పవిత్ర ఖురాన్ యొక్క భావార్థాల అనువాదం - అమ్హారిక్ అనువాదం - ఆఫ్రికా అకాడమీ

పేజీ నెంబరు:close

external-link copy
122 : 3

إِذۡ هَمَّت طَّآئِفَتَانِ مِنكُمۡ أَن تَفۡشَلَا وَٱللَّهُ وَلِيُّهُمَاۗ وَعَلَى ٱللَّهِ فَلۡيَتَوَكَّلِ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ

122. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ረዳታቸው ሲሆን ከእናንተ መካከል ሁለት ቡድኖች (ወገኖች) ለመፍራት ባሰቡ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: በአላህ ላይ ብቻ አማኞች ይመኩ:: info
التفاسير:

external-link copy
123 : 3

وَلَقَدۡ نَصَرَكُمُ ٱللَّهُ بِبَدۡرٖ وَأَنتُمۡ أَذِلَّةٞۖ فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ لَعَلَّكُمۡ تَشۡكُرُونَ

123. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) በበድር ዘመቻ ዕለት እናንተ ጥቂቶች ሆናችሁ ሳለ አላህ በእርግጥ ረዳችሁ:: አላህን ታመሰግኑ ዘንድ ፍሩት:: info
التفاسير:

external-link copy
124 : 3

إِذۡ تَقُولُ لِلۡمُؤۡمِنِينَ أَلَن يَكۡفِيَكُمۡ أَن يُمِدَّكُمۡ رَبُّكُم بِثَلَٰثَةِ ءَالَٰفٖ مِّنَ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةِ مُنزَلِينَ

124. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለአማኞች (እንዲህ) በምትል ጊዜ የሆነውን አስታውስ: «ጌታችሁ በሶስት ሺ መላዕክት የተወረዱ ሲሆኑ ቢረዳችሁ አይበቃችሁምን? info
التفاسير:

external-link copy
125 : 3

بَلَىٰٓۚ إِن تَصۡبِرُواْ وَتَتَّقُواْ وَيَأۡتُوكُم مِّن فَوۡرِهِمۡ هَٰذَا يُمۡدِدۡكُمۡ رَبُّكُم بِخَمۡسَةِ ءَالَٰفٖ مِّنَ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةِ مُسَوِّمِينَ

125. «አዎን! ብትታገሱና ብትጠነቀቁ አሁኑኑ በፍጥነት ጠላቶቻችሁ ቢመጡባችሁም ጌታችሁ ምልክት ባላቸው አምስት ሺህ መላዕክት ይረዳችኋል።» info
التفاسير:

external-link copy
126 : 3

وَمَا جَعَلَهُ ٱللَّهُ إِلَّا بُشۡرَىٰ لَكُمۡ وَلِتَطۡمَئِنَّ قُلُوبُكُم بِهِۦۗ وَمَا ٱلنَّصۡرُ إِلَّا مِنۡ عِندِ ٱللَّهِ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡحَكِيمِ

126. አላህ ለእናንተ ብስራትና ልቦቻችሁ በእርሱ እንዲረኩ እንጂ እርዳታውን ለምንም አላደረገዉም:: ድልም አሸናፊና ጥበበኛ ከሆነው ከአላህ ዘንድ ብቻ እንጂ ከሌላ ከማንም የሚገኝ አይደለም:: info
التفاسير:

external-link copy
127 : 3

لِيَقۡطَعَ طَرَفٗا مِّنَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ أَوۡ يَكۡبِتَهُمۡ فَيَنقَلِبُواْ خَآئِبِينَ

127. (ድልን ያጎናፀፋችሁ) ከእነዚያ ከካዱት ከፊልን ሊቆርጥ (ሊያጠፋ) ወይም ሊያዋርዳቸውና ያፈሩ ሁነው እንዲመለሱ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
128 : 3

لَيۡسَ لَكَ مِنَ ٱلۡأَمۡرِ شَيۡءٌ أَوۡ يَتُوبَ عَلَيۡهِمۡ أَوۡ يُعَذِّبَهُمۡ فَإِنَّهُمۡ ظَٰلِمُونَ

128. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱ ራሳቸውን በዳዮች ናቸውና አላህ በእነርሱ ላይ ከፈለገም ይቅርታ ቢያደርግ ወይም በጥፋታቸው ቢቀጣቸውም ላንተ በነገሩ ላይ ምንም የለህም። info
التفاسير:

external-link copy
129 : 3

وَلِلَّهِ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۚ يَغۡفِرُ لِمَن يَشَآءُ وَيُعَذِّبُ مَن يَشَآءُۚ وَٱللَّهُ غَفُورٞ رَّحِيمٞ

129. በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውም ሁሉ የአላህ ብቻ ነው:: ለፈለገው ሰው ይምራል:: የሚፈለገውን ሰው ይቀጣል:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
130 : 3

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تَأۡكُلُواْ ٱلرِّبَوٰٓاْ أَضۡعَٰفٗا مُّضَٰعَفَةٗۖ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ لَعَلَّكُمۡ تُفۡلِحُونَ

130. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አራጣን የተነባበሩ እጥፎች ሲሆኑ አትብሉ:: ከገሀነም እሳት ትድኑም ዘንድ (አራጣን በመተው) አላህን ፍሩ:: info
التفاسير:

external-link copy
131 : 3

وَٱتَّقُواْ ٱلنَّارَ ٱلَّتِيٓ أُعِدَّتۡ لِلۡكَٰفِرِينَ

131. ያችን ለከሓዲያን የተደገሰችውን የገሀነም እሳት ተጠንቀቁ:: info
التفاسير:

external-link copy
132 : 3

وَأَطِيعُواْ ٱللَّهَ وَٱلرَّسُولَ لَعَلَّكُمۡ تُرۡحَمُونَ

132.(እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህንና መልዕክተኛውን ታዘዙ:: info
التفاسير: