పవిత్ర ఖురాన్ యొక్క భావార్థాల అనువాదం - అమ్హారిక్ అనువాదం - ఆఫ్రికా అకాడమీ

పేజీ నెంబరు:close

external-link copy
92 : 3

لَن تَنَالُواْ ٱلۡبِرَّ حَتَّىٰ تُنفِقُواْ مِمَّا تُحِبُّونَۚ وَمَا تُنفِقُواْ مِن شَيۡءٖ فَإِنَّ ٱللَّهَ بِهِۦ عَلِيمٞ

92. (ሙስሊሞች ሆይ!) ከምትወዱት ነገር እስከምትለግሱ ድረስ የበጎ ስራን ዋጋ (ገነትን) አታገኙም:: ከምንም ነገር ብትለግሱም አላህ ያውቀዋል:: info
التفاسير:

external-link copy
93 : 3

۞ كُلُّ ٱلطَّعَامِ كَانَ حِلّٗا لِّبَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ إِلَّا مَا حَرَّمَ إِسۡرَٰٓءِيلُ عَلَىٰ نَفۡسِهِۦ مِن قَبۡلِ أَن تُنَزَّلَ ٱلتَّوۡرَىٰةُۚ قُلۡ فَأۡتُواْ بِٱلتَّوۡرَىٰةِ فَٱتۡلُوهَآ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ

93. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ተውራት ከመውረዱ በፊት ኢስራኢል በራሱ ላይ እርም ካደረገው ነገር በስተቀር ምግብ ሁሉ ለኢስራኢል ልጆች የተፈቀደ ነበር። «እውነተኞች ከሆናችሁ እስኪ ተውራትን አምጡና አንብቡት።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
94 : 3

فَمَنِ ٱفۡتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ ٱلۡكَذِبَ مِنۢ بَعۡدِ ذَٰلِكَ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلظَّٰلِمُونَ

94. ከዚህ በኋላ በአላህ ላይ ውሸትን የቀጣጠፉ ሰዎች እነዚያ እነርሱ ብቻ በዳዮች (በደለኞች) ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
95 : 3

قُلۡ صَدَقَ ٱللَّهُۗ فَٱتَّبِعُواْ مِلَّةَ إِبۡرَٰهِيمَ حَنِيفٗاۖ وَمَا كَانَ مِنَ ٱلۡمُشۡرِكِينَ

95. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ እውነትን ተናገረ። (ትክክለኛ የኢብራሂም ወዳጆች ከሆናችሁ) የኢብራሂምንም መንገድ ቀጥተኛ ሲሆን ተከተሉ። ከአጋሪዎችም አልነበረም።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
96 : 3

إِنَّ أَوَّلَ بَيۡتٖ وُضِعَ لِلنَّاسِ لَلَّذِي بِبَكَّةَ مُبَارَكٗا وَهُدٗى لِّلۡعَٰلَمِينَ

96. ለሰዎች (ማምለኪያ ይሆን ዘንድ በመሬት ላይ) በመጀመሪያ የተሰራው ቤት ብሩክና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ ሲሆን ያ በበካህ (በመካ) ያለው ቤት (ካዕባ) ነው። info
التفاسير:

external-link copy
97 : 3

فِيهِ ءَايَٰتُۢ بَيِّنَٰتٞ مَّقَامُ إِبۡرَٰهِيمَۖ وَمَن دَخَلَهُۥ كَانَ ءَامِنٗاۗ وَلِلَّهِ عَلَى ٱلنَّاسِ حِجُّ ٱلۡبَيۡتِ مَنِ ٱسۡتَطَاعَ إِلَيۡهِ سَبِيلٗاۚ وَمَن كَفَرَ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَنِيٌّ عَنِ ٱلۡعَٰلَمِينَ

97. በውስጡ ግልጽ የሆኑ ተዐምራት አሉበት:: የኢብራሂምም መቆሚያ (የነበረው በዉስጡ አለ::) ወደ እርሱ የገባም ሁሉ ሰላም ይሆናል። በሰዎች ላይ ወደ እርሱ የመሄድን ጣጣ በቻለ ሁሉ ግዴታቸው ሲሆን ቤቱን ሊጎብኙት ለአላህ መብት አለው። በአላህ የካደ (ግን እራሱን እንጂ ማንንም አይጎዳም።) አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነውና። info
التفاسير:

external-link copy
98 : 3

قُلۡ يَٰٓأَهۡلَ ٱلۡكِتَٰبِ لِمَ تَكۡفُرُونَ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ وَٱللَّهُ شَهِيدٌ عَلَىٰ مَا تَعۡمَلُونَ

98.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! አላህ በምትሰሩት ሁሉ ላይ አዋቂ ሲሆን በአላህ ተዐምራቱ ለምን ትክዳላችሁ?» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
99 : 3

قُلۡ يَٰٓأَهۡلَ ٱلۡكِتَٰبِ لِمَ تَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ مَنۡ ءَامَنَ تَبۡغُونَهَا عِوَجٗا وَأَنتُمۡ شُهَدَآءُۗ وَمَا ٱللَّهُ بِغَٰفِلٍ عَمَّا تَعۡمَلُونَ

99. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እናንተ መስካሪዎች ሆናችሁ ከአላህ መንገድ መጥመሟን የምትፈልጉ ስትሆኑ ያመነን ሰው ለምን ትከለክላላችሁ? አላህም ከምትሰሩት ነገር ላይ ሁሉ ዘንጊ አይደለም።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
100 : 3

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِن تُطِيعُواْ فَرِيقٗا مِّنَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ يَرُدُّوكُم بَعۡدَ إِيمَٰنِكُمۡ كَٰفِرِينَ

100. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእነዚያ መጽሐፍትን ከተሰጡ መካከል ከፊሎቹን ብትታዘዙ ከእምነታችሁ በኋላ ወደ ክህደት ይመልሷችኋል። info
التفاسير: