Tradução dos significados do Nobre Qur’an. - Tradução do amárico - Academia África

Número de página:close

external-link copy
51 : 28

۞ وَلَقَدۡ وَصَّلۡنَا لَهُمُ ٱلۡقَوۡلَ لَعَلَّهُمۡ يَتَذَكَّرُونَ

51. ይገሠጹም ዘንድ ቃልን (ቁርኣንን በያይነቱ) ለእነርሱ በእርግጥ አስከታተልን:: info
التفاسير:

external-link copy
52 : 28

ٱلَّذِينَ ءَاتَيۡنَٰهُمُ ٱلۡكِتَٰبَ مِن قَبۡلِهِۦ هُم بِهِۦ يُؤۡمِنُونَ

52. እነዚያም ከእርሱ በፊት መጽሐፍን የሰጠናቸው እነርሱ በእርሱ ያምናሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
53 : 28

وَإِذَا يُتۡلَىٰ عَلَيۡهِمۡ قَالُوٓاْ ءَامَنَّا بِهِۦٓ إِنَّهُ ٱلۡحَقُّ مِن رَّبِّنَآ إِنَّا كُنَّا مِن قَبۡلِهِۦ مُسۡلِمِينَ

53. በእነርሱ ላይ በሚነበብላቸዉም ጊዜ «በእርሱ አምነናል:: እርሱ ከጌታችን የሆነ እውነት ነው እኛ ከእርሱ በፊት ሙስሊሞች ነበርን።» ይላሉ። info
التفاسير:

external-link copy
54 : 28

أُوْلَٰٓئِكَ يُؤۡتَوۡنَ أَجۡرَهُم مَّرَّتَيۡنِ بِمَا صَبَرُواْ وَيَدۡرَءُونَ بِٱلۡحَسَنَةِ ٱلسَّيِّئَةَ وَمِمَّا رَزَقۡنَٰهُمۡ يُنفِقُونَ

54. እነዚያ በመታገሳቸው ምክኒያት ዋጋቸውን ሁለት ጊዜ ይሰጣሉ:: ክፉውንም ነገር በበጎ ምግባር ይገፈትራሉ፤ ከሰጠናቸዉም ሲሳይ ይለግሳሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
55 : 28

وَإِذَا سَمِعُواْ ٱللَّغۡوَ أَعۡرَضُواْ عَنۡهُ وَقَالُواْ لَنَآ أَعۡمَٰلُنَا وَلَكُمۡ أَعۡمَٰلُكُمۡ سَلَٰمٌ عَلَيۡكُمۡ لَا نَبۡتَغِي ٱلۡجَٰهِلِينَ

55. ውድቅንም ቃል በሰሙ ጊዜ ከእርሱ ይርቃሉ። «ለእኛ ስራዎቻችን አሉን:: ለእናንተም ስራዎቻችሁ አሉላችሁ:: ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን ባለጌዎችን አንፈልግም።» ይላሉ። info
التفاسير:

external-link copy
56 : 28

إِنَّكَ لَا تَهۡدِي مَنۡ أَحۡبَبۡتَ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ يَهۡدِي مَن يَشَآءُۚ وَهُوَ أَعۡلَمُ بِٱلۡمُهۡتَدِينَ

56. አንተ የወደድከውን ሰው ፈጽሞ አታቀናም:: ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያቀናል:: እርሱም ቅኖቹን አዋቂ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
57 : 28

وَقَالُوٓاْ إِن نَّتَّبِعِ ٱلۡهُدَىٰ مَعَكَ نُتَخَطَّفۡ مِنۡ أَرۡضِنَآۚ أَوَلَمۡ نُمَكِّن لَّهُمۡ حَرَمًا ءَامِنٗا يُجۡبَىٰٓ إِلَيۡهِ ثَمَرَٰتُ كُلِّ شَيۡءٖ رِّزۡقٗا مِّن لَّدُنَّا وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ

57. «ካንተ ጋር ቅንን መንገድ ብንከተል ከምድራችን እንባረራለን።» አሉም:: ከእኛ ዘንድ የተሰጠ ሲሳይ ሲሆን የነገሩ ሁሉ ፍሬዎች ወደ እርሱ የሚሄዱበትን ጸጥተኛ ክልል (መካን) እነርሱ አላስመቸናቸዉምን? ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም:: info
التفاسير:

external-link copy
58 : 28

وَكَمۡ أَهۡلَكۡنَا مِن قَرۡيَةِۭ بَطِرَتۡ مَعِيشَتَهَاۖ فَتِلۡكَ مَسَٰكِنُهُمۡ لَمۡ تُسۡكَن مِّنۢ بَعۡدِهِمۡ إِلَّا قَلِيلٗاۖ وَكُنَّا نَحۡنُ ٱلۡوَٰرِثِينَ

58. ከከተማም ኑሮዋን ምቾትዋን የካደችን ከተማ ያጠፋናት ብዙ ናት፤ እነዚህም ከእነርሱ በኋላ ጥቂት ጊዜ እንጂ ያልተኖረባቸው ሲሆኑ መኖሪያዎቻቸው ናቸው:: እኛም ከእነርሱ ወራሾች ነበርን። info
التفاسير:

external-link copy
59 : 28

وَمَا كَانَ رَبُّكَ مُهۡلِكَ ٱلۡقُرَىٰ حَتَّىٰ يَبۡعَثَ فِيٓ أُمِّهَا رَسُولٗا يَتۡلُواْ عَلَيۡهِمۡ ءَايَٰتِنَاۚ وَمَا كُنَّا مُهۡلِكِي ٱلۡقُرَىٰٓ إِلَّا وَأَهۡلُهَا ظَٰلِمُونَ

59. ጌታህም ከተሞችን በዋናዋ ከተማ ውስጥ አናቅጻችንን በእነርሱ ላይ የሚያነብ መልዕክተኛን እስከሚልክ ድረስ አጥፊ አልነበረም:: ከተሞችንም ባለቤቶችዋ በዳዮች ሆነው እንጂ አጥፊዎች አልነበርንም:: info
التفاسير: