قۇرئان كەرىم مەنىلىرىنىڭ تەرجىمىسى - ئەمھەرىيچە تەرجىمىسى - ئافرىقا ئاكادېمىيىسى

بەت نومۇرى:close

external-link copy
112 : 9

ٱلتَّٰٓئِبُونَ ٱلۡعَٰبِدُونَ ٱلۡحَٰمِدُونَ ٱلسَّٰٓئِحُونَ ٱلرَّٰكِعُونَ ٱلسَّٰجِدُونَ ٱلۡأٓمِرُونَ بِٱلۡمَعۡرُوفِ وَٱلنَّاهُونَ عَنِ ٱلۡمُنكَرِ وَٱلۡحَٰفِظُونَ لِحُدُودِ ٱللَّهِۗ وَبَشِّرِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ

112. እነርሱ ተጸፃቾች፤ ተገዢዎች፤ አመስጋኞች፤ ፆመኞች፤ (በሶላት) አጎንባሾች፤ በግንባር ተደፊዎች፤ በበጎ ሥራ አዛዦች፤ ከክፉ ከልካዮች እና የአላህንም ሕግጋት ጠባቂዎች ናቸው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ትክክለኛ አማኞችንም አብስር:: info
التفاسير:

external-link copy
113 : 9

مَا كَانَ لِلنَّبِيِّ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ أَن يَسۡتَغۡفِرُواْ لِلۡمُشۡرِكِينَ وَلَوۡ كَانُوٓاْ أُوْلِي قُرۡبَىٰ مِنۢ بَعۡدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُمۡ أَنَّهُمۡ أَصۡحَٰبُ ٱلۡجَحِيمِ

113. መልዕክተኛዉም ሆነ እነዚያ በእሱ ያመኑት ሰዎች ለአጋሪዎቹ የዝምድና ባለቤቶች ቢሆኑም እንኳ ከሓዲያን እነርሱ የእሳት ጓዶች መሆናቸው ከተገለጸላቸው በኋላ የአላህን ምሕረት ሊለምኑላቸው የሚገባ አልነበረም:: info
التفاسير:

external-link copy
114 : 9

وَمَا كَانَ ٱسۡتِغۡفَارُ إِبۡرَٰهِيمَ لِأَبِيهِ إِلَّا عَن مَّوۡعِدَةٖ وَعَدَهَآ إِيَّاهُ فَلَمَّا تَبَيَّنَ لَهُۥٓ أَنَّهُۥ عَدُوّٞ لِّلَّهِ تَبَرَّأَ مِنۡهُۚ إِنَّ إِبۡرَٰهِيمَ لَأَوَّٰهٌ حَلِيمٞ

114. ኢብራሂምም ለአባቱ ምህረትን መለመኑ ቀድሞ ገብቶለት የነበረውን ቃል ለመሙላት እንጂ ለሌላ አልነበረም:: እናም የአላህ ጠላት መሆኑ በተገለጸለት ጊዜ ከእርሱ ራቀ:: (ተወው):: ኢብራሂም በእርግጥ አልቃሻ እና ታጋሽ ነበርና። info
التفاسير:

external-link copy
115 : 9

وَمَا كَانَ ٱللَّهُ لِيُضِلَّ قَوۡمَۢا بَعۡدَ إِذۡ هَدَىٰهُمۡ حَتَّىٰ يُبَيِّنَ لَهُم مَّا يَتَّقُونَۚ إِنَّ ٱللَّهَ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمٌ

115. አላህ ህዝቦችን ካቀናቸው በኋላ የሚጠነቀቁትን ነገር እሥከሚገልጽላቸው ድረስ ሳያውቁ በሰሩት ጥፋት ጥፋተኛ የሚያደርግ ጌታ አይደለም:: አላህ በነገሩ ሁሉ አዋቂ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
116 : 9

إِنَّ ٱللَّهَ لَهُۥ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ يُحۡيِۦ وَيُمِيتُۚ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ مِن وَلِيّٖ وَلَا نَصِيرٖ

116. አላህ የሰማያትና የምድር ንግስና የእርሱ ብቻ ነው:: ህያው ያደርጋል:: ይገድላልም:: ለእናንተም ከእርሱ በስተቀር ጠባቂም ሆነ ወዳጅ የላችሁም:: info
التفاسير:

external-link copy
117 : 9

لَّقَد تَّابَ ٱللَّهُ عَلَى ٱلنَّبِيِّ وَٱلۡمُهَٰجِرِينَ وَٱلۡأَنصَارِ ٱلَّذِينَ ٱتَّبَعُوهُ فِي سَاعَةِ ٱلۡعُسۡرَةِ مِنۢ بَعۡدِ مَا كَادَ يَزِيغُ قُلُوبُ فَرِيقٖ مِّنۡهُمۡ ثُمَّ تَابَ عَلَيۡهِمۡۚ إِنَّهُۥ بِهِمۡ رَءُوفٞ رَّحِيمٞ

117. በመልዕክተኛው በስደተኞችና በረዳቶች በእነዚህም በችግሩ ጊዜ (በተቡክ ዘመቻ) ከእነርሱ የከፊሎቹ ልቦች ለመቅረት ሊዘነበሉ ከተቃረቡ በኋላ በተከተሉት ላይ አላህ በእርግጥ ጸጸታቸውን ተቀበለ:: ከዚያ ከእነርሱ ንሰሃ መግባታቸውን ተቀበለ:: እርሱ(አላህ ) ለእነርሱ ሩህሩህና አዛኝ ነውና:: info
التفاسير: