰውን መልዕክተኛ አድርጎ ላከን?» ማለታቸው ብቻ እንጂ ሌላ አልከለከላቸዉም። info
التفاسير:

external-link copy
95 : 17

قُل لَّوۡ كَانَ فِي ٱلۡأَرۡضِ مَلَٰٓئِكَةٞ يَمۡشُونَ مُطۡمَئِنِّينَ لَنَزَّلۡنَا عَلَيۡهِم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ مَلَكٗا رَّسُولٗا

95. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በምድር ላይ ተረጋግተው የሚጓዙ መላእክት ቢኖሩ ኑሮ ከሰማይ የመልአክ መልዕክተኛ እናወርድላቸው እንደነበር ንገራቸው። info
التفاسير:

external-link copy
96 : 17

قُلۡ كَفَىٰ بِٱللَّهِ شَهِيدَۢا بَيۡنِي وَبَيۡنَكُمۡۚ إِنَّهُۥ كَانَ بِعِبَادِهِۦ خَبِيرَۢا بَصِيرٗا

96. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእኔና በእናንተ መካከል ላለን ልዩነት መስካሪ በአላህ በቃ:: ምክኒያቱም እርሱ ባሮቹን ጠንቅቆ አዋቂና ተመልካች ነውና።» በላቸው። info
التفاسير: