Tradução dos significados do Nobre Qur’an. - Tradução do amárico - Academia África

Número de página:close

external-link copy
6 : 28

وَنُمَكِّنَ لَهُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَنُرِيَ فِرۡعَوۡنَ وَهَٰمَٰنَ وَجُنُودَهُمَا مِنۡهُم مَّا كَانُواْ يَحۡذَرُونَ

6. ለእነርሱም በምድር ላይ ልናስመች ፈርዖንን፤ ሃማንንና ሰራዊቶቻቸውንም ከእነርሱ ይፈሩት የነበሩትን ነገር ልናሳያቸው እንሻለን:: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 28

وَأَوۡحَيۡنَآ إِلَىٰٓ أُمِّ مُوسَىٰٓ أَنۡ أَرۡضِعِيهِۖ فَإِذَا خِفۡتِ عَلَيۡهِ فَأَلۡقِيهِ فِي ٱلۡيَمِّ وَلَا تَخَافِي وَلَا تَحۡزَنِيٓۖ إِنَّا رَآدُّوهُ إِلَيۡكِ وَجَاعِلُوهُ مِنَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ

7. ወደ ሙሳም እናት “አጥቢው፤ በእርሱም ላይ በፈራሽ ጊዜ በባህሩ ውስጥ ጣይው፤ አትፍሪም:: አትዘኝም:: እኛ ወዳንቺ መላሾቹና ከመልእክተኞቹም አድራጊዎቹ ነንና” ማለትን አመለከትን (አወረድን):: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 28

فَٱلۡتَقَطَهُۥٓ ءَالُ فِرۡعَوۡنَ لِيَكُونَ لَهُمۡ عَدُوّٗا وَحَزَنًاۗ إِنَّ فِرۡعَوۡنَ وَهَٰمَٰنَ وَجُنُودَهُمَا كَانُواْ خَٰطِـِٔينَ

8. የፈርዖን ቤተሰቦችም መጨረሻው ለእነርሱ ጠላት ሐዘንም ይሆን ዘንድ አነሱት:: ፈርዖንና ሃማንም ሰራዊቶቻቸዉም ኃጢአተኞች ነበሩ:: info
التفاسير:

external-link copy
9 : 28

وَقَالَتِ ٱمۡرَأَتُ فِرۡعَوۡنَ قُرَّتُ عَيۡنٖ لِّي وَلَكَۖ لَا تَقۡتُلُوهُ عَسَىٰٓ أَن يَنفَعَنَآ أَوۡ نَتَّخِذَهُۥ وَلَدٗا وَهُمۡ لَا يَشۡعُرُونَ

9. የፈርዖንም ሚስት “ለእኔም ሆነ ላንተ የዓይናችን መርጊያ ነው:: አትግደሉት:: ሊጠቅመን ወይም ልጅ ልናደርገው ይከጀላልና” አለች:: እነርሱም ፍጻሜውን የማያውቁ ሆነው (አነሱት):: info
التفاسير:

external-link copy
10 : 28

وَأَصۡبَحَ فُؤَادُ أُمِّ مُوسَىٰ فَٰرِغًاۖ إِن كَادَتۡ لَتُبۡدِي بِهِۦ لَوۡلَآ أَن رَّبَطۡنَا عَلَىٰ قَلۡبِهَا لِتَكُونَ مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ

10. የሙሳም እናት ልብ ባዶ ሆነ:: ከምእምናን ትሆን ዘንድ በልቧ ላይ ባላጠነከርን ኖሮ ልትገልጸው ቀርባ ነበር:: info
التفاسير:

external-link copy
11 : 28

وَقَالَتۡ لِأُخۡتِهِۦ قُصِّيهِۖ فَبَصُرَتۡ بِهِۦ عَن جُنُبٖ وَهُمۡ لَا يَشۡعُرُونَ

11. ለእህቱም “ተከታተይው” አለቻት:: (እርሱንም) እነርሱ የማያውቁ ሲሆኑ በሩቅ ሆና አየችው፤ info
التفاسير:

external-link copy
12 : 28

۞ وَحَرَّمۡنَا عَلَيۡهِ ٱلۡمَرَاضِعَ مِن قَبۡلُ فَقَالَتۡ هَلۡ أَدُلُّكُمۡ عَلَىٰٓ أَهۡلِ بَيۡتٖ يَكۡفُلُونَهُۥ لَكُمۡ وَهُمۡ لَهُۥ نَٰصِحُونَ

12. ወደ እናቱ ከመመለሱ በፊትም አጥቢዎችን መጥባትን በእርሱ ላይ እርም አደረግን:: እህቱም “ለእናንተ የሚያሳድግላችሁን እነርሱም ለእርሱ ቅን አገልጋዮች የሆኑን ቤተሰቦች ላመልክታችሁን?” አለችም። info
التفاسير:

external-link copy
13 : 28

فَرَدَدۡنَٰهُ إِلَىٰٓ أُمِّهِۦ كَيۡ تَقَرَّ عَيۡنُهَا وَلَا تَحۡزَنَ وَلِتَعۡلَمَ أَنَّ وَعۡدَ ٱللَّهِ حَقّٞ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ

13. ወደ እናቱም ዓይኗ እንድትረጋ እንዳታዝንም የአላህም የተስፋ ቃል እርግጥ መሆኑን እንድታውቅ መለስነው:: ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም:: info
التفاسير: