Bản dịch ý nghĩa nội dung Qur'an - 阿姆哈拉语翻译:非洲学院

Số trang:close

external-link copy
234 : 2

وَٱلَّذِينَ يُتَوَفَّوۡنَ مِنكُمۡ وَيَذَرُونَ أَزۡوَٰجٗا يَتَرَبَّصۡنَ بِأَنفُسِهِنَّ أَرۡبَعَةَ أَشۡهُرٖ وَعَشۡرٗاۖ فَإِذَا بَلَغۡنَ أَجَلَهُنَّ فَلَا جُنَاحَ عَلَيۡكُمۡ فِيمَا فَعَلۡنَ فِيٓ أَنفُسِهِنَّ بِٱلۡمَعۡرُوفِۗ وَٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ خَبِيرٞ

234. (ወንዶች ሆይ!) እነዚያ ከናንተ ውስጥ የሚሞቱና ሚስቶችን የሚተው ሚስቶቻቸው በራሳቸው አራት ወር ከአስር ቀናትን ከጋብቻ ይታገሱ:: ጊዜያቸውንም በጨረሱ ጊዜ በራሳቸው ተነሳሽነት በሚፈጽሙት ሕጋዊ ተግባር በእናንተ ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም:: አላህ የምትሰሩትን ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
235 : 2

وَلَا جُنَاحَ عَلَيۡكُمۡ فِيمَا عَرَّضۡتُم بِهِۦ مِنۡ خِطۡبَةِ ٱلنِّسَآءِ أَوۡ أَكۡنَنتُمۡ فِيٓ أَنفُسِكُمۡۚ عَلِمَ ٱللَّهُ أَنَّكُمۡ سَتَذۡكُرُونَهُنَّ وَلَٰكِن لَّا تُوَاعِدُوهُنَّ سِرًّا إِلَّآ أَن تَقُولُواْ قَوۡلٗا مَّعۡرُوفٗاۚ وَلَا تَعۡزِمُواْ عُقۡدَةَ ٱلنِّكَاحِ حَتَّىٰ يَبۡلُغَ ٱلۡكِتَٰبُ أَجَلَهُۥۚ وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ يَعۡلَمُ مَا فِيٓ أَنفُسِكُمۡ فَٱحۡذَرُوهُۚ وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ حَلِيمٞ

235. (ወንዶች ሆይ!) ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች የጋብቻ (አሽሙር) ፍንጭ በመስጠታችሁ ወይም እንዲህ ዓይነቱን ሀሳብ በውስጣችሁ በማሰባችሁ ምክንያት በእናንተ ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም:: አላህ እናንተ በእርግጥ እንዲህ ዓይነቱን ሀሳብ እንደምታስተናግዱ ቀድሞውኑ ያውቃል:: ስለዚህ (አሽሙር) ፍንጭ መስጠትንና ማሰብን ፈቀደላችሁ:: ግና በሕግ የታወቀን ጨዋ ንግግር የምትነጋገሩ ካልሆናችሁ በስተቀር የተፃፈው የኢዳ ጊዜው እስከሚደርስ ድረስ ለትዳር እንደምትፈልጓቸው በሚስጥር ቃል አትግቡላቸው:: ጋብቻን ለመዋዋልም ቁርጥ ሀሳብ አታድርጉ:: አላህ በነፍሶቻችሁ ውስጥ ያለውን ሁሉን ጠንቅቆ የሚያውቅ መሆኑን እወቁ:: ተጠንቀቁም፤ አላህ መሀሪና ታጋሽ መሆኑንም እወቁ:: info
التفاسير:

external-link copy
236 : 2

لَّا جُنَاحَ عَلَيۡكُمۡ إِن طَلَّقۡتُمُ ٱلنِّسَآءَ مَا لَمۡ تَمَسُّوهُنَّ أَوۡ تَفۡرِضُواْ لَهُنَّ فَرِيضَةٗۚ وَمَتِّعُوهُنَّ عَلَى ٱلۡمُوسِعِ قَدَرُهُۥ وَعَلَى ٱلۡمُقۡتِرِ قَدَرُهُۥ مَتَٰعَۢا بِٱلۡمَعۡرُوفِۖ حَقًّا عَلَى ٱلۡمُحۡسِنِينَ

236. (ባሎች ሆይ!) ሴቶችን ግንኙነት ከማድረግ በፊት ወይም ለእነርሱ መህርን ሳትወስኑላቸው ብትፈቷቸው በእናንተ ላይ ኃጢአት የለባችሁም:: ነገር ግን ሀብታምም ደሃም እንደየአቅማቸው ይካሷቸው:: ይህ አቅምን መሰረት ያደረገ ካሳ በቅን ሰዎች ላይ የተደነገገ ህግ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
237 : 2

وَإِن طَلَّقۡتُمُوهُنَّ مِن قَبۡلِ أَن تَمَسُّوهُنَّ وَقَدۡ فَرَضۡتُمۡ لَهُنَّ فَرِيضَةٗ فَنِصۡفُ مَا فَرَضۡتُمۡ إِلَّآ أَن يَعۡفُونَ أَوۡ يَعۡفُوَاْ ٱلَّذِي بِيَدِهِۦ عُقۡدَةُ ٱلنِّكَاحِۚ وَأَن تَعۡفُوٓاْ أَقۡرَبُ لِلتَّقۡوَىٰۚ وَلَا تَنسَوُاْ ٱلۡفَضۡلَ بَيۡنَكُمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ بِمَا تَعۡمَلُونَ بَصِيرٌ

237. (ባሎች ሆይ!) ለሚስቶቻችሁ መህርን የወሰናችሁላቸው ስትሆኑ ሳትገናኟቸው በፊት ብትፈቷቸው ራሳቸው ይቅር ካላሉ ወይም ያ የጋብቻ ውል በእጁ የሆነ ባል ካላግራራ በስተቀር ከወሰናችሁት ግማሹን መስጠት ግድ ሆኖባችኋል:: ሁላችሁም ይቅር መባባላችሁ ወደ አላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው:: አንዱ ለሌላው በጎ መዋልን አይዘንጋ:: አላህም የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና:: info
التفاسير: