Tradução dos significados do Nobre Qur’an. - Tradução do amárico - Academia África

Número de página:close

external-link copy
14 : 28

وَلَمَّا بَلَغَ أَشُدَّهُۥ وَٱسۡتَوَىٰٓ ءَاتَيۡنَٰهُ حُكۡمٗا وَعِلۡمٗاۚ وَكَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ

14. ብርታቱንም በደረሰና በተስተካከለ ጊዜ ጥበብንና እውቀትን ሰጠነው፤ ልክ እንደዚሁም መልካም ሰሪዎችን እንመነዳለን:: info
التفاسير:

external-link copy
15 : 28

وَدَخَلَ ٱلۡمَدِينَةَ عَلَىٰ حِينِ غَفۡلَةٖ مِّنۡ أَهۡلِهَا فَوَجَدَ فِيهَا رَجُلَيۡنِ يَقۡتَتِلَانِ هَٰذَا مِن شِيعَتِهِۦ وَهَٰذَا مِنۡ عَدُوِّهِۦۖ فَٱسۡتَغَٰثَهُ ٱلَّذِي مِن شِيعَتِهِۦ عَلَى ٱلَّذِي مِنۡ عَدُوِّهِۦ فَوَكَزَهُۥ مُوسَىٰ فَقَضَىٰ عَلَيۡهِۖ قَالَ هَٰذَا مِنۡ عَمَلِ ٱلشَّيۡطَٰنِۖ إِنَّهُۥ عَدُوّٞ مُّضِلّٞ مُّبِينٞ

15. ሙሳ ከተማይቱንም ሰዎቿ በዝንጋቴ ላይ ሆነው ሳሉ ገባ:: በእርሷም ውስጥ የሚጋደሉን ሁለት ሰዎች አገኘ:: ይህ (አንዱ) ከወገኑ ነው፤ ይህ (ሌላው) ደግሞ ከጠላቱ ነው፤ ያ ከወገኑ የሆነው ሰው በዚያ ከጣላት በሆነው ሰው ላይ እርዳታን ጠየቀው:: ሙሳም በጡጫ መታው:: ገደለዉም:: “ይህ ከሰይጣን ስራ ነው:: እርሱ ግልጽ አሣሣች ጠላት ነውና” አለ:: info
التفاسير:

external-link copy
16 : 28

قَالَ رَبِّ إِنِّي ظَلَمۡتُ نَفۡسِي فَٱغۡفِرۡ لِي فَغَفَرَ لَهُۥٓۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلۡغَفُورُ ٱلرَّحِيمُ

16. “ጌታዬ ሆይ! እኔ ነፍሴን በደልኩ ለኔም ማር” አለ ለርሱም ምህረት አደረገለት:: እርሱ መሓሪና አዛኝ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
17 : 28

قَالَ رَبِّ بِمَآ أَنۡعَمۡتَ عَلَيَّ فَلَنۡ أَكُونَ ظَهِيرٗا لِّلۡمُجۡرِمِينَ

17. “ጌታዬ ሆይ! በእኔ ላይ በመለገስህ ይሁንብኝ (ከስህተቴ እጸጸታለሁ):: ለአመጸኞችም ፈጽሞ ረዳት አልሆንም” አለ:: info
التفاسير:

external-link copy
18 : 28

فَأَصۡبَحَ فِي ٱلۡمَدِينَةِ خَآئِفٗا يَتَرَقَّبُ فَإِذَا ٱلَّذِي ٱسۡتَنصَرَهُۥ بِٱلۡأَمۡسِ يَسۡتَصۡرِخُهُۥۚ قَالَ لَهُۥ مُوسَىٰٓ إِنَّكَ لَغَوِيّٞ مُّبِينٞ

18. በከተማይቱም ውስጥ ፈሪና የሚጠባበቅ ሆኖ አደረ:: በንጋቱም ያ ትላንት እርዳታን የጠየቀው ሰው በጩኸት እርዳታን ይጠይቀዋል:: ሙሳም ለእርሱ፡- “አንተ በእርግጥ ግልጽ ጠማማ ነህ” አለው:: info
التفاسير:

external-link copy
19 : 28

فَلَمَّآ أَنۡ أَرَادَ أَن يَبۡطِشَ بِٱلَّذِي هُوَ عَدُوّٞ لَّهُمَا قَالَ يَٰمُوسَىٰٓ أَتُرِيدُ أَن تَقۡتُلَنِي كَمَا قَتَلۡتَ نَفۡسَۢا بِٱلۡأَمۡسِۖ إِن تُرِيدُ إِلَّآ أَن تَكُونَ جَبَّارٗا فِي ٱلۡأَرۡضِ وَمَا تُرِيدُ أَن تَكُونَ مِنَ ٱلۡمُصۡلِحِينَ

19. ሙሳ ያንን እርሱ ለሁለቱም ጠላት የሆነው ሰው በኃይል ሊይዘው በፈለገም ጊዜ “ሙሳ ሆይ በትላንትናው ቀን ነፍስን እንደ ገደልክ ልትገድለኝ ትፈልጋለህን? በምድር ላይ ጨካኝ መሆንን እንጂ ሌላ አትፈልግም ከመልካም ሰሪዎች መሆንን አትፈልግም” አለው። info
التفاسير:

external-link copy
20 : 28

وَجَآءَ رَجُلٞ مِّنۡ أَقۡصَا ٱلۡمَدِينَةِ يَسۡعَىٰ قَالَ يَٰمُوسَىٰٓ إِنَّ ٱلۡمَلَأَ يَأۡتَمِرُونَ بِكَ لِيَقۡتُلُوكَ فَٱخۡرُجۡ إِنِّي لَكَ مِنَ ٱلنَّٰصِحِينَ

20. ከከተማይቱም ዳርቻ አንድ ሰው እየሮጠ መጣ “ሙሳ ሆይ! ሹማምንቶቹ ሊገድሉህ ባንተ ይመካከራሉና ውጣ እኔ ላንተ ከመካሪዎች ነኝና” አለው:: info
التفاسير:

external-link copy
21 : 28

فَخَرَجَ مِنۡهَا خَآئِفٗا يَتَرَقَّبُۖ قَالَ رَبِّ نَجِّنِي مِنَ ٱلۡقَوۡمِ ٱلظَّٰلِمِينَ

21. የፈራና የሚጠባበቅ ሆኖም ከእርሷ ወጣ:: “ጌታዬ ሆይ! ከበደለኞች ህዝቦች አድነኝ” አለ:: info
التفاسير: