Bản dịch ý nghĩa nội dung Qur'an - 阿姆哈拉语翻译:非洲学院

Số trang:close

external-link copy
231 : 2

وَإِذَا طَلَّقۡتُمُ ٱلنِّسَآءَ فَبَلَغۡنَ أَجَلَهُنَّ فَأَمۡسِكُوهُنَّ بِمَعۡرُوفٍ أَوۡ سَرِّحُوهُنَّ بِمَعۡرُوفٖۚ وَلَا تُمۡسِكُوهُنَّ ضِرَارٗا لِّتَعۡتَدُواْۚ وَمَن يَفۡعَلۡ ذَٰلِكَ فَقَدۡ ظَلَمَ نَفۡسَهُۥۚ وَلَا تَتَّخِذُوٓاْ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ هُزُوٗاۚ وَٱذۡكُرُواْ نِعۡمَتَ ٱللَّهِ عَلَيۡكُمۡ وَمَآ أَنزَلَ عَلَيۡكُم مِّنَ ٱلۡكِتَٰبِ وَٱلۡحِكۡمَةِ يَعِظُكُم بِهِۦۚ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمٞ

231. (ሙስሊሞች ሆይ!) ሚስቶቻችሁን በፈታችሁ እና የኢዳ ጊዜያቸውን ለማገባደድ በቀረቡ ጊዜ በመልካም መልሷቸው:: ወይም በመልካም ሁኔታ ያለ አንድ ጉዳት አሰናብቷቸው:: ለመጉዳትም ወሰን ታልፉባቸው ዘንድ አትያዟቸው:: ይህን የሚሰራም ነፍሱን በእርግጥ በደለ:: የአላህን አናቅጽ ማላገጫ አታድርጉ:: አላህ በእናንተ ላይ የዋለውን ጸጋ፤ በእርሱ ሊገስፃችሁም ያወረደውን መጽሐፍ (ቁርኣንን) እና ጥበብንም (ሱናን) አስታውሱ:: አላህንም ፍሩ:: አላህ በሁሉ ነገር ላይ አዋቂ መሆኑንም እወቁ:: info
التفاسير:

external-link copy
232 : 2

وَإِذَا طَلَّقۡتُمُ ٱلنِّسَآءَ فَبَلَغۡنَ أَجَلَهُنَّ فَلَا تَعۡضُلُوهُنَّ أَن يَنكِحۡنَ أَزۡوَٰجَهُنَّ إِذَا تَرَٰضَوۡاْ بَيۡنَهُم بِٱلۡمَعۡرُوفِۗ ذَٰلِكَ يُوعَظُ بِهِۦ مَن كَانَ مِنكُمۡ يُؤۡمِنُ بِٱللَّهِ وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِۗ ذَٰلِكُمۡ أَزۡكَىٰ لَكُمۡ وَأَطۡهَرُۚ وَٱللَّهُ يَعۡلَمُ وَأَنتُمۡ لَا تَعۡلَمُونَ

232. ሚስቶቻችሁን በፈታችሁ እና የኢዳ ጊዜያቸውን በጨረሱ ጊዜ ጥንዶቹ በመካከላቸው ሕጋዊና ፍትሀዊ የጋራ ስምምነት ላይ ከደረሱ ባሎቻቸውን ከማግባት አታስተጓጉሏቸው:: ይህ ከናንተ መካከል በአላህና በመጨረሻ ቀን የሚያምን ሁሉ ይገሰጽበታል:: ይህ ለእናንተ በላጭና አጥሪ ነው:: አላህ ያውቃል:: እናንተ ግን አታውቁም:: info
التفاسير:

external-link copy
233 : 2

۞ وَٱلۡوَٰلِدَٰتُ يُرۡضِعۡنَ أَوۡلَٰدَهُنَّ حَوۡلَيۡنِ كَامِلَيۡنِۖ لِمَنۡ أَرَادَ أَن يُتِمَّ ٱلرَّضَاعَةَۚ وَعَلَى ٱلۡمَوۡلُودِ لَهُۥ رِزۡقُهُنَّ وَكِسۡوَتُهُنَّ بِٱلۡمَعۡرُوفِۚ لَا تُكَلَّفُ نَفۡسٌ إِلَّا وُسۡعَهَاۚ لَا تُضَآرَّ وَٰلِدَةُۢ بِوَلَدِهَا وَلَا مَوۡلُودٞ لَّهُۥ بِوَلَدِهِۦۚ وَعَلَى ٱلۡوَارِثِ مِثۡلُ ذَٰلِكَۗ فَإِنۡ أَرَادَا فِصَالًا عَن تَرَاضٖ مِّنۡهُمَا وَتَشَاوُرٖ فَلَا جُنَاحَ عَلَيۡهِمَاۗ وَإِنۡ أَرَدتُّمۡ أَن تَسۡتَرۡضِعُوٓاْ أَوۡلَٰدَكُمۡ فَلَا جُنَاحَ عَلَيۡكُمۡ إِذَا سَلَّمۡتُم مَّآ ءَاتَيۡتُم بِٱلۡمَعۡرُوفِۗ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ بِمَا تَعۡمَلُونَ بَصِيرٞ

233. እናቶች ልጆቻቸውን ሁለት ሙሉ ዓመታትን ያጠባሉ:: ይህም ማጥባትን የተሟላ ለማድረግ ለፈለገ ሰው ነው:: በአባት ላይ ምግባቸውንና ልብሳቸውን የማቅረብ ግዴታ አለበት:: ማንም ነፍስ ከችሎታዋ በላይ አትገደድምና:: እናት በልጇ ምክኒያት ጉዳት እንዲደርስባት አይደረግም:: አባትም በልጁ ምክንያት እንዲንገላታ መሆን የለበትም:: በወራሽም ላይ የዚሁ ተመሳሳይ ሀላፊነት አለበት:: ወላጆቹ በመልካም ፈቃድ ልጁን ከጡት መነጠል (ማስጣል) ቢፈልጉ በሁለቱም መማከር በሁለቱም ላይ ኃጢአት የለባቸዉም:: ለልጆቻችሁ አጥቢዎችን ብትቀጥሩ ተስፋ የሰጣችሁትን ክፍያ በአግባቡ እስከሰጣችሁ ድረስ በማስጠባታችሁ በእናንተ ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም:: አላህን ፍሩ:: አላህ የምትሰሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች መሆኑን እወቁ፡፡ info
التفاسير: