அல்குர்ஆன் மொழிபெயர்ப்பு - அம்ஹாரிக் மொழிபெயர்ப்பு - ஆபிரிக்கா அகாடமி

பக்க எண்:close

external-link copy
55 : 16

لِيَكۡفُرُواْ بِمَآ ءَاتَيۡنَٰهُمۡۚ فَتَمَتَّعُواْ فَسَوۡفَ تَعۡلَمُونَ

55. የሚያጋሩትም በሰጠናቸው ሊክዱ ነው:: ተጠቀሙም ወደፊትም የሚደርስባቸውን ታውቃላችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
56 : 16

وَيَجۡعَلُونَ لِمَا لَا يَعۡلَمُونَ نَصِيبٗا مِّمَّا رَزَقۡنَٰهُمۡۗ تَٱللَّهِ لَتُسۡـَٔلُنَّ عَمَّا كُنتُمۡ تَفۡتَرُونَ

56. ለማያውቁት ጣዖታትም ከሰጠናቸው ሲሳይ ድርሻን ያደርጋሉ:: በአላህ እምላለሁ ትቀጣጥፉት ከነበራችሁት ሁሉ በእርግጥ ትጠየቃላችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
57 : 16

وَيَجۡعَلُونَ لِلَّهِ ٱلۡبَنَٰتِ سُبۡحَٰنَهُۥ وَلَهُم مَّا يَشۡتَهُونَ

57. ለአላህ ሴቶች ልጆችን ያደርጋሉ። ጥራት ይገባው። ለእነርሱ ግን የሚፈልጉትን ያደርጋሉ። info
التفاسير:

external-link copy
58 : 16

وَإِذَا بُشِّرَ أَحَدُهُم بِٱلۡأُنثَىٰ ظَلَّ وَجۡهُهُۥ مُسۡوَدّٗا وَهُوَ كَظِيمٞ

58. ከመሀከላቸው አንዱ በሴት ልጅ (መወለድ) በተበሰረ ጊዜ እርሱ የተቆጨ ሆኖ ፊቱ ጠቁሮ ቅስሙ ይሰበራል። info
التفاسير:

external-link copy
59 : 16

يَتَوَٰرَىٰ مِنَ ٱلۡقَوۡمِ مِن سُوٓءِ مَا بُشِّرَ بِهِۦٓۚ أَيُمۡسِكُهُۥ عَلَىٰ هُونٍ أَمۡ يَدُسُّهُۥ فِي ٱلتُّرَابِۗ أَلَا سَآءَ مَا يَحۡكُمُونَ

59. ከተበሰረበት ነገር መጥፎነት በውርደት ላይ ሆኖም ቢሆን ይያዘውን? ወይስ በአፈር ውስጥ ይደብቀውን? በማለት እያምታታ ከሰዎች ይደበቃል:: የሚፈርዱት ፍርድ ምንኛ ከፋ! info
التفاسير:

external-link copy
60 : 16

لِلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ مَثَلُ ٱلسَّوۡءِۖ وَلِلَّهِ ٱلۡمَثَلُ ٱلۡأَعۡلَىٰۚ وَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ

60. ለእነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም ለማያምኑት ሰዎች ሁሉ መጥፎ መገለጫ አላቸው:: ለአላህ ግን ታላቅ መገለጫ አለው:: እርሱም ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
61 : 16

وَلَوۡ يُؤَاخِذُ ٱللَّهُ ٱلنَّاسَ بِظُلۡمِهِم مَّا تَرَكَ عَلَيۡهَا مِن دَآبَّةٖ وَلَٰكِن يُؤَخِّرُهُمۡ إِلَىٰٓ أَجَلٖ مُّسَمّٗىۖ فَإِذَا جَآءَ أَجَلُهُمۡ لَا يَسۡتَـٔۡخِرُونَ سَاعَةٗ وَلَا يَسۡتَقۡدِمُونَ

61. አላህም ሰዎችን በበደላቸው ሁሉ በቀጣቸው ኖሮ በምድር ላይ ከተንቀሳቃሽ ምንንም ባላስቀረ ነበር:: ግን እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ ያቆያቸዋል:: ጊዜያቸዉም በመጣ ወቅት አንዲትን ሰዓት አይዘገዩም፤ አይቀድሙም። info
التفاسير:

external-link copy
62 : 16

وَيَجۡعَلُونَ لِلَّهِ مَا يَكۡرَهُونَۚ وَتَصِفُ أَلۡسِنَتُهُمُ ٱلۡكَذِبَ أَنَّ لَهُمُ ٱلۡحُسۡنَىٰۚ لَا جَرَمَ أَنَّ لَهُمُ ٱلنَّارَ وَأَنَّهُم مُّفۡرَطُونَ

62. ለአላህም የሚጠሉትን ነገር ያደርጋሉ:: ለእነርሱም መልካሚቱ (ሀገር) እንዳለቻቸው በምላሶቻቸው ውሸትን ይናገራሉ:: ለእነርሱም እሳት ያለቻቸው መሆናቸውና እነርሱም ወደ እርሷ በቅድሚያ የሚነዱ መሆናቸው ጥርጥር የለበትም:: info
التفاسير:

external-link copy
63 : 16

تَٱللَّهِ لَقَدۡ أَرۡسَلۡنَآ إِلَىٰٓ أُمَمٖ مِّن قَبۡلِكَ فَزَيَّنَ لَهُمُ ٱلشَّيۡطَٰنُ أَعۡمَٰلَهُمۡ فَهُوَ وَلِيُّهُمُ ٱلۡيَوۡمَ وَلَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ

63. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ እንምላለን ካንተ በፊት ወደ ነበሩት ሕዝቦች በእርግጥ ብዙ መልዕክተኞችን ልከናል:: ሰይጣንም ለእነርሱ ስራዎቻቸውን ሸለመላቸው:: ረዳታቸው ዛሬም እርሱ ነው:: ለእነርሱም ኋላ አሳማሚ ቅጣት አላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
64 : 16

وَمَآ أَنزَلۡنَا عَلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبَ إِلَّا لِتُبَيِّنَ لَهُمُ ٱلَّذِي ٱخۡتَلَفُواْ فِيهِ وَهُدٗى وَرَحۡمَةٗ لِّقَوۡمٖ يُؤۡمِنُونَ

64. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያንን በእርሱ የተለያዩበትን ለእነርሱ ልታብራራላቸውና ለሚያምኑትም ህዝቦች መሪና እዝነት ሊሆን እንጂ ባንተ ላይ መፅሀፉን አላወረድንም። info
التفاسير: