የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ

የገፅ ቁጥር:close

external-link copy
18 : 17

مَّن كَانَ يُرِيدُ ٱلۡعَاجِلَةَ عَجَّلۡنَا لَهُۥ فِيهَا مَا نَشَآءُ لِمَن نُّرِيدُ ثُمَّ جَعَلۡنَا لَهُۥ جَهَنَّمَ يَصۡلَىٰهَا مَذۡمُومٗا مَّدۡحُورٗا

18. ጊዜያዊቱን ዓለም (በሥራው) የሚፈልግ ሁሉ ለእርሱ ከእርሷ ውስጥ የፈለግነውን ጸጋ ብቻ ለምንፈልገውም ብቻ እናስቸኩልለታለን:: ከዚያም ለእርሱ ገሀነምን መኖሪያ አድርገንለታል:: ተወቃሽና ከአላህ እዝነት የተባረረ ሆኖ ይገባባታል። info
التفاسير:

external-link copy
19 : 17

وَمَنۡ أَرَادَ ٱلۡأٓخِرَةَ وَسَعَىٰ لَهَا سَعۡيَهَا وَهُوَ مُؤۡمِنٞ فَأُوْلَٰٓئِكَ كَانَ سَعۡيُهُم مَّشۡكُورٗا

19. የመጨረሻይቱን ዓለም የፈለገ እና እርሱ አማኝ ሆኖ ለእርሷ ተገቢ የሆነን ሥራ የሠራ ደግሞ እነዚህ ሥራቸው የተመሰገነ ይሆናል:: info
التفاسير:

external-link copy
20 : 17

كُلّٗا نُّمِدُّ هَٰٓؤُلَآءِ وَهَٰٓؤُلَآءِ مِنۡ عَطَآءِ رَبِّكَۚ وَمَا كَانَ عَطَآءُ رَبِّكَ مَحۡظُورًا

20. ሁሉንም እነዚህንም እነዚያንም ከጌታህ ስጦታ በዚህ ዓለም እንጨምርላቸዋለን:: የጌታህም ስጦታ በዚች ዓለም ክልክል አይደለም:: info
التفاسير:

external-link copy
21 : 17

ٱنظُرۡ كَيۡفَ فَضَّلۡنَا بَعۡضَهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٖۚ وَلَلۡأٓخِرَةُ أَكۡبَرُ دَرَجَٰتٖ وَأَكۡبَرُ تَفۡضِيلٗا

21. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ እንዴት እንዳስበለጥን ተመልከት:: የመጨረሻይቱም ሀገር በማዕረጎች በጣም የከበረችና በመብለጥም የላቀች ናት:: info
التفاسير:

external-link copy
22 : 17

لَّا تَجۡعَلۡ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ فَتَقۡعُدَ مَذۡمُومٗا مَّخۡذُولٗا

22. (የሰው ልጅ ሆይ!) ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ አታድርግ:: የተወቀስክ፤ ረዳት የሌለህ ትሆናለህና:: info
التفاسير:

external-link copy
23 : 17

۞ وَقَضَىٰ رَبُّكَ أَلَّا تَعۡبُدُوٓاْ إِلَّآ إِيَّاهُ وَبِٱلۡوَٰلِدَيۡنِ إِحۡسَٰنًاۚ إِمَّا يَبۡلُغَنَّ عِندَكَ ٱلۡكِبَرَ أَحَدُهُمَآ أَوۡ كِلَاهُمَا فَلَا تَقُل لَّهُمَآ أُفّٖ وَلَا تَنۡهَرۡهُمَا وَقُل لَّهُمَا قَوۡلٗا كَرِيمٗا

23. (የሰው ልጅ ሆይ!) ጌታህ እንዲህ ሲል አዘዘ:: እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ፤ ለወላጆቻችሁም መልካምን ሥሩ፤ ባንተ ዘንድ ሆነው ከወላጆችህ አንዳቸው ወይም ሁለታቸው እርጅናን ቢደርሱ «ኡፍ!» እንኳን አትበላቸው:: አትገላምጣቸዉም:: ለእነርሱም መልካምን ቃል ብቻ ተናገራቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
24 : 17

وَٱخۡفِضۡ لَهُمَا جَنَاحَ ٱلذُّلِّ مِنَ ٱلرَّحۡمَةِ وَقُل رَّبِّ ٱرۡحَمۡهُمَا كَمَا رَبَّيَانِي صَغِيرٗا

24. (ልጅ ሆይ!) ለሁለቱም የመተናነስ ክንፍን ዝቅ አድርግላቸው። «ጌታዬ ሆይ! በሕጻንነቴ በርህራሄ እንዳሳደጉኝ ሁሉ ለእነርሱም እዘንላቸው።» በልም። info
التفاسير:

external-link copy
25 : 17

رَّبُّكُمۡ أَعۡلَمُ بِمَا فِي نُفُوسِكُمۡۚ إِن تَكُونُواْ صَٰلِحِينَ فَإِنَّهُۥ كَانَ لِلۡأَوَّٰبِينَ غَفُورٗا

25. (ሰዎች ሆይ!) ጌታችሁ በነፍሶቻችሁ ውስጥ ያለውን ነገር ሁሉ ይበልጥ አዋቂ ነው:: ታዛዦችም ብትሆኑ ወይም ብታጠፉ እርሱ ለተመላሾች ሁሉ መሓሪ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
26 : 17

وَءَاتِ ذَا ٱلۡقُرۡبَىٰ حَقَّهُۥ وَٱلۡمِسۡكِينَ وَٱبۡنَ ٱلسَّبِيلِ وَلَا تُبَذِّرۡ تَبۡذِيرًا

26. (የሰው ልጅ ሆይ!) ለዝምድና ባለቤት ሁሉ ተገቢ መብቱን ስጥ:: ለምስኪንና ለመንገደኛም እንዲሁ መብቱን ስጥ:: (በሁሉም ነገር ላይ) ማባከንንም አታባክን:: info
التفاسير:

external-link copy
27 : 17

إِنَّ ٱلۡمُبَذِّرِينَ كَانُوٓاْ إِخۡوَٰنَ ٱلشَّيَٰطِينِۖ وَكَانَ ٱلشَّيۡطَٰنُ لِرَبِّهِۦ كَفُورٗا

27. አባካኞች የሰይጣናት ወንድሞች ናቸውና:: ሰይጣንም ለጌታው ብርቱ ከሓዲ ነው:: info
التفاسير: