قۇرئان كەرىم مەنىلىرىنىڭ تەرجىمىسى - ئەمھەرىيچە تەرجىمىسى - ئافرىقا ئاكادېمىيىسى

بەت نومۇرى:close

external-link copy
55 : 9

فَلَا تُعۡجِبۡكَ أَمۡوَٰلُهُمۡ وَلَآ أَوۡلَٰدُهُمۡۚ إِنَّمَا يُرِيدُ ٱللَّهُ لِيُعَذِّبَهُم بِهَا فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا وَتَزۡهَقَ أَنفُسُهُمۡ وَهُمۡ كَٰفِرُونَ

55. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ገንዘቦቻቸውና ልጆቻቸው አይድነቁህ:: አላህ የሚሻው በቅርቢቱ ህይወት በእነርሱ (በገንዘቦቻቸውና በልጆቻቸው) ሊቀጣቸው ነፍሶቻቸዉም ከሓዲያን ሆነው ሊሞቱ ብቻ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
56 : 9

وَيَحۡلِفُونَ بِٱللَّهِ إِنَّهُمۡ لَمِنكُمۡ وَمَا هُم مِّنكُمۡ وَلَٰكِنَّهُمۡ قَوۡمٞ يَفۡرَقُونَ

56. እነርሱም ከናንተ ጋር ለመሆናቸው በአላህ ይምላሉ:: እነርሱ ግን ከናንተ ጋር አይደሉም:: ይልቁንም እነርሱ አጋሪዎችን ያገኘው ነገር እንዳያገኛቸው የሚፈሩ ህዝቦች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
57 : 9

لَوۡ يَجِدُونَ مَلۡجَـًٔا أَوۡ مَغَٰرَٰتٍ أَوۡ مُدَّخَلٗا لَّوَلَّوۡاْ إِلَيۡهِ وَهُمۡ يَجۡمَحُونَ

57. (ሙስሊሞች ሆይ!) መጠጊያ ወይም መሸሸጊያ ዋሻዎችን ወይም መግቢያ ቀዳዳዎችን ባገኙ ኖሮ በፍጥነት ወደ እርሱ በሸሹ ነበር:: info
التفاسير:

external-link copy
58 : 9

وَمِنۡهُم مَّن يَلۡمِزُكَ فِي ٱلصَّدَقَٰتِ فَإِنۡ أُعۡطُواْ مِنۡهَا رَضُواْ وَإِن لَّمۡ يُعۡطَوۡاْ مِنۡهَآ إِذَا هُمۡ يَسۡخَطُونَ

58. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ መካከል በምጽዋቶች ክፍፍል ዙሪያ የሚዘልፉህ ሰዎች አሉ:: ከእርሷም የሚሹትን ያህል ቢሰጡ ይደሰታሉ:: ከእርሷ ምንም ካልተሰጣቸው ግን ይጠላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
59 : 9

وَلَوۡ أَنَّهُمۡ رَضُواْ مَآ ءَاتَىٰهُمُ ٱللَّهُ وَرَسُولُهُۥ وَقَالُواْ حَسۡبُنَا ٱللَّهُ سَيُؤۡتِينَا ٱللَّهُ مِن فَضۡلِهِۦ وَرَسُولُهُۥٓ إِنَّآ إِلَى ٱللَّهِ رَٰغِبُونَ

59. እነርሱም አላህና መልእክተኛው የሰጣቸውን በወደዱ፤ «አላህ በቂያችን ነው አላህ ከችሮታው በእርግጥ ይሰጠናል፣ መልክተኛውም (ይሰጠናል) እኛ ወደ አላህ ከጃዮች ነን።» ባሉ ኖሮ ለነርሱ በተሸላቸው ነበር:: info
التفاسير:

external-link copy
60 : 9

۞ إِنَّمَا ٱلصَّدَقَٰتُ لِلۡفُقَرَآءِ وَٱلۡمَسَٰكِينِ وَٱلۡعَٰمِلِينَ عَلَيۡهَا وَٱلۡمُؤَلَّفَةِ قُلُوبُهُمۡ وَفِي ٱلرِّقَابِ وَٱلۡغَٰرِمِينَ وَفِي سَبِيلِ ٱللَّهِ وَٱبۡنِ ٱلسَّبِيلِۖ فَرِيضَةٗ مِّنَ ٱللَّهِۗ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٞ

60. ግዴታ ዘካን የሚከፈሉት ለድሆች፤ ለችግረኞች፤ በእርሷም ላይ ለሚሰሩ ሠራተኞች፤ ልቦቻቸው በኢስላም ለሚለማመዱት ወገኖች፤ ጫንቃዎችን (ባሪያዎች) ነጻ ለማውጣት፤ ባለ እዳ ለሆኑት፤ በአላህ መንገድም ለሚሰሩና (ስንቅ ላለቀበት) መንገደኛ ብቻ ነው:: ይህ ስርአት ከአላህ የተደነገገ ግዴታ ነው:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና። info
التفاسير:

external-link copy
61 : 9

وَمِنۡهُمُ ٱلَّذِينَ يُؤۡذُونَ ٱلنَّبِيَّ وَيَقُولُونَ هُوَ أُذُنٞۚ قُلۡ أُذُنُ خَيۡرٖ لَّكُمۡ يُؤۡمِنُ بِٱللَّهِ وَيُؤۡمِنُ لِلۡمُؤۡمِنِينَ وَرَحۡمَةٞ لِّلَّذِينَ ءَامَنُواْ مِنكُمۡۚ وَٱلَّذِينَ يُؤۡذُونَ رَسُولَ ٱللَّهِ لَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ

61. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ) ከአስመሳዮች መካከል ነብዩ ሙሐመድን የሚያስቸግሩና «እርሱ እኮ ወሬ ሰሚ ነው።» የሚሉ አሉ። «ለእናንተ የበጎ ወሬ ሰሚ ነው:: በአላህ ያምናል:: አማኞችንም ያምናቸዋል:: ከናንተ መካከል ለእነዚያ በአላህ ላመኑት ሰዎችም እዝነት ነው።» በላቸው:: እነዚያ የአላህን መልዕክተኛ የሚያስቸግሩ ሰዎች ሁሉ አሳማሚ ቅጣት አለባቸው። info
التفاسير: