పవిత్ర ఖురాన్ యొక్క భావార్థాల అనువాదం - అమ్హారిక్ అనువాదం - ఆఫ్రికా అకాడమీ

పేజీ నెంబరు:close

external-link copy
38 : 3

هُنَالِكَ دَعَا زَكَرِيَّا رَبَّهُۥۖ قَالَ رَبِّ هَبۡ لِي مِن لَّدُنكَ ذُرِّيَّةٗ طَيِّبَةًۖ إِنَّكَ سَمِيعُ ٱلدُّعَآءِ

38. እዚያ ዘንድም ዘከርያ ጌታውን እንደዚህ በማለት ለመነ: «ጌታዬ ሆይ! ካንተ ዘንድ መልካም ዘርን ለእኔ ስጠኝ:: አንተ ጸሎትን ሰሚ ነህና» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
39 : 3

فَنَادَتۡهُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ وَهُوَ قَآئِمٞ يُصَلِّي فِي ٱلۡمِحۡرَابِ أَنَّ ٱللَّهَ يُبَشِّرُكَ بِيَحۡيَىٰ مُصَدِّقَۢا بِكَلِمَةٖ مِّنَ ٱللَّهِ وَسَيِّدٗا وَحَصُورٗا وَنَبِيّٗا مِّنَ ٱلصَّٰلِحِينَ

39. እርሱም በዱዓ ማድረጊያ ክፍል ቆሞ ዱዓ ሲያደርግ መላዕክት:- «አላህ በየህያ: ከአላህ በሆነ ቃል የሚያረጋግጥ፣ በላጭ፣ ከሴት ጋር የማይገናኝ ድንግልና ከደጋጎቹም አንዱ ሲሆን ያበስርሃል።» በማለት መላዕክት ጠሩት። info
التفاسير:

external-link copy
40 : 3

قَالَ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي غُلَٰمٞ وَقَدۡ بَلَغَنِيَ ٱلۡكِبَرُ وَٱمۡرَأَتِي عَاقِرٞۖ قَالَ كَذَٰلِكَ ٱللَّهُ يَفۡعَلُ مَا يَشَآءُ

40. ዘከርያም «ጌታዬ ሆይ! እኔ እርጅና የደረሰብኝ ሚስቴም መካን ስትሆን እንዴት ልጅ ይኖረኛል?» አለ። መልአኩም: «ልክ እንደዚሁ ነው። አላህ የሚሻውን ነገር ሁሉ ይሰራልና።» አለው። info
التفاسير:

external-link copy
41 : 3

قَالَ رَبِّ ٱجۡعَل لِّيٓ ءَايَةٗۖ قَالَ ءَايَتُكَ أَلَّا تُكَلِّمَ ٱلنَّاسَ ثَلَٰثَةَ أَيَّامٍ إِلَّا رَمۡزٗاۗ وَٱذۡكُر رَّبَّكَ كَثِيرٗا وَسَبِّحۡ بِٱلۡعَشِيِّ وَٱلۡإِبۡكَٰرِ

41. ዘከርያም «ጌታዬ ሆይ! ለእዚህ ነገር ምልክትን አድርግልኝ።» አለ:: «ምልክትህ ሶስት ቀን በጥቅሻ እንጂ ሰዎችን አለማናገርህ ነው:: በዚያ ጊዜ ጌታህን በብዙ አውሳ:: በማታና በጠዋትም አወድሰው።» አለው። info
التفاسير:

external-link copy
42 : 3

وَإِذۡ قَالَتِ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ يَٰمَرۡيَمُ إِنَّ ٱللَّهَ ٱصۡطَفَىٰكِ وَطَهَّرَكِ وَٱصۡطَفَىٰكِ عَلَىٰ نِسَآءِ ٱلۡعَٰلَمِينَ

42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መላእክትም ባሉ ጊዜ: «መርየም ሆይ! አላህ በእርግጥ መረጠሸ:: ከነውሮች ሁሉ አጸዳሸ:: ከዓለማት ሴቶችም መካከል መረጠሸ። info
التفاسير:

external-link copy
43 : 3

يَٰمَرۡيَمُ ٱقۡنُتِي لِرَبِّكِ وَٱسۡجُدِي وَٱرۡكَعِي مَعَ ٱلرَّٰكِعِينَ

43. «መርየም ሆይ! ለጌታሽ ታዘዢ:: ስገጂም:: ከአጎንባሾች ጋርም ሁነሽ አጎንብሺ።» (ያለበትን ታሪክ ለህዝቦችህ አውሳ።) info
التفاسير:

external-link copy
44 : 3

ذَٰلِكَ مِنۡ أَنۢبَآءِ ٱلۡغَيۡبِ نُوحِيهِ إِلَيۡكَۚ وَمَا كُنتَ لَدَيۡهِمۡ إِذۡ يُلۡقُونَ أَقۡلَٰمَهُمۡ أَيُّهُمۡ يَكۡفُلُ مَرۡيَمَ وَمَا كُنتَ لَدَيۡهِمۡ إِذۡ يَخۡتَصِمُونَ

44.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ታሪክ ወደ አንተ ከምናወርደው ከሩቅ ወሬ ነው:: መርየምን ማን እንደሚያሳድግ ብዕሮቻቸውን ለዕጣ በጣሉ ጊዜ አንተ እነርሱ ዘንድ አልነበርክም:: በሚከራከሩም ጊዜ እነርሱ ዘንድ አልነበርክም:: info
التفاسير:

external-link copy
45 : 3

إِذۡ قَالَتِ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ يَٰمَرۡيَمُ إِنَّ ٱللَّهَ يُبَشِّرُكِ بِكَلِمَةٖ مِّنۡهُ ٱسۡمُهُ ٱلۡمَسِيحُ عِيسَى ٱبۡنُ مَرۡيَمَ وَجِيهٗا فِي ٱلدُّنۡيَا وَٱلۡأٓخِرَةِ وَمِنَ ٱلۡمُقَرَّبِينَ

45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መላዕክትም «መርየም ሆይ! አላህ ከእርሱ በሆነው ቃል የሚፈጠር ስሙ አል መሲህ ዒሳ የመርየም ልጅ በሚባል፤ በዚህ ዓለምም ሆነ በመጨረሻው ዓለም የተከበረና ከባለሟሎቹ አንዱ በሆነ ልጅ ያበስርሻል። (ባላት ጊዜ እዚያ ቦታ አልነበርክም) :: info
التفاسير: