அல்குர்ஆன் மொழிபெயர்ப்பு - அம்ஹாரிக் மொழிபெயர்ப்பு - ஆபிரிக்கா அகாடமி

பக்க எண்:close

external-link copy
88 : 16

ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَصَدُّواْ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ زِدۡنَٰهُمۡ عَذَابٗا فَوۡقَ ٱلۡعَذَابِ بِمَا كَانُواْ يُفۡسِدُونَ

88. እነዚያ በአላህ የካዱና ከአላህ መንገድ የከለከሉ ያጠፉ በነበሩት ምክንያት ቅጣትን በቅጣት ላይ ጨመርንባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
89 : 16

وَيَوۡمَ نَبۡعَثُ فِي كُلِّ أُمَّةٖ شَهِيدًا عَلَيۡهِم مِّنۡ أَنفُسِهِمۡۖ وَجِئۡنَا بِكَ شَهِيدًا عَلَىٰ هَٰٓؤُلَآءِۚ وَنَزَّلۡنَا عَلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبَ تِبۡيَٰنٗا لِّكُلِّ شَيۡءٖ وَهُدٗى وَرَحۡمَةٗ وَبُشۡرَىٰ لِلۡمُسۡلِمِينَ

89. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በየህዝቡ ሁሉ ውስጥ ከጎሳቸው በራሳቸው ላይ መስካሪን የምንቀሰቅስበትንና አንተንም በእነዚህ ሕዝቦች ላይ መስካሪ አድርገን የምናመጣብህን ቀን አስታውስ:: መጽሐፉንም ለሁሉም ነገር አብራሪ፤ መመሪያ፣ እዝነትና ለሙስሊሞች አብሳሪ ሆኖ ባንተ ላይ አወረድነው:: info
التفاسير:

external-link copy
90 : 16

۞ إِنَّ ٱللَّهَ يَأۡمُرُ بِٱلۡعَدۡلِ وَٱلۡإِحۡسَٰنِ وَإِيتَآيِٕ ذِي ٱلۡقُرۡبَىٰ وَيَنۡهَىٰ عَنِ ٱلۡفَحۡشَآءِ وَٱلۡمُنكَرِ وَٱلۡبَغۡيِۚ يَعِظُكُمۡ لَعَلَّكُمۡ تَذَكَّرُونَ

90. አላህ በማስተካከል (በፍትህ) ፤ በማሳመር (በመልካም ሥራ) እና ለዝምድና ባለቤት በመስጠትም ያዛል። ከአስከፊ (ጸያፍ ነገር) ከማመንዘር፤ ከሚጠላ ነገር ሁሉ ከመበደልም ይከለክላል:: ትገነዘቡ ዘንድ ይገሥጻችኋል:: info
التفاسير:

external-link copy
91 : 16

وَأَوۡفُواْ بِعَهۡدِ ٱللَّهِ إِذَا عَٰهَدتُّمۡ وَلَا تَنقُضُواْ ٱلۡأَيۡمَٰنَ بَعۡدَ تَوۡكِيدِهَا وَقَدۡ جَعَلۡتُمُ ٱللَّهَ عَلَيۡكُمۡ كَفِيلًاۚ إِنَّ ٱللَّهَ يَعۡلَمُ مَا تَفۡعَلُونَ

91. (ሙስሊሞች ሆይ!) ቃል ኪዳን በገባችሁ ጊዜ በአላህ ቃል ኪዳን ሙሉ:: መሓሎቻችሁንም ከአጠነከራችኋት በኋላና አላህን በእናንተ ላይ መስካሪ ያደረጋችሁ ስትሆኑ አታፍርሱ:: አላህ የምትሠሩትን ሁሉ ያውቃልና:: info
التفاسير:

external-link copy
92 : 16

وَلَا تَكُونُواْ كَٱلَّتِي نَقَضَتۡ غَزۡلَهَا مِنۢ بَعۡدِ قُوَّةٍ أَنكَٰثٗا تَتَّخِذُونَ أَيۡمَٰنَكُمۡ دَخَلَۢا بَيۡنَكُمۡ أَن تَكُونَ أُمَّةٌ هِيَ أَرۡبَىٰ مِنۡ أُمَّةٍۚ إِنَّمَا يَبۡلُوكُمُ ٱللَّهُ بِهِۦۚ وَلَيُبَيِّنَنَّ لَكُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ مَا كُنتُمۡ فِيهِ تَخۡتَلِفُونَ

92. ቃል ኪዳናችሁን በማፍረስ አንዲቱ ሕዝብ ከሌላይቱ ሕዝብ የበዛች ለመሆንዋ በመካከላችሁ መሓሎቻችሁን ለክዳት መግቢያ አድርጋችሁ የምትይዙ ስትሆኑ እንደዚያች ፈትሏን ከጠነከረ በኋላ ትርትሮች አድርጋ እንዳፈረሰችው ሴት አትሁኑ:: አላህ በእርሱ ይሞክራችኋል፤ በትንሣኤ ቀንም ትለያዩበት የነበራችሁትን ነገር በእርግጥ ያብራራላችኋል:: info
التفاسير:

external-link copy
93 : 16

وَلَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ لَجَعَلَكُمۡ أُمَّةٗ وَٰحِدَةٗ وَلَٰكِن يُضِلُّ مَن يَشَآءُ وَيَهۡدِي مَن يَشَآءُۚ وَلَتُسۡـَٔلُنَّ عَمَّا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ

93. አላህ በፈለገ ኖሮ አንዲት ሕዝብ ባደረጋችሁ ነበር:: ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያጠማል:: የሚሻውን ሰው ያቀናል:: ትሠሩት ከነበራችሁት ሁሉ በእርግጥ ትጠየቃላችሁ:: info
التفاسير: