పవిత్ర ఖురాన్ యొక్క భావార్థాల అనువాదం - అమ్హారిక్ అనువాదం - ఆఫ్రికా అకాడమీ

పేజీ నెంబరు:close

external-link copy
181 : 3

لَّقَدۡ سَمِعَ ٱللَّهُ قَوۡلَ ٱلَّذِينَ قَالُوٓاْ إِنَّ ٱللَّهَ فَقِيرٞ وَنَحۡنُ أَغۡنِيَآءُۘ سَنَكۡتُبُ مَا قَالُواْ وَقَتۡلَهُمُ ٱلۡأَنۢبِيَآءَ بِغَيۡرِ حَقّٖ وَنَقُولُ ذُوقُواْ عَذَابَ ٱلۡحَرِيقِ

181. አላህ የእነዚያን «አላህ ድሃ ነው እኛ ግን ከበርቴዎች ነን።» ያሉትን ሰዎች ቃል በእርግጥ ሰማ:: ያንን ያሉትንና ነብያትን ያለ ህግ መግደላቸውንም በእርግጥ እንጽፋለን:: «የማቃጠልንም ስቃይ ቅመሱ።» እንላቸዋለን። info
التفاسير:

external-link copy
182 : 3

ذَٰلِكَ بِمَا قَدَّمَتۡ أَيۡدِيكُمۡ وَأَنَّ ٱللَّهَ لَيۡسَ بِظَلَّامٖ لِّلۡعَبِيدِ

182. ያ ስቃይ እጃችሁ ባሳለፉት ስራና አላህም ለባሮቹ በዳይ ባለመሆኑ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
183 : 3

ٱلَّذِينَ قَالُوٓاْ إِنَّ ٱللَّهَ عَهِدَ إِلَيۡنَآ أَلَّا نُؤۡمِنَ لِرَسُولٍ حَتَّىٰ يَأۡتِيَنَا بِقُرۡبَانٖ تَأۡكُلُهُ ٱلنَّارُۗ قُلۡ قَدۡ جَآءَكُمۡ رُسُلٞ مِّن قَبۡلِي بِٱلۡبَيِّنَٰتِ وَبِٱلَّذِي قُلۡتُمۡ فَلِمَ قَتَلۡتُمُوهُمۡ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ

183. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ይህን ቃል የተናገሩት: «ለማንኛዉም መልዕክተኛ እሳት የምትበላው ቁርባን እስከሚያመጣልን ድረስ በሱ እንዳናምን አላህ ወደ እኛ አዝዟል።» ያሉ ናቸው:: «ብዙ መልዕክተኞች ከእኔ በፊት በግልጽ ተዓምራትና በዚያ ባላችሁት ቁርባን በእርግጥ መጥተውላችኋል:: እውነተኞች ከሆናችሁ ታዲያ ለምን ገደላቸኃቸው?» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
184 : 3

فَإِن كَذَّبُوكَ فَقَدۡ كُذِّبَ رُسُلٞ مِّن قَبۡلِكَ جَآءُو بِٱلۡبَيِّنَٰتِ وَٱلزُّبُرِ وَٱلۡكِتَٰبِ ٱلۡمُنِيرِ

184. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢያስተባብሉህም ካንተ በፊትም በግልጽ ተዐምራት፣ በጽሁፎች፣ በብሩህ መጽሐፍም የመጡ መልዕክተኞችም በእርግጥ (በእነርሱ መሰሎች) ተስተባብለዋል:: info
التفاسير:

external-link copy
185 : 3

كُلُّ نَفۡسٖ ذَآئِقَةُ ٱلۡمَوۡتِۗ وَإِنَّمَا تُوَفَّوۡنَ أُجُورَكُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۖ فَمَن زُحۡزِحَ عَنِ ٱلنَّارِ وَأُدۡخِلَ ٱلۡجَنَّةَ فَقَدۡ فَازَۗ وَمَا ٱلۡحَيَوٰةُ ٱلدُّنۡيَآ إِلَّا مَتَٰعُ ٱلۡغُرُورِ

185. ነፍስ ሁሉ ሞትን በእርግጥ ቀማሽ ናት:: ምንዳዎቻችሁንም የምትሞሉት በትንሳኤ ቀን ብቻ ነው:: ከእሳት እንዲርቅ ተደርጎ ገነት እንዲገባ የተደረገም በእርግጥ ምኞቱን አገኘ:: የቅርቢቱ ሕይወት ማታለያ እንጂ ሌላ አይደለችም:: info
التفاسير:

external-link copy
186 : 3

۞ لَتُبۡلَوُنَّ فِيٓ أَمۡوَٰلِكُمۡ وَأَنفُسِكُمۡ وَلَتَسۡمَعُنَّ مِنَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ مِن قَبۡلِكُمۡ وَمِنَ ٱلَّذِينَ أَشۡرَكُوٓاْ أَذٗى كَثِيرٗاۚ وَإِن تَصۡبِرُواْ وَتَتَّقُواْ فَإِنَّ ذَٰلِكَ مِنۡ عَزۡمِ ٱلۡأُمُورِ

186. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) በገንዘቦቻችሁና በነፍሶቻችሁ ትፈተናላችሁ:: ከእነዚያ ከናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡትም ከእነዚያ በአላህ ካጋሩትም ቡድኖች ብዙ መጥፎ ነገሮችን ትሰማላችሁ:: ብትታገሱና ብትጠነቀቁ (በጣም ጥሩ ነው።) ይህ ተግባር ከታላላቅ ነገሮች አንዱ ነው። info
التفاسير: