قۇرئان كەرىم مەنىلىرىنىڭ تەرجىمىسى - ئەمھەرىيچە تەرجىمىسى - ئافرىقا ئاكادېمىيىسى

بەت نومۇرى:close

external-link copy
107 : 9

وَٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُواْ مَسۡجِدٗا ضِرَارٗا وَكُفۡرٗا وَتَفۡرِيقَۢا بَيۡنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ وَإِرۡصَادٗا لِّمَنۡ حَارَبَ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ مِن قَبۡلُۚ وَلَيَحۡلِفُنَّ إِنۡ أَرَدۡنَآ إِلَّا ٱلۡحُسۡنَىٰۖ وَٱللَّهُ يَشۡهَدُ إِنَّهُمۡ لَكَٰذِبُونَ

107. እነዚያም አማኞችን ለመጉዳት ክህደትንም ለማበረታታት በአማኞችም መካከል ለመለያየት ከአሁን በፊት አላህንና መልዕክተኛውን የተዋጋውን ሰው ለመጠባበቅ መስጊዱን የሠሩት ሰዎች ከእነርሱ ናቸው:: «መልካምን እንጂ ሌላ አልሻንም።» ሲሉ በእርግጥ ይምላሉ:: አላህ ደግሞ ውሸታሞች መሆናቸውን በእርግጥ ይመሰክራል:: info
التفاسير:

external-link copy
108 : 9

لَا تَقُمۡ فِيهِ أَبَدٗاۚ لَّمَسۡجِدٌ أُسِّسَ عَلَى ٱلتَّقۡوَىٰ مِنۡ أَوَّلِ يَوۡمٍ أَحَقُّ أَن تَقُومَ فِيهِۚ فِيهِ رِجَالٞ يُحِبُّونَ أَن يَتَطَهَّرُواْۚ وَٱللَّهُ يُحِبُّ ٱلۡمُطَّهِّرِينَ

108. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእርሱ ውስጥ በፍጹም አትስገድ:: ይልቁንም ከመጀመሪያ ቀን ይዞ በአላህ ፍራቻ ላይ የተመሠረተው (የቁባ ) መስጊድ በውስጡ ልትሰግዱበት የተገባው ነው:: በውስጡ መጥራራትን የሚወዱ ወንዶች አሉ:: አላህ ተጥራሪዎችን ይወዳል:: info
التفاسير:

external-link copy
109 : 9

أَفَمَنۡ أَسَّسَ بُنۡيَٰنَهُۥ عَلَىٰ تَقۡوَىٰ مِنَ ٱللَّهِ وَرِضۡوَٰنٍ خَيۡرٌ أَم مَّنۡ أَسَّسَ بُنۡيَٰنَهُۥ عَلَىٰ شَفَا جُرُفٍ هَارٖ فَٱنۡهَارَ بِهِۦ فِي نَارِ جَهَنَّمَۗ وَٱللَّهُ لَا يَهۡدِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلظَّٰلِمِينَ

109. አላህን በመፍራትና ውዴታውን በመፈለግ ላይ ግንቡን የመሠረተ ሰው ወይስ ጎርፍ በሸረሸረው ለመናድ በተቃረበ ገደል አፋፍ ላይ ግንቡን የመሠረተውና እርሱንም ይዞት ወደ ገሀነም እሳት ውስጥ የወደቀው ይበልጣልን? አላህ በደለኛ ሕዝቦችን አይመራም:: info
التفاسير:

external-link copy
110 : 9

لَا يَزَالُ بُنۡيَٰنُهُمُ ٱلَّذِي بَنَوۡاْ رِيبَةٗ فِي قُلُوبِهِمۡ إِلَّآ أَن تَقَطَّعَ قُلُوبُهُمۡۗ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ

110. ያ የካቡት ግንባቸው ልቦቻቸው በሞት ካልተቆራረጡ በስተቀር በልቦቻቸው ውስጥ የመጠራጠር ምክንያት ከመሆን አይወገድም:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
111 : 9

۞ إِنَّ ٱللَّهَ ٱشۡتَرَىٰ مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ أَنفُسَهُمۡ وَأَمۡوَٰلَهُم بِأَنَّ لَهُمُ ٱلۡجَنَّةَۚ يُقَٰتِلُونَ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ فَيَقۡتُلُونَ وَيُقۡتَلُونَۖ وَعۡدًا عَلَيۡهِ حَقّٗا فِي ٱلتَّوۡرَىٰةِ وَٱلۡإِنجِيلِ وَٱلۡقُرۡءَانِۚ وَمَنۡ أَوۡفَىٰ بِعَهۡدِهِۦ مِنَ ٱللَّهِۚ فَٱسۡتَبۡشِرُواْ بِبَيۡعِكُمُ ٱلَّذِي بَايَعۡتُم بِهِۦۚ وَذَٰلِكَ هُوَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡعَظِيمُ

111. አላህ ከትክክለኛ አማኞች ነፍሶቻቸውንና ገንዘቦቻቸውን ገነትን ለእነርሱ በማድረግ ገዛቸው:: በአላህ መንገድ ላይ ይጋደላሉ:: ይገድላሉም:: ይገደላሉም:: በተውራት፤ በኢንጂልና በቁርኣንም የተነገረውን ተስፋ በእርሱ ላይ አረጋገጠ:: ከአላህ የበለጠ በቃል ኪዳኑ የሚሞላ ማን ነው? (ትክክለኛ አማኞች ሆይ!) በዚያም በእርሱ በተሻሻጣችሁበት ሽያጫችሁ ተደሰቱ:: ይህ ታላቅ ዕድል ነውና:: info
التفاسير: