அல்குர்ஆன் மொழிபெயர்ப்பு - அம்ஹாரிக் மொழிபெயர்ப்பு - ஆபிரிக்கா அகாடமி

பக்க எண்:close

external-link copy
73 : 16

وَيَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَمۡلِكُ لَهُمۡ رِزۡقٗا مِّنَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ شَيۡـٔٗا وَلَا يَسۡتَطِيعُونَ

73. ከአላህም ሌላ ከሰማያትና ከምድር ምንንም ሲሳይ የማይሰጧቸውንና ምንንም የማይችሉትን እነርሱ ያመልካሉን:: info
التفاسير:

external-link copy
74 : 16

فَلَا تَضۡرِبُواْ لِلَّهِ ٱلۡأَمۡثَالَۚ إِنَّ ٱللَّهَ يَعۡلَمُ وَأَنتُمۡ لَا تَعۡلَمُونَ

74. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለአላህ አምሳያዎችን አታድርጉ:: አላህ ያውቃል፤ እናንተ ግን አታውቁም:: info
التفاسير:

external-link copy
75 : 16

۞ ضَرَبَ ٱللَّهُ مَثَلًا عَبۡدٗا مَّمۡلُوكٗا لَّا يَقۡدِرُ عَلَىٰ شَيۡءٖ وَمَن رَّزَقۡنَٰهُ مِنَّا رِزۡقًا حَسَنٗا فَهُوَ يُنفِقُ مِنۡهُ سِرّٗا وَجَهۡرًاۖ هَلۡ يَسۡتَوُۥنَۚ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِۚ بَلۡ أَكۡثَرُهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ

75. በምንም ላይ የማይችል ሆኖ በይዞታ (አለቃ ያለበት) የሆነውን ባሪያና መልካም ሲሳይን ሰጥተነው እርሱም ከእርሱ ከሰጠነው በሚስጥርና በግልጽ የሚለግሰውን ነፃ ሰው አላህ ለጣኦትና ለእርሱ ምሳሌ አደረገ:: ሁለቱ ይስተካከላሉን? ምስጋና ሁሉ ለአላህ ይሁን:: በእውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም:: info
التفاسير:

external-link copy
76 : 16

وَضَرَبَ ٱللَّهُ مَثَلٗا رَّجُلَيۡنِ أَحَدُهُمَآ أَبۡكَمُ لَا يَقۡدِرُ عَلَىٰ شَيۡءٖ وَهُوَ كَلٌّ عَلَىٰ مَوۡلَىٰهُ أَيۡنَمَا يُوَجِّههُّ لَا يَأۡتِ بِخَيۡرٍ هَلۡ يَسۡتَوِي هُوَ وَمَن يَأۡمُرُ بِٱلۡعَدۡلِ وَهُوَ عَلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ

76. አላህ ሁለትን ወንዶች (ለከሓዲያንና ለአማኞች) ምሳሌ አደረገ:: አንደኛቸው በምንም ነገር ላይ የማይችል ዲዳ ነው:: እርሱም በጌታው ላይ ሸክም ነው:: ወደ የትም ቢያዞረው ደግ ነገር አያመጣም:: እርሱና ያ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ሆኖ በማስተካከል (ፍትህ) የሚያዘው ሰው ይስተካከላሉን? info
التفاسير:

external-link copy
77 : 16

وَلِلَّهِ غَيۡبُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَمَآ أَمۡرُ ٱلسَّاعَةِ إِلَّا كَلَمۡحِ ٱلۡبَصَرِ أَوۡ هُوَ أَقۡرَبُۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ

77. በሰማያትና በምድር ያለው ሩቅ ምስጢር የአላህ ብቻ ነው:: የሰዓቲቱም ነገር መምጣቷ እንደ ዓይን ቅጽበት እንጂ አይደለም:: ወይም ይበልጥ የቀረበ ነው:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
78 : 16

وَٱللَّهُ أَخۡرَجَكُم مِّنۢ بُطُونِ أُمَّهَٰتِكُمۡ لَا تَعۡلَمُونَ شَيۡـٔٗا وَجَعَلَ لَكُمُ ٱلسَّمۡعَ وَٱلۡأَبۡصَٰرَ وَٱلۡأَفۡـِٔدَةَ لَعَلَّكُمۡ تَشۡكُرُونَ

78. አላህ ከእናቶቻችሁ ሆዶች ምንም የማታውቁ ሆናችሁ አወጣችሁ:: ታመሰግኑ ዘንድም ለእናንተ መስሚያንና ማያዎችን ልቦችንም አደረገላችሁ (ፈጠረላችሁ):: info
التفاسير:

external-link copy
79 : 16

أَلَمۡ يَرَوۡاْ إِلَى ٱلطَّيۡرِ مُسَخَّرَٰتٖ فِي جَوِّ ٱلسَّمَآءِ مَا يُمۡسِكُهُنَّ إِلَّا ٱللَّهُۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّقَوۡمٖ يُؤۡمِنُونَ

79. ወደ በራሪዎችም በሰማይ አየር ውስጥ ለመብረር የተገሩ ሲሆኑ ከመውደቅ አላህ እንጂ ሌላ የማይዛቸው መሆናቸውን አይመለከቱምን? በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ህዝቦች ሁሉ አያሌ ተዓምራት አሉ:: info
التفاسير: