அல்குர்ஆன் மொழிபெயர்ப்பு - அம்ஹாரிக் மொழிபெயர்ப்பு - ஆபிரிக்கா அகாடமி

பக்க எண்:close

external-link copy
111 : 16

۞ يَوۡمَ تَأۡتِي كُلُّ نَفۡسٖ تُجَٰدِلُ عَن نَّفۡسِهَا وَتُوَفَّىٰ كُلُّ نَفۡسٖ مَّا عَمِلَتۡ وَهُمۡ لَا يُظۡلَمُونَ

111. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ነፍስ ሁሉ ከራሷ ላይ የምትከራከር ሆና የምትመጣበትን ነፍስም ሁሉ የሠራችውን ዋጋ የምትቀበልበትን ቀን (አስታውስ):: እነርሱም ፈጹሞ አይበደሉም:: info
التفاسير:

external-link copy
112 : 16

وَضَرَبَ ٱللَّهُ مَثَلٗا قَرۡيَةٗ كَانَتۡ ءَامِنَةٗ مُّطۡمَئِنَّةٗ يَأۡتِيهَا رِزۡقُهَا رَغَدٗا مِّن كُلِّ مَكَانٖ فَكَفَرَتۡ بِأَنۡعُمِ ٱللَّهِ فَأَذَٰقَهَا ٱللَّهُ لِبَاسَ ٱلۡجُوعِ وَٱلۡخَوۡفِ بِمَا كَانُواْ يَصۡنَعُونَ

112. አላህ ጸጥተኛ የረካች ሲሳይዋ ሰፊ ሆኖ ከየስፍራው ይመጣላት የነበረችውንና ከዚያም በአላህ ጸጋዎች የካደችውን አላህም ይሠሩት በነበሩት ኃጢአት የረሀብንና የፍርሀትን ቅጣቶች ያቀመሳትን ከተማ ምሳሌ አደረገ:: info
التفاسير:

external-link copy
113 : 16

وَلَقَدۡ جَآءَهُمۡ رَسُولٞ مِّنۡهُمۡ فَكَذَّبُوهُ فَأَخَذَهُمُ ٱلۡعَذَابُ وَهُمۡ ظَٰلِمُونَ

113. ከእነርሱም ውስጥ የሆነ መልዕክተኛም በእርግጥ መጣላቸው:: አስተባበሉትም እነርሱም በዳዬች ሆነው ቅጣቱ ያዛቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
114 : 16

فَكُلُواْ مِمَّا رَزَقَكُمُ ٱللَّهُ حَلَٰلٗا طَيِّبٗا وَٱشۡكُرُواْ نِعۡمَتَ ٱللَّهِ إِن كُنتُمۡ إِيَّاهُ تَعۡبُدُونَ

114. አላህም ከሰጣችሁ ሲሳይ የተፈቀደና ንጹሕ ሲሆን ብሉ:: የአላህንም ጸጋ እርሱን የምትገዙት ከሆናችሁ አመስግኑት:: info
التفاسير:

external-link copy
115 : 16

إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيۡكُمُ ٱلۡمَيۡتَةَ وَٱلدَّمَ وَلَحۡمَ ٱلۡخِنزِيرِ وَمَآ أُهِلَّ لِغَيۡرِ ٱللَّهِ بِهِۦۖ فَمَنِ ٱضۡطُرَّ غَيۡرَ بَاغٖ وَلَا عَادٖ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ رَّحِيمٞ

115. በእናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትን፣ ደምን፣ የአሳማን ሥጋ፣ ያንንም በሚታረድ ጊዜ በእርሱ ላይ ከአላህ ስም ሌላ የተወሳበትን ብቻ ነው:: አመጸኛና ወሰን አላፊም ሳይሆን ከእነዚህ አንዱን ለመብላት የተገደደ ሰው ይፈቀድለታል:: አላህ መሓሪና አዛኝ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
116 : 16

وَلَا تَقُولُواْ لِمَا تَصِفُ أَلۡسِنَتُكُمُ ٱلۡكَذِبَ هَٰذَا حَلَٰلٞ وَهَٰذَا حَرَامٞ لِّتَفۡتَرُواْ عَلَى ٱللَّهِ ٱلۡكَذِبَۚ إِنَّ ٱلَّذِينَ يَفۡتَرُونَ عَلَى ٱللَّهِ ٱلۡكَذِبَ لَا يُفۡلِحُونَ

116. (ሰዎች ሆይ) በአላህ ላይ ውሸትን ልትቀጣጥፉ ምላሶቻችሁ በሚመጥኑት ውሸት «ይህ የተፈቀደ ነው፤ ይህ ደግሞ እርም ነው» አትበሉ:: እነዚያ በአላህ ላይ ውሸትን የሚቀጣጥፉ ክፍሎች በፍጹም አይድኑም:: info
التفاسير:

external-link copy
117 : 16

مَتَٰعٞ قَلِيلٞ وَلَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ

117. ጥቂት መጣቀም ብቻ አለላቸው:: ለእነርሱም አሳማሚ ቅጣት አለባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
118 : 16

وَعَلَى ٱلَّذِينَ هَادُواْ حَرَّمۡنَا مَا قَصَصۡنَا عَلَيۡكَ مِن قَبۡلُۖ وَمَا ظَلَمۡنَٰهُمۡ وَلَٰكِن كَانُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ يَظۡلِمُونَ

118. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእነዚያ አይሁድ በሆኑት ሰዎች ላይ ከአሁን በፊት ባንተ ላይ የተረክነውን ነገር እርም አድርገንባቸዋል:: እኛም አልበደልናቸዉም:: ግን ራሳቸው ነፍሶቻቸውን ይበድሉ ነበሩ:: info
التفاسير: